(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 7/2010)በኢትዮጵያ የአልኮልና የጫት ተጠቃሚ ወጣቶች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ ተገለጸ። ራሳቸውን የሚያጠፉ ወጣቶችም እየተበራከቱ መምጣታቸውን አንድ ጥናት አመልክቷል። እድሜያቸው ከ10 እስከ 24 ዓመት ከሚሆናቸው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች መሀል 51 በመቶ የሚሆኑት የጫት ሱስ አለባቸው። 45.6 በመቶ ያህሉ ደግሞ የአልኮል መጠጥ ሱሰኛ ናቸው። በሌላ በኩል በህገ ወጥ መንገድ ያለሀኪም ትዕዛዝ የሚሸጥ አነቃቂ መድሃኒት በወጣቱ ላይ ከፍተኛ አደጋ እያመጣ መሆኑ ተገለጸ። ...
Read More »የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በማስፈራሪያ መቀጠሉ ታወቀ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 7/2010) ዕሁድ የተጀመረው የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በውዝግብ እና በሕውሃት ማስፈራሪያ መቀጠሉን ምንጮች ገለጹ። የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ በ4 ድርጅቶች ስምምነት የወጣ ነው መባሉም በስብሰባው ላይ ተቃውሞ ቀስቅሷል። ቀደምቶቹን የሕውሃት መሪዎችን በብዛት ወደ ስብሰባው በማስገባት ተጽዕኖ ለማሳረፍ የተደረገው ጥረት የተፈለገውን ያህል ውጤት ባለማምጣቱ በስብሰባው አዳራሽ አካባቢ የጦር ጄኔራሎች ታይተዋል። ጡረተኞቹ እና በስራ ላይ ያሉት ጄኔራሎች ከደህነንት ሃላፊው አቶ ...
Read More »የነዳጅ ስርጭትን የማስተጓጎል ዘመቻ እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 7/2010) ለአንድ ሳምንት የተጠራው የነዳጅ ስርጭትን የማስተጓጎል ዘመቻ ለአራተኛ ቀን መቀጠሉ ታወቀ። በሰሜን ጎንደር ከመተማ የተነሳ አንድ የነዳጅ ቦቴ ተሽከርካሪ ጭልጋ ላይ ጥቃት እንደተሰነዘረበት የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በኦሮሚያ ክልል የነዳጅ አቅርቦትን ለማስተጓጎል እየተካሄደ ያለው ዘመቻም መጠናከሩን መረጃዎች ያሳያሉ። በሌላ በኩል የጭሮ ከተማ ከንቲባ ዛሬ በኮማንድ ፖስቱ መታሰራቸውን ለማወቅ ተችሏል። በነዳጅ ዝውውር ላይ የተጠራው የማስተጓጎል ዘመቻ በአራተኛ ቀኑም የነዳጅ ...
Read More »ከ7 በላይ የመከላከያ ወታደሮች ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 7/2010) በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ትጥቅ ለማስፈታት በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ከ7 በላይ የመከላከያ ወታደሮች ተገደሉ። በዞኑ አርማጭሆ ወረዳ ሮቢት ከተማ ትጥቅ ለማስፈታት የተንቀሳቀሱት የሕወሃት ወታደሮች ከአካባቢው ሕብረተሰብ ጋር መጋጨታቸውም ታውቋል። ሕዝቡ መሳሪያ ለማስፈታት በሕወሃት ታጣቂዎች ላይ በወሰደው ርምጃም ከ15 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች ቆስለዋል። በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ትጥቅ የማስፈታት ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የበርካታ የአካባቢው አርሶ አደሮች ቤትን ...
Read More »ሊቢያ በ250 ግለሰቦች ላይ የእስር ትዕዛዝ አወጣች
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 6/2010) ሊቢያ በህገወጥ ሰው ማዘዋወር ስራ ላይ ተሰማርተዋል ባለቻቸው 250 ግለሰቦች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣቷን አስታውቀች። ሊቢያውያንና ሌሎች የውጪ ዜጎች በተጠረጠሩበት በዚህ ወንጀል ከፍተኛ የደህንነት ሰራተኞች ፣ የመጠለያ ካምፕ ሃላፊዎች እና በሊቢያ የሚገኙ የኤምባሲ ሰራተኞች ተሳታፊ ናቸው ሲሉ የሊቢያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ገልጸዋል። የሙሀመድ ጋዳፊን መውደቅ ተከትሎ ከፈረንጆቹ 2011 ጀምሮ በከፍተኛ አለመረጋጋት ውስጥ የምትገኘው ሊቢያ በህገጥ ...
Read More »የሕወሐት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር ተገደለ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 6/2010) አርበኞች ግንቦት ሰባት አንድ የሕወሐት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር መግደሉን አስታወቀ። የተገደለው ከፍተኛ የሕወሃት ወታደራዊ አመራሩ የኮለኔልነት ማእረግ ያለው መሆኑ ተገልጿል። ኮለኔሉ ከመከላከያ ማዕከላዊ እዝ ሐይል የተወሰኑ ወታደሮችን በመያዝ ለከፍተኛ ተልእኮ ከሽሬ ወደ ጎንደር በማምራት ላይ እያለ የግንቦት ሰባት ታጣቂዎች ትናንት ረቡዕ ሊማሊሞ ላይ በሰነዘሩት ጥቃት መገደሉን የግንባሩ ሕዝብ ግኑኝነት አስታወቋል። የአርበኞች ግንቦት 7 ሕዝብ ግኑኝነት እንዳስታወቀው ኮሎኔል ...
Read More »አቶ ታየ ደንዳአ ታሰሩ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 6/2010) በሞያሌ ከተማ በመከላከያ ሰራዊት የተፈጸመው ግድያ በስህተት የሆነ አይደለም ያሉት የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ታየ ደንዳአ መታሰራቸው ተነገረ፡፡ አቶ ታየ በፌዴራል ፖሊስ አባላት የታሰሩት አዲሱ ገበያ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ወደ ስራ ሲሄዱ መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል። የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ በቅርቡ በሞያሌ ከተማ የተፈጸመውን ግድያ ማውገዛቸው ይታወቃል። በመከላከያ ሰራዊት አባላት በግፍ የተገደሉት ከ13 ...
Read More »ከሶማሌላንድ ጋር የተደረገው የወደብ ስምምነት ውድቅ ሆነ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 6/2010)የኢትዮጵያ መንግስት ከሱማሌላንድ ጋር የወደብ ስምምነት ማድረጉን የሶማሊያ ፓርላማ ውድቅ አደረገ። እርምጃው ሉአላዊነትን መድፈር ነው ሲል ፓርላማው አውግዟል። ዲፒ ወርልድ ወይንም ዱባይ ፖርት የተባለው የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ኩባንያና የኢትዮጵያ መንግስት የበርበራ ወደብን ድርሻ በመውሰድ ለመጠቀም ከሱማሌላንድ መንግስት ጋር ያደረጉትን ስምምነት የሱማሊያ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ውድቅ አድርጎታል። 170 አባላት ካሉት የምክርቤት አባላት ውስጥ 168 የሚሆኑት ናቸው ውድቅ ያደረጉት። የህዝብ ...
Read More »የኬኒያ ምሁራን በኢትዮጵያ የተከፈተው የፖለቲካ ቀውስ አሳስቦናል አሉ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 6/2010)በኢትዮጵያ በተከሰተው የፖለቲካ ቀውስ ኬንያ በስደተኞች ልትጥለቀለቅ ትችላለች በማለት የኬንያ ምሁራን ስጋታቸውን ገለፁ። በአዲስ አበባ ዙሪያ በየጎዳናው ሰዎች እየተገደሉ የአፍሪካ ሕብረት አዲስ አበባ ቁጭ ብሎ እስከመቼ ዝም ይላል ሲሉም ጠይቀዋል። የአፍሪካ ህብረት ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጭምር ጥሪ በማቅረብ በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ቀውስ ለማርገብ እንዲንቀሳቀስም ጠይቀዋል። ኢትዮጳያ የጭቆናው ሥረዓት ፍጻሜ ላይ ናት ሲሉም ተደምጠዋል። የኬኒያው NTV ቴሊቪዥን ትናንት ባዘጋጀው በዚህ ...
Read More »የነዳጅ ዕቀባ ዘመቻው እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 6/2010) በኢትዮጵያ በነዳጅ አመላላሽ ቦቴዎች ላይ የተጀመረው የዕቀባ ዘመቻ ውጤታም በሆነ መንገድ መቀጠሉ ተገለጸ። መንግስት ደግሞ በጉዳዩ ላይ ተከታታይ መግለጫዎችን በመስጠት ስራ ላይ መጠመዱ ታውቋል። የዕቀባ ጥሪውን ይፋ ያደረገው ቄሮ ደግሞ ተጨማሪ ርምጃዎችን እንደሚቀጥል ዛሬ አስታውቋል። ማክሰኞ የተጀመረውን የነዳጅ ተአቅቦ ጥሪ ተከትሎ የነዳጅ ቦቴ ባለንብረቶች ከኢንሹራንስ ጋር የተያያዘ ጥያቄ ሲያነሱ፣ሾፌሮቹ ደግሞ የደህንነት ዋስትና በማቅረብ ለመጓዝ ፍቃደኛ አለመሆናቸው ታውቋል። ...
Read More »