የግብጽና ሱዳን መሪዎች ብሔራዊ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የጋራ ስምምነት ላይ ደረሱ

የግብጽና ሱዳን መሪዎች ብሔራዊ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የጋራ ስምምነት ላይ ደረሱ
(ኢሳት ዜና ማጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ/ም) የሱዳኑ መሪ ኦማር አልበሽር በግብጽ የአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት አድርገዋል። የፕሬዚዳንቱን ጉብኝት ተከትሎ ሁለቱ አገራት በ2015 እ.ኤ.አ. የተፈረመውን የአባይ ግድብ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ኢጅብት ቱዴይ ዘግቧል።
የግብጹ ፕሬዚዳንት አልሲሲና የሱዳኑ አቻቸው ኦማር አልበሽር ከመገናኘታቸው በፊት የሁለቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮችና የደኅንነት ባለስልጣናት ስብሰባው አድርገው ነበር።
3ቱ አገራት ግድቡ በውሃ ከመሞላቱ በፊት ግብጽና ሱዳን ስምምነታቸውን እንዲገልጹ መፈራረማቸውን በመግለጽ፣ ስምምነቱ ተግባራዊ እንዲሆን ሁለቱም አገራት ቃል መግባታቸው በዘገባው ተመልክቷል።
ግብጽና ሱዳን በከፍተኛ ደረጃ የተዋቀረ የሁለትዮሽ ወታደራዊ፣ የዓባይ ወንዝ ሸለቆ አቅጣጫ ቅየሳና የድንበር ጉዳይ አስፈጻሚ የምክክር ኮሚቴ ለማቋቋም ተስማምተዋል። ሁለቱም አገራት ብሔራዊ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ በጋራ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ፕሬዚዳንት አል ሲሲ ገልጸው፣ በተጨማሪም በኤሌትሪክሲቲ፣ በኃይል ማመንጫና በመሰረተ ልማት ግንባታና በባህር ኃይላቸው ዙሪያ መወያየታቸውንም ተናገረዋል።
በአባይ ገድብ ዙሪያ ሱዳን ለርጅም ጊዜ የኢትዮጵያን አቋም ስትደግፍ ቆይታለች። ግብጽም በሱዳን አቋም በመበሳጨት በሁለቱ ድንበሮች አካባቢ ሃይሏን ስታስበሰብ ነበር። ይሁን እንጅ ሱዳን ከግብጽ ጎን ለመሰለፍ ፍላጎት ማሳያት መጀመሩዋ ምናልባትም ኢትዮጵያ በውስጥ ፖለቲካዋ ተዳክማለች የሚል እምነት እየያዘች በመምጣቷ ሊሆን እንደሚችል አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። ግብጽ በውስጥ ችግሯ ተቆልፋ በተያዘችበት ወቅት ሱዳን ከኢትዮጵያ ጎን መቆሟን የገለጸችበት አጋጣሚ፣ አገሪቱ የሁለቱን አገራት የሃይል ሚዛን እያየች አቋሟን እንደምትቀይር ማረጋገጫ ተደርጎ ተወስዷል።