የኢህአዴግ ካድሬዎች ወጣቶች ብድር እንዲወስዱ እየለመኑ ቢሆንም ወጣቶቹ ግን “ መሸንገያ ነው” በማለት አልተቀበሉትም

የኢህአዴግ ካድሬዎች ወጣቶች ብድር እንዲወስዱ እየለመኑ ቢሆንም ወጣቶቹ ግን “ መሸንገያ ነው” በማለት አልተቀበሉትም (ኢሳት ዜና ማጋቢት 12 ቀን 2010 ዓ/ም) በአገሪቱ የሚካሄደውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ የወጣቱን ቁጣ ያበርዳል በሚል ወጣቶች ብድር እንዲወስዱ እየተጠየቁ ነው። ከአዲስ አበባ ውጭ በሚገኙ ከተሞች፣ የኢህአዴግ ካድሬዎች ቤት ለቤት እየሄዱ ወጣቶችን ብድር ውሰዱ እያሉ በመለመን ላይ ናቸው። ወጣቶች እንደሚሉት ባልተዘጋጁበትና በገንዘቡ ምን እንደሚሰሩ በውል ...

Read More »

ካለ ምንም ፍርድ አንድ ዓመት ከአንድ ወር በእስራት የቆዩት አቶ ብስራት አቢ አሁንም አልተፈቱም

ካለ ምንም ፍርድ አንድ ዓመት ከአንድ ወር በእስራት የቆዩት አቶ ብስራት አቢ አሁንም አልተፈቱም (ኢሳት ዜና ማጋቢት 12 ቀን 2010 ዓ/ም) በሰማያዊ ፓርቲ የማእከላዊ ኮሚቴ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ብስራት አቢ ከአዲስ አበባ ለሥራ ጉዳይ ወደ ደሴ ከተማ በሄዱበት ታፍነው ከተወሰዱ አንድ ዓመት ከአንድ ወር ሞልቷቸዋል። እስካሁንም ምንም ዓይነት የፍርድ ብያኔ አላገኙም። አቶ ብስራት ታፍነው ከተወሰዱ ከሁለት ወራት በኋላ ...

Read More »

ወጣት ሰይፉ ዓለሙ በማእከላዊ እስር ቤት አካላዊና በማንነቱ ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች እንደተፈጸሙበት ለፍርድ ቤት ተናገረ

ወጣት ሰይፉ ዓለሙ በማእከላዊ እስር ቤት አካላዊና በማንነቱ ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች እንደተፈጸሙበት ለፍርድ ቤት ተናገረ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 12 ቀን 2010 ዓ/ም) በሽብር ክስ የተከሰሰው ወጣት ሰይፉ ዓለሙ በማእከላዊ እስር ቤት ቆይታው ወቅት በምርመራ ሥም የተፈጸመበትን ኢሰብዓዊ የመብት ጥሰቶች አስመልክቶ ለ19ኛው ወንጀል ችሎት በአካል ቀርቦ አሰምቷል። ተከሳሹ ወጣት ሰይፉ ዓለሙ በማዕከላዊ እስር ቤት ቆይታው የደረሱበትን በደሎች አስመልክቶ ለችሎቱ ሲናገር ”በድብደባ ...

Read More »

በራሷ ችግር የተተበተበችው ኢትዮጵያ እኛን ለማደራደር ብቁ አይደለችም ስትል ደቡብ ሱዳን ገለጸች።

በራሷ ችግር የተተበተበችው ኢትዮጵያ እኛን ለማደራደር ብቁ አይደለችም ስትል ደቡብ ሱዳን ገለጸች። (ኢሳት ዜና ማጋቢት 12 ቀን 2010 ዓ/ም) ደቡብ ሱዳን ይህን ያለችው፣ የምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት በምህጻረ ቃሉ ኢጋድ፣ በደቡብ ሱዳን የእርስበርስ ግጭት ዙሪያ ለመምከር በሚቀጥለው ሳምንት አዲስ አበባ ላይ ስብሰባ እንደሚቀመጥ ይፋ መሆኑን ተከትሎ ነው። ኢትዮጵያ በራሷ የውስጥ ችግር እየታመሰች ባለችበት ሁኔታ፣ ለሯሷ መፍትሄ በመፈለግ ፋንታ ለደቡብ ...

Read More »

ግሎባል አሊያንስ ከሞያሌ ለተፈናቀሉ ወገኖች 10 ሺ ዶላር ሰጠ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 11/2010)በውጭ ሃገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያቋቋሙት ግሎባል አሊያንስ /ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት /ከሞያሌ ተፈናቅለው ኬንያ ለገቡ ኢትዮጵያውያን የ10 ሺ ዶላር እርዳታ ሰጠ። በአሜሪካ ቀይመስቀል በኩል ወደ ኬንያ ለስደተኞች የሚላከውን ገንዘብ ትላንት ለአሜሪካ ቀይ መስቀል ያበረከቱት የትብብሩ ሰብሳቢ አቶ ታማኝ በየነና ሌሎች የትብብሩ አመራሮች መሆናቸውን መረዳት ተችሏል። መጋቢት 1 ቀን 2010 በመከላከያ ሰራዊት አባላት በሞያሌ በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ ...

Read More »

በባሌ ዞን ሕጻናትን ጨምሮ 5 የአንድ ቤተሰብ አባላት ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 11/2010) በሶማሌ ክልል የልዩ ሐይል አባላት በኦሮሚያ ባሌ ዞን ሕጻናትን ጨምሮ 5 የአንድ ቤተሰብ አባላትን መገደላቸው ተነገረ። በሌላ ዜና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/ በኦሮሚያ ክልል በሶስት አቅጣጫ ገብቷል በሚል በክልሉ አሰሳ እና እስራት መጠናከሩን ምንጮች  ለኢሳት ገለጸዋል። ለኢሳት በደረሰው መረጃ በነገሌ ቦረና ዞን ማክሰኞ ሌሊት የተጀመረው አሰሳ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ከሞያሌ በ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው የመከላከያ ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር ዞን በሮቢት ከተማ አካባቢ በሚካሄደው ውጊያ ነዋሪዎች መጎዳታቸው እንዲሁም የአገዛዙ ወታደሮች መገደላቸው ታወቀ

በሰሜን ጎንደር ዞን በሮቢት ከተማ አካባቢ በሚካሄደው ውጊያ ነዋሪዎች መጎዳታቸው እንዲሁም የአገዛዙ ወታደሮች መገደላቸው ታወቀ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ/ም) ዛሬ፣ መጋቢት 11 ቀን 2010 ዓም ከጎንደር ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ሮቢት ከተማ አካባቢ በሚገኙ የገጠር የቀበሌዎች፣ አገዛዙ በከባድ የጦር መሳሪያዎች የታጀበ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት አሰማርቶ በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣ ከወታደሮች በኩልም 7 ተገድለው ...

Read More »

ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ለደረሰው የሰውና የንብረት ውድመት ከፍተኛ አመራሩ ተጠያቂ ነው አለ

ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ለደረሰው የሰውና የንብረት ውድመት ከፍተኛ አመራሩ ተጠያቂ ነው አለ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ/ም) በኢትዮጵያ ለደረሰው የዜጎች እልቂት፣ የሚሊዮኖች መፈናቀልና ከፍተኛ ንብረት ውድመት የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር ሃላፊነቱን ይወስዳል ሲል ፓርቲው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ድርጅቱ ሰሞኑን በሰጣቸው ተከታታይ መግለጫዎች፣ በኢትዮጵያ ለሚታዬው የጸጥታ መደፍረስ የቀለም አብዮት እንዲካሄድ የሚፈልጉ የምዕራብ አገራትንና ኤርትራን ተጠያቂ አድርጎ ነበር። ዛሬ ባወጣው መግለጫ ደግሞ ...

Read More »

በምስራቅ ሃረርጌ ነዋሪዎች በወታደራዊ አገዛዙ መማረራቸውን ገለጹ

በምስራቅ ሃረርጌ ነዋሪዎች በወታደራዊ አገዛዙ መማረራቸውን ገለጹ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት በተለይ በኮምቦልቻ ከተማ ካለፈው እሁድ ጀምሮ በመካሄድ ላይ ባለው ፍተሻ ፣ ነዋሪዎች ጥንድ ጥንድ ሆነው መጓዝ እንደማይችሉና ህጉን ጥሰው ቢገኙ ሊመቱ እንደሚችሉ ተነግሯቸዋል። ሃዘን ቤት ተቀምጦ ማውራት፣ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት በሁዋላ መዘዋወር እንዲሁም የተለያዩ የውጭ ጣቢያዎችን ማዬት እንደማይቻል እንደተነገራቸው ነዋሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል። ካለፈው ...

Read More »

የግብጽና ሱዳን መሪዎች ብሔራዊ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የጋራ ስምምነት ላይ ደረሱ

የግብጽና ሱዳን መሪዎች ብሔራዊ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የጋራ ስምምነት ላይ ደረሱ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ/ም) የሱዳኑ መሪ ኦማር አልበሽር በግብጽ የአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት አድርገዋል። የፕሬዚዳንቱን ጉብኝት ተከትሎ ሁለቱ አገራት በ2015 እ.ኤ.አ. የተፈረመውን የአባይ ግድብ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ኢጅብት ቱዴይ ዘግቧል። የግብጹ ፕሬዚዳንት አልሲሲና የሱዳኑ አቻቸው ኦማር አልበሽር ከመገናኘታቸው በፊት የሁለቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮችና ...

Read More »