ወ/ሮ ጠይባ ሃሰን የአቶ ለማ መገርሳ ምክትል ሆነው ተሾሙ

ወ/ሮ ጠይባ ሃሰን የአቶ ለማ መገርሳ ምክትል ሆነው ተሾሙ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 10 ቀን 2010 ዓ/ም) የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ የሆኑት ወ/ሮ ጣይባ ሃሰን የኦሮምያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመዋል። በሻሸመኔ ህዝባዊ የለውጥ ትግል በሚካሄድበት ወቅት፣ የአጋዚ ወታደሮች ሲወስዱት የነበረውን እርምጃ አጥብቀው በመቃወም እንዲሁም በተለያዩ ዝርፊያዎች የተሰማሩ የህወሃት አባላትን በቁጥጥር ስር በማድረግና በድፍረት ለመገናኛ ብዙሃን አሳባቸውን በመስጠት የሚታወቁት ወ/ሮ ጣይባ ሃሰን ...

Read More »

በምስራቅ ጎጃም ዞን የመርጦ ለማርያም ከተማ ወጣቶች በአገዛዙ ላይ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ዋሉ

በምስራቅ ጎጃም ዞን የመርጦ ለማርያም ከተማ ወጣቶች በአገዛዙ ላይ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ዋሉ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 10 ቀን 2010 ዓ/ም) ለተቃውሞው መነሻ የሆነው ለድልድይ ስራ የዋለ ትርፍ ብረት በ4 መኪኖች ተጭነው ወደ ትግራይ ክልል መጓጓዛቸውን የአካባቢው ህዝብ በመቃወሙ ነው። ወጣቶቹ እቃውን የጫኑትን መኪኖች አስቁመው እቃው እንዲራገፍ ሲጠይቁ ከወረዳው ባለስልጣናት ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል። ባለስልጣኑ ግለሰቦቹ ህጋዊ ፍቃድ እንዳላቸው ገልጸው ለማሳመን ቢሞክሩም ...

Read More »

አፍሪካዊያን ስደተኞች በየመን ባለስልጣናት ግድያ፣ ሰቆቃና መደፈር ይፈጸምባቸዋል ሲል ሂውማን ራይትስ ወች አስታወቀ

አፍሪካዊያን ስደተኞች በየመን ባለስልጣናት ግድያ፣ ሰቆቃና መደፈር ይፈጸምባቸዋል ሲል ሂውማን ራይትስ ወች አስታወቀ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 10 ቀን 2010 ዓ/ም) አፍሪካዊያን ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞች ላይ ኢሰብ ዓዊ በሆነ ሁኔታ መብቶቻቸውን በመጣስ ግድያ፣ ሰቆቃና መደፈር ይፈጸምባቸዋል ሲል ሂውማን ራይትስ ወች መግለጫ አወጣ። በሰሜናዊ የመን በምትገኘው የባህር ወደብ ከተማ በሆነችው አደን ለምስራቅ አፍሪካዊያን ስደተኞች በተናጠል በእስር ቤት ውስጥ እንዲታሰሩ ተደርገዋል። በእስር ቤቱ ...

Read More »

በወልዲያ እግር ኳስ ቡድን ላይ የተጣለውን ቅጣት በመቃወም በአዲስ አበባ ከተማ የቡድኑ ደጋፊዎችና አጋሮቻቸው ተቃውሟቸውን አሰሙ፤ አሰልጣኝ ስዩም አባተ ታመው ሆስፒታል ገቡ

በወልዲያ እግር ኳስ ቡድን ላይ የተጣለውን ቅጣት በመቃወም በአዲስ አበባ ከተማ የቡድኑ ደጋፊዎችና አጋሮቻቸው ተቃውሟቸውን አሰሙ፤ አሰልጣኝ ስዩም አባተ ታመው ሆስፒታል ገቡ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 10 ቀን 2010 ዓ/ም) በመላው ኢትዮጵይያ በእግር ኳስ ሜዳዎች ከከስፖርት መርህ ውጪ ስርዓት አልበኝነት ከጊዜ ወደጊዜ እየተሳፋ መጥቷል። በዚህም የብዙ ሰላማዊ ዜጎች ህይወትና ንብረት ለመውደም ምክንያት ሆኗል። ችግሩን ከመሰርቱ እንዲፈታ ወቅታዊ የሕግ እርምጃዎች መውሰድ የነበረበት ...

Read More »

ድምጻዊ ታምራት ደስታ በድንገተኛ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ድምጻዊ ታምራት ደስታ በድንገተኛ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 10 ቀን 2010 ዓ/ም) ድምጻዊ ታምራት ደስታ ለሕክምና ወደ ስላሴ ክሊኒክ በመኪና እየተጓዘ እያለ በድንገተኛ አደጋ ራሱን ስቶ ሕይወቱ አልፏል። ድምጻዊ ታምራት ደስታ ባለትዳርና የ5 ልጆች አባት ነበር። በሻሸመኔና ሃዋሳ ከተማ አማካኝ ላይ በምትገኘው በጥቁር ውሃ ከተማ በ1971 ዓ.ም የተወለደውና በሻሸመኔ ከተማ ያደገው ድምጻዊ ታምራት ደስታ ለቤተሰቦቹ 2ኛ ...

Read More »

ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ 250 ዳኞችን ከስራ አባረሩ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 9/2010) የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ 250 ዳኞችን በሙስናና ከትምህርት ማስረጃ ጋር በታያያዘ አባረሩ። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የመሪነት መንበር አባታቸውን ሎራን ካቢላን ተክተው የያዙት ጆሴፍ ካቢላ ከአመታት በፊት በተመሳሳይ ወደ አንድ መቶ የሚጠጉ ዳኞችን አባረዋል። ወደ 80 ሚሊየን ሕዝብ የሚኖርባትና በማዕድን ሃብት የበለጸገችው ሐገር መሪ ጆሴፍ ካቢላ በሰጡት ትዕዛዝ በአጠቃላይ 256 ዳኞች ተባረዋል። የተባረሩት ዳኞች በከፊል የሕግ ...

Read More »

ኢትዮጵያ በውጭ ምንዛሪ እጥረት ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባት ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 9/2010)ኢትዮጵያ በውጭ ምንዛሪ እጥረት ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ። ዶክተር አብይ አሕመድ ከባለሃብቶች ጋር ባካሄዱት ውይይት ላይ እንደገለጹት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገር ቤት የሚልኩትን የውጭ ምንዛሪ ማቀብ ከፍተኛ ጉዳት አለው። እናም በውጭ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን መንግስትን ለመቆንጠጥ ብላችሁ የምታደርጉት ርምጃ ሕዝብን እየጎዳ ነው ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ እንዳሉት የውጭ ምንዛሪ ችግር ለሚቀጥሉት 10 ...

Read More »

አቶ በቀለ ገርባ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መልዕክት አስተላለፉ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 9/2010) አቶ በቀለ ገርባ የሰላም ጠንቅ የሆነውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአስቸኳይ እንዲያነሱ ለጠቅላይ ሚኒስትር  አብይ አህመድ መልዕክት አስተላለፉ። በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ኦፌኮ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ በግላቸው ባስተላለፉት በዚሁ መልዕክት ህዝቡ ለሰላም ዘብ ይቁም በማለት ብቻ ሰላም አይገኝም ብለዋል። አቶ በቀለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ቢሮአቸው ተመልሰው በአራት ጉዳዮች ላይ ውሳኔ እንዲሰጡም ጠይቀዋል። አቶ ...

Read More »

ለሰአታት የተቋረጠው አለም አቀፍ በረራ ዘግይቶ ጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 9/2010) የኢትዮጵያ ሲቪል አቭዬሽን የአየር ትራፊክ ሰራተኞች በመቱት አድማ ለሰአታት የተቋረጠው አለም አቀፍ በረራ ዘግይቶ ጀመረ። ወደ ሶስት ሰአታት የተስተጓጎለው በረራ መነሻው ምክንያት የአየር ትራፊክ ሰራተኞች ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያቀረቡት ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ እንደሆነም ተመልክቷል። በውጤቱም 48 በረራዎች ተስተጓጉለዋል፣ወደ ለንደንና ዱባይ የሚበሩ አውሮፕላኖችም ከዘገዩት ውስጥ ይጠቀሳሉ። በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከጠዋቱ 3 ሰአት እስከ 4.30 የተስተጓጎለው በረራ የቀጠለው ጥያቄውን ...

Read More »

በምስራቅ ጎጃም ብረት ጭኖ ወደ ትግራይ እያመራ የነበረ ከባድ ተሽከርካሪ በህዝብ ታገተ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 9/2010) በምስራቅ ጎጃም መርጦ ለማርያም ብረት ጭኖ ወደ ትግራይ እያመራ የነበረ ከባድ ተሽከርካሪ በህዝብ ተቃውሞ መታገቱ ተሰማ። ለኢሳት በደረሰው መረጃ ላይ እንደተመለከተው ቁርጥራጭ ብረት የጫነው ተሽከርካሪ ወደ ትግራይ ክልል እያመራ መሆኑ ጥቆማ የደረሰው የመርጦ ለማሪያም ከተማ ነዋሪ ተሽከርካሪውን በማስቆም ተቃውሞውን ሲገልጽ ነበር። በህዝቡና በአካባቢው ባለስልጣናት መሃል ውዝግብ መነሳቱም ተሰምቷል። በሌላ በኩል በሰሜን ጎንደር ዞን ህዝቡን መሳሪያ ለማስፈታት በተንቀሳቀሱ ...

Read More »