በጅግጅጋ ባለፈው ቅዳሜ በደረሰው የጎርፍ አደጋ እስካሁን ከ7 ያላነሰ አስከሬን መገኘቱ ታወቀ

በጅግጅጋ ባለፈው ቅዳሜ በደረሰው የጎርፍ አደጋ እስካሁን ከ7 ያላነሰ አስከሬን መገኘቱ ታወቀ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 05 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ነዋሪዎ እንደገለጹት ባለፈው ቅዳሜ በጅግጅጋ ቀበሌ 10፣ 17 እና 18 የተፈጠረውን ጎርፍ ተከትሎ በርካታ ዜጎች በጎርፍ ተወስደው ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፣ ኢሳት ዘገባውን ባቀረበ ማግስት የክልሉ ፖሊስ እና መከላከያ ፍለጋ ጀምረው እስካሁን የ7 ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል። የበርካታ ዜጎች አስከሬን አሁንም ድረስ ...

Read More »

በጉጂ ዞን ግጭት ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 5/2010)  በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን ሀገረማርያም ከተማ ብሄር ተኮር ግጭት ተቀሰቀሰ። የጌዲዮ ተወላጆች ከከተማችን ይውጡልን የሚሉ ግለሰቦች ቀሰቀሱት በተባለው በዚሁ ግጭት በርካታ ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል ። ወደሀገረማርያም የስልክ አገልግሎትም መቋረጡ ተሰምቷል። ከዲላ በኋላ ያለውም መንገድ ተዘግቷል። ከ15ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውንም የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። እያበቃ ባለው ሳምንት መጀመሪያ አንስቶ በጉጂ ዞንና በጌዲዮ ዞን ድንበር አካባቢ በጉጂና በጌዲዮ ብሔረሰቦች መካከል ...

Read More »

ዩጋንዳ የኤርትራና የሱዳን ስደተኞችን ልትቀበል ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 5/2010) ዩጋንዳ እስራኤል ከሃገሯ እንዲወጡ ካዘቸቻቸው ስደተኞች መካከል 500 የኤርትራና የሱዳን ስደተኞችን እቀበላለሁ አለች። ዩጋንዳ ስደተኞቹን ለመቀበል የወሰነችው እስራኤል በርካታ አፍሪካውያን ስደተኞችን ከሃገር አባርራለሁ ማለቷን ተከትሎ ነው። እስራኤል በሃገሯ የሚኖሩ አፍሪካውያን ስደተኞችን አስወጣለሁ ስትል ቆይታለች። ይህን ተከትሎም ዩጋንዳ እስራኤል ከሃገር ከምታስወጣቸው አፍሪካውያን መካከል 500 ያህል የሚሆኑ የኤርትራና የሱዳን ስደተኞችን ተቀብላ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች። ጥሪውን በስደተኞች ተወካዩ ሙሳ ...

Read More »

የዋልድባ መነኮሳት ከእስር ተፈቱ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 5/2010) የዋልድባ መነኮሳት ከእስር ተለቀቁ። መነኮሳቱን ጨምሮ 114 የሕሊና እስረኞች ክሳቸው እንዲቋረጥ መደረጉ ይታወሳል። አቃቤ ሕግ የ114 የሕሊና እስረኞች ክስ እንዲቋረጥ ያደረገው ከትላንት በስቲያ ረቡዕ ነው። ክሱ እንዲቋረጥ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ያስታወቀው አቃቤ ሕግ ተከሳሾቹ ለሚገኙበት ለቂሊንጦ እስር ቤት የመፍቻ ትዕዛዝ እንዲጻፍለት ጠይቋል። በዚሁም መሰረት ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ሁለቱን የዋልድባ ...

Read More »

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በመቀሌ ከተማ ጉብኝት አደረጉ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 5/2010) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከትግራይ ልዩ ልዩ ወረዳዎች ከተውጣጡ ሰዎች ጋር በመቀሌ ከተማ ውይይት አደረጉ። ዶክተር አብይ አህመድ በትግርኛ ቋንቋ ባደረጉት ንግግር የትግራይ ሕዝብ የኢትዮጵያ መሰረት ነው ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ መቀሌ ያመሩት በኢትዮጵያ ከሚገኙ ተቃዋሚዎች ጋር በቤተመንግስት የራት ግብዣ ካደረጉ በኋላ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ መቀሌ ካመሩ በኋላ የሰማዕታት ሃውልት ተብሎ ...

Read More »

በመቀሌ በ8 ቢሊየን ብር የውሃ ግድብ ግንባታ ሊጀመር ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 5/2010)በመቀሌ ከተማ ያለውን የውሃ እጥረት በዘላቂነት ለመፍታት የፌደራል መንግስት ከቻይና መንግስት ባገኘው 8 ቢሊየን ብር የግድብ ግንባታ እንደሚጀምር ተገለጸ። የግድቡ ግንባታ ሲጠናቀቅም ለከተማዋ ከሚያስፈልገው የውሃ መጠን ከሁለት እጥፍ በላይ ተጨማሪ ውሃ እንደሚያስገኝም ተመልክቷል። የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ/ሕወሃት/ ንብረት የሆነው ሬዲዮ ፋና እንደዘገበው የመቀሌ ከተማ በየቀኑ የሚያስፈልገው 50ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ቢሆንም እየቀረበ ያለው ግማሽ ያህሉ 25ሺ ሜትር ኪዩብ ...

Read More »

በአቶ በረከት ስምኦን አማካኝነት ብአዴንን እንደገና ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ ተጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 5/2010) የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ መሪዎች በአቶ በረከት ስምኦን አማካኝነት ብአዴንን እንደገና ለመቆጣጠር በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። ከአቶ በረከት ጋር በመሆን በብአዴን ውስጥ የሕወሃትን ጉዳይ ለማስፈጸም የተመለመሉ ግለሰቦች ማንነትም ታውቋል። ከነዚህ ውስጥ ከፊሉ ከዚህ ቀደምም በሕወሃት አፍቃሪነት የሚታወቁና በአመራር ላይ የነበሩ መሆናቸውንም የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።  በነሐሴ ላይ ከሚካሄደው የኢሕአዴግ ጉባኤ አስቀድሞ በሚካሄደው የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ...

Read More »

በግብጽ ሕጻናትን ለገበያ ባቀረቡ ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 4/2010) በግብጽ  ሕጻናትን በድረገጽ ለገበያ ባቀረቡ ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ። ድርጊቱን ፈጽመዋል የተባሉት ግለሰቦች ጉዳይም በወንጀለኞች ፍርድ ቤት እንዲታይ መደረጉም ታውቋል። እንዲህ አይነቱ ጉዳይ በፍርድ ቤት ቀርቦ ሲታይም ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል። በግብጽ ፍርድ ቤት ሲቀርብ የመጀመሪያው ነው በተባለው ሕጻናትን በኦንላይን ለገበያ በማቅረቡ ጉዳይ ተሳታፊ ናቸው ባሏቸውን ግለሰቦች ላይ የግብጽ የሕግ አካላት ክስ መመስረታቸውን ነው ዘገባዎች ያመለከቱት። የግብጽ ...

Read More »

በሙስና ተከሰው የነበሩት የሕወሃት አባላት ተፈቱ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 4/2010)በሙስና ተከሰው የነበሩት የሕወሃት አባላቱ አቶ ነጋ ገብረእግዚአብሔርና አቶ ገብረስላሴ ገብሬ በዋስትና መፈታታቸው ተነገረ። በሕጉ መሰረት ቢሆን ኖሮ በሙስና የተከሰሰ ሰው የዋስትና መብት አይፈቀድለትም። በእነ አቶ መላኩ ፈንታ የክስ መዝገብ ተከሰው የነበሩት የነጻ ትሬዲንግ ባለቤት አቶ ነጋ ገብረእግዚአብሔር በ750ሺ ብር የኮሜት ኩባንያ ባለቤት አቶ ገብረስላሴ ገብሬ ደግሞ በ5 መቶ ሺ ብር ዋስ ተለቀዋል። ሁለቱ ተከሳሾች በሙስና ወንጀል ከታሰሩ ...

Read More »

የአዲስአበባና የድሬደዋ ምርጫ በአንድ አመት እንዲራዘም ተወሰነ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 4/2010)በዚህ አመት መካሄድ የነበረበት የአዲስአበባና የድሬደዋ ምርጫ እንዲሁም በመላ ሃገሪቱ የሚካሄዱ የአካባቢና ማሟያ ምርጫ በአንድ አመት እንዲራዘሙ ፓርላማው ዛሬ ወሰነ። ከአመት በኋላም ምርጫው መቼ ይካሄዳል ለሚለው ወርና ቀን ተቆርጦ አልተቀመጠለትም። 8 የፓርላማ አባላትም ድምጸ ተአቅቦ ማድረጋቸው ተሰምቷል። ከ230 በላይ የፓርላማ አባላትም አልተገኙም። የሕወሃቱ ኤፈርት ንብረት የሆነው ሬዲዮ ፋና እንደዘገበው በፓርላማው የዛሬ ውሎ የማሟያ ምርጫም ለአንድ አመት ተራዝሟል። ፓርላማው ...

Read More »