(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 2/2010) የኮንሶ ህዝብ የመብት ጥያቄውን ካነሳበት ጊዜ ጀምሮ ከ200 በላይ ሰዎች እንደተገደሉ ተገለጸ። የተገደሉት ሰዎች ስም ዝርዝርም ይፋ ሆኗል። የኮንሶን ህዝብ የመብት ጥያቄ የሚያስተባብሩ አካላት ለኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሲቪል ካውንስል በላኩት ሪፖርት ላይ የዞን መዋቅር መብት በመጠየቅ የተጀመረውን ተቃውሞ ለማፈን የመከላከያ ሰራዊት፣ የፌደራል ፖሊስና የደቡብ ክልል ልዩ ሃይል የወሰዱት የግድያ፣ የማሰቃየትና ሌሎች ርምጃዎች በዝርዝር ቀርበዋል። ከፌደራል ጀምሮ እስከ ወረዳ ...
Read More »ኤች አር 128 የተባለው ረቂቅ ሕገ ደንብ ዛሬ ድምጽ ይሰጥበታል ተብሎ ይጠበቃል
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 2/2010)ኤች አር 128 የተባለው ረቂቅ ሕገ ደንብ ዛሬ በአሜሪካ ምክርቤት ይቀርባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገለጸ። ይሄ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ረቂቅ ሕገ ደንቡ ስለመጽደቅና አለመጽደቁ የታወቀ ነገር የለም። ዛሬ ከሰአት በኋላ በአሜሪካ ምክር ቤት የሚቀርበው ይህ ረቂቅ ህገ ደንብ ከአንድ መቶ በላይ የምክር ቤቱ አባላት የደገፉት መሆኑም ታውቋል። በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት እንዲከበርና ሁሉንም የሳተፈ መንግስታዊ ስርአት እንዲኖር ለማበረታታት በሚል ...
Read More »10 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ በሞቃዲሾ አውሮፕላን ማረፍያ ተያዘ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 1/2010) ንብረትነቱ የማን እንደሆነ ያልታውቀ 10 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ሞቃዲሾ አውሮፕላን ማረፍያ ተያዘ ። ገንዘቡ ከዩናይትድ አረብ ኤምሬት መዲና አቡዳቢ ወደ ሞቃዲሾ በበረረ አውሮፕላን ውስጥ መገኘቱ በሃገራቱ መካከል ውጥረት አስከትሏል። ዩናይትድ አረብ ኤምሬት ከሶማሌ ላንድ መንግስት ጋር በርበራ ወደብ ላይ ያደረገችው ስምምነት የሶማሊያን መንግስት ማስቆጣቱ ይታወሳል። በዚህም የሶማሊያ መንግስት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሉዓላዊነቴ ተደፍሯል በማለት የተባበሩት አረብ ...
Read More »እምቦጭ አረምን ለማስወገድ የ20 ሚሊዮን ብር ዕርዳታ ተሰጠ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 1/2010)በእስር ላይ የሚገኙት የኬኬ ድርጅት ባለቤት አቶ ከተማ ከበደ በጣና ሐይቅ ላይ የተንሰራፋውን እምቦጭ አረም ለማስወገድ የ20 ሚሊዮን ብር ዕርዳታ ሰጡ። አቶ ከተማ ከበደ፣ ዕርዳታውን ያደረጉት በወኪላቸውና በድርጅታቸው ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ በአቶ ቦጋለ ማሞ አማካይነት ነው፡፡ የኬኬ ድርጅት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጁ እንዳሉት አቶ ከተማ ከበደ ዕርዳታውን ያደረጉት በሁለት መንገዶች ነው፡፡ — በጥሬ ገንዘብና ማሽን በመግዛት፡፡ ስጦታው ...
Read More »ስቃይ ሲፈጸምባቸው የነበሩ ግለሰቦች ምስክርነታቸውን ሰጡ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 1/2010) በሕወሐት መራሹ አገዛዝ በማእከላዊ ምርምራ እስር ቤት ስቃይ ሲፈጸምባቸው የነበሩ ግለሰቦች ለመንግስት መገናኛ ብዙሀን ምስክርነታቸውን ሰጡ። ማእከላዊ ለሰው ልጅ ሕሊና የሚከብድና ዘር እስከማጥፋት የሚደርስ እርምጃ በዚህ መንግስት ሲወስድበት እንደነበር የችግሩ ሰለባዎች ገልጸዋል። ባለፉት 26 አመታት በማዕከላዊ ምርመራ እስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ ሲፈጸምባቸው የነበሩ ግለሰቦች ምስክርነታቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ለሆነው የኦሮሞ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ/ኦ ቢ ኤን/ ገልጸዋል። ለሚዲያ ተቋሙ ...
Read More »ኤችአር 128ን የአሜሪካ ኮንግረስ እንዲያጸድቀው ጥሪ ቀረበ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 1/2010)በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ አስተዳደር እንዲኖርና የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ ተጽእኖ የሚያሳድረውን ኤችአር 128 የአሜሪካ ኮንግረስ እንዲያጸድቀው ስድስት የሰብአዊ መብትና የዲያስፖራ ቡድኖች ጥሪ አቀረቡ። ኤችአር 128 በነገው እለት በአሜሪካ ኮንግረንስ ፊት ቀርቦ ድምጽ ይሰጥበታል። ኤች አር 128 በኮንግረሱ እንዲጸድቅ ጥሪ ያቀረቡት ስድስት የሰብአዊ መብትና የዲያስፖራ ቡድኖች ናቸው። እነሱም ሒዩማን ራይትስዎች፣ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ፕሮጀክት፣የኢትዮጵያ አድቮኬሲ ኔትወርክ፣የአማራ ማህበር በአሜሪካ፣የኦሮሞ አድቮኬሲ ትብብር፣ቅንጅት ...
Read More »ምስራቅ አፍሪካ ለሁለት ልትሰነጠቅ ትችላለች ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 28/2010) ምስራቅ አፍሪካ ለሁለት ልትሰነጠቅ እንደምትችል አንድ ጥናት አመለከተ ጥናት አመለከተ። እንደ ጥናቱ ከሆነ በደቡብ ምዕራብ ኬንያ ብዙ ኪሎ ሜትርን የሚሸፍን መሬት ለሁለት ተገምሷል። የመሬቱ ለሁለት መገመስም ከጊዜ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱንና ስጋት ማጫሩን ነው ዘገባዎች ያመለከቱት። የስምጥ ሽለቆን ተከትሎ 3000 ኪሎ ሜትር ይደርሳል የተባለውና ከምስራቅ አፍሪካ እስከ ዚምባቡዌ ይደርሳል የተባለው የመሬት መሰንጠቅ አፍሪካን ለ2 እኩል ያልሆነ ቦታ ይከፍላታል ...
Read More »በኢትዮጵያ፣በግብጽና በሱዳን መካከል የተካሄደው ውይይት ያለ ስምምነት ተጠናቀቀ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 28/2010)በኢትዮጵያ፣በግብጽና በሱዳን መካከል በካርቱም የተካሄደው ውይይት ያለ ስምምነት መጠናቀቁ ታወቀ። የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለዜና ሰዎች እንደገለጹት በርካታ ጉዳዮች ላይ ውይይት ቢደረግም በአንድም ጉዳይ ላይ ከስምምነት ሳይደረስ ስብሰባው ተጠናቋል። ከ7 አመት በፊት የተገነባው የሕዳሴው ግድብ በግርጌ ባሉ ሃገራት ላይ የሚያሳድረውን ተጽእኖ በተመለከተ በፈረንሳይ ኩባንያ የተደረገውን ጥናት ለማጽደቅ ሃገራቱ ሳይስማሙ ቆይተዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና የውሃ ሚኒስትሮች እንዲሁም የደህንነት ባለሙያዎች ...
Read More »ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ 11 ታዋቂ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ትላንት ተፈቱ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 28/2010) ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ 11 ታዋቂ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ትናንት ተፈቱ ። በሌላ ዜና ከወር በላይ በመላ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ በቀር የተቋረጠው የኢንተርኔት የዳታ አገልግሎት ዛሬ መጀመሩ ታውቋል። መጋቢት 16 ቀን 2010 በድጋሚ ታስረው የነበሩት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አቶ አንዱአለም አራጌ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ አዲሱ ጌታሁን፣ ጦማሪ ዘላለም ወርቅአገኘሁ፣ ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁን፣ ጋዜጠኛ በፈቃዱ ሃይሉ፣ ወ/ት ወይንሸት ሞላ፣ ...
Read More »በማዕከላዊ እስር ቤት የሚገኙ እስረኞች ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተዛወሩ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 28/2010) በማዕከላዊ እስር ቤት የሚገኙ እስረኞች ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጊዜያዊ ማቆያ እንዲዛወሩ ተደረገ። የእስረኛ ጠያቂዎች ከዛሬ ጀምሮ ወደ ማዕከላዊ እንዳይመጡ የሚገልጽ ማስታወቂ በእስር ቤቱ አጥር ላይ መለጠፉን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጊዜያዊ ማቆያ ከተዛወሩት መካከል የኦሮሚያ ክልል ፍትህ ቢሮ ቃል አቀባይ አቶ ታዬ ደንደአ እና መምህር ስዩም ተሾመ እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል። የአገዛዙ ...
Read More »