የቀድሞዎቹ የህወሃት መሪዎች ለአሜሪካ ባለስልጣናት ማስተባበያ ሰጡ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 22/2010) የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በኢትዮጵያ የታወጀው ወታደሩ ስልጣን እንዳይወስድ ለመከላከል ነው ሲሉ የቀድሞዎቹ የህወሃት መሪዎች ለአሜሪካ ባለስልጣናት ተናገሩ። የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን በተመለከተ ማብራሪያ ለመስጠት ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ጥያቄ ያቀረቡት  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ተቀባይነት አለማግኘታቸውንም የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገልጸዋል። ከሳምንታተ በፊት በዩ ኤስ አሜሪካ በዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ ላይ የነበሩት ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ሊታወጅ ነው የሚለውን ...

Read More »

ራሱን ኮማንድ ፖስት ብሎ የሚጠራው ክፍል በኦሮምያ ክልል ባለስልጣናት ላይ የሚወስደውን እርምጃ ቀጥሎበታል

ራሱን ኮማንድ ፖስት ብሎ የሚጠራው ክፍል በኦሮምያ ክልል ባለስልጣናት ላይ የሚወስደውን እርምጃ ቀጥሎበታል (ኢሳት ዜና የካቲት 22 ቀን 2010 ዓ/ም)የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገን በማድረግ ኮማንድ ፖስት የተባለው ቡድን ተቃውሞ በነበረባቸው የኦሮምያ ክልል አካባቢዎች የሚወስደውን እርምጃ ቀጥሎበታል። ትናንት የነቀምቴ ከተማ ከንቲባ በኮማንድ ፖስት አባላት ከታሰሩ በሁዋላ ዛሬ ደግሞ ምክትል ከንቲባው ተይዘው መታሰራቸው ታውቋል። ሁለቱም ባለስልጣናት ቄሮ እየተባለ ከሚጠራው ...

Read More »

በእስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ የሆኑ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን መመልከታቸውን አቶ ኦኬሎ አኳይ ተናገሩ

በእስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ የሆኑ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን መመልከታቸውን አቶ ኦኬሎ አኳይ ተናገሩ (ኢሳት ዜና የካቲት 22 ቀን 2010 ዓ/ም)የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ በቅርቡ ከእስር ቤት ተፈተው ኖርዌይ ገቡ በሁዋላ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በእስር ቤት ውስጥ ብልታቸው የተኮላሸ፣ በድብደባ ብዛት መራመድ የማይችሉ እንዲሁም በደረሰባቸው ጥቃት ራሳቸውን ስተው ያበዱ ሰዎች መኖራቸውን ተናግረዋል። በአርበኞች ግንቦት7 አባልነት ተከሶ ...

Read More »

የወጣቶችን ፈንድ በአስቸኳይ ለማከፋፈል እንቅስቃሴ ተጀመረ

የወጣቶችን ፈንድ በአስቸኳይ ለማከፋፈል እንቅስቃሴ ተጀመረ (ኢሳት ዜና የካቲት 22 ቀን 2010 ዓ/ም)በአገሪቱ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ለወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር ተቃውሞውን ሊቀንስ ይችላል በሚል የተመደበው የወጣቶች የስራ ማስያዣ በጀት በአፋጣኝ ጥቅም ላይ እንዲውል ትዕዛዝ በመተላለፉ ሁሉም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሮችና ክልሎች ወከባ ውስጥ መውደቃቸው ታውቋል። ገንዘቡ ከተመደ በሁዋላ የባለስልጣናት ቤተሰቦችን ኪስ ከማደለብ ውጭ የፈየደው ነገር እንዳልነበር የሚገልጹት ምንጮች፣ በአዲስ አበባ ...

Read More »

የሞዛንቢክ ፖሊስ ሕገወጥ ናቸው ያላቸውን 23 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን መያዙን አስታወቀ

የሞዛንቢክ ፖሊስ ሕገወጥ ናቸው ያላቸውን 23 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን መያዙን አስታወቀ (ኢሳት ዜና የካቲት 22 ቀን 2010 ዓ/ም)ከሞዛንቢክ ዋና ከተማ ማፑቶ በ80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው ማኒካ አውራጃ አቆራርጠው በሕገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊገቡ የሞከሩ 23 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የአገሪቱ ፖሊስ ገልጿል። የስደተኞች ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ጆርጌ ማቻቫ ”ኢትዮጵያዊያኑን ስደተኞች በተኙበት ይዘናቸዋል። በአሁኑ ወቅትም በቫንዱዚ ፖሊስ ...

Read More »

የጎንደር አካባቢ ህዝብ ደስታውን ሲገልጽ ዋለ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 21/2010) ትላንት የአርበኛ ጎቤ መልኬን አንደኛ ሙት ዓመት መታሰቢያና የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮሚቴ አባላትን ከእስር መለቀቅ ምክንያት በማድረግ በቆላማው የጎንደር አካባቢ ህዝቡ ደስታውን ሲገልጽ መዋሉ ታወቀ። በተኮስ እሩምታና በመኪናጥሩምባ የታጀበው የደስታ መግለጫ ትዕይንት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የጣሰ የህዝብ እርምጃ እንደሆነ ም ታውቋል። አርበኛ ጎቤ መልኬ ከጎንደሩ ህዝባዊ እምቢተኝነት በኋላ ስማቸው ጎልቶ የወጣ ይሁን እንጂ በፊትም በልጅ አዋቂው ዘንድ ...

Read More »

በስደት የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪ አቀረበ   (ኢሳት ዲሲ–የካቲት 21/2010) አሁን ከገጠመን አደገኛ አዙሪት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመውጣት ሀገሩን የሚወድ ዜጋ ሁሉ በአንድነት መታገል አለበት ሲል በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስተያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪ አቀረበ። የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ እንዲነሳ እና የሽግግር መንግስት እንዲመሰረትም ጥሪ አቅርቧል። በስደት የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ብሄራዊ መረጋጋትና የሰላም ጥሪ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ በማለት ባወጣው ...

Read More »

ጃሬድ ኩሽነር የደህንነት ምርመራን ለማልፍ አለመቻላቸው ተነገረ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 21/2010) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የቅርብ አማካሪና የልጃቸው ባለቤት ጃሬድ ኩሽነር በኋይት ሃውስ ከፍተኛ ሰነዶችን ለማየት የሚያስችለውን የደህንነት ምርመራን ለማልፍ አለመቻላቸው ተነገረ። ፕሬዝደንት ትራምፕ ከተመረጡ ግዜ አንስቶ ከፍተኛ አማካሪያቸው አድርገው የሾሟቸው ጃሬድ ኩሽነር በጊዜያዊ የደህንነት ፈቃድ አማካሪ ሆነው ቆይተዋል። እንደ ሲ ኤን ኤን ዘገባ ከሆነ ኩሽነር ከዚህ በኋላ በቋሚነት ከፍተኛ ሰነዶችን ለማየት የሚያስችላቸው ፈቃድ ከአሜሪካ የደህንነት መስሪያ ቤት ማግኘት አይችሉም። ...

Read More »

በጋምቤላ የባጃጅ አገልግሎት ተቋረጠ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 21/2010) ጋምቤላ ከተማ የባጃጅ ታክሲ አገልግሎት መቋረጡ ተገለጸ። ከፍተኛ ግብር ተጭኖብናል ያሉት የታክሲ አሽከርካሪዎቹ ከዛሬ ጀምሮ ስራ ማቆማቸውን ነው ሪፖርተር ጋዜጣ የዘገበው። እነዚህ ለጋምቤላ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡት ባጃጆች ዛሬ ረቡዕ ከጠዋት ጀምሮ አገልግሎት ማቆማቸው የተገለጸ ሲሆን በዚህም የተነሳ ነዋሪዎች ትራንስፖርት መቸገራቸው ታውቋል። የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡት የባጃጅ ሾፌሮቹ የተጣለብን ግብር ከአቅማችን በላይ በመሆኑ መክፈል አንችልም ማለታቸው ተጠቅሷል። በጉዳዩ ...

Read More »

ሁሉም የኢህአዴግ ምክርቤት አባላት ለግንባሩ ሊቀመንበርነት መወዳደር ይችላሉ ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 21/2010) ሁሉም የኢህአዴግ ምክርቤት አባላት ለግንባሩ ሊቀመንበርነት መወዳደር እንደሚችሉ አቶ በረከት ስምኦን ገለፁ ሰሞኑን በማህበራዊ ድረ ገፅ የተለቀቀው ፅሁፍ ” የእኔ አይደለም” ሲሉም አስተባብለዋል። ህውሓት/ ኢህአዴግ አጣብቂኝ ውስጥ በገባ ቁጥር ወደ ሚዲያ በመምጣት መግለጫ በመስጠት ይታወቃሉ አቶ በረከት ስምኦን። የብአዴን ነባር አባልና በተለያዩ የድርጅት እና የመንግስት ስልጣናት ላይ በመመደብ ህውሓትን በታማኝነት ያገለገሉ ናቸው። በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ በውሸትና የተሳሳተ ...

Read More »