በባህርዳር ቤተክርስቲያን ተፈናቃዮችን ከግቢዋ እንድታስወጣ ብትጠየቀም አሻፈረኝ አለች (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 25 ቀን 2010 ዓ/ም) ከቤንሻንጉል ጉሙዝና ከኦሮምያ ክልሎች ተፈናቅለው ባህርዳር በጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተጠልለው የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ግቢውን ለቀው እንዲወጡ የደህንነት አባላት ለቤተክርስቲያኗ ትእዛዝ ቢሰጡም፣ ቤተክርስቲያኗ ግን ተፈናቃዮችን ለማስወጣት ፈቃዳኛ አለመሆኗን ገልጻለች። የደህንነት ሰራተኞች የተፈናቃዮችን አመራሮች ይዘው በማሰር እና ተፈናቃዮች ወደ መጡበት ክልል ወይም ወደ ትውልድ አካባቢያቸው እንዲሄዱ እንዲያግባቡ ...
Read More »ሞያሌ መረጋጋት አለመቻሉዋን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ ከከተማዋ የተፈናቀሉት ዜጎች እስካሁን አለመመለሳቸውም ታውቋል
ሞያሌ መረጋጋት አለመቻሉዋን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ ከከተማዋ የተፈናቀሉት ዜጎች እስካሁን አለመመለሳቸውም ታውቋል (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 25 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት የሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት በየጊዜው የሚፈጽሙት ግድያ ፣ ነዋሪዎችን አፍኖ የመውሰድ ድርጊት ሊቆም በለመቻሉ እንደ ልባቸው ወጥተው መግባት አልቻሉም። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ አብዛኛው የከተማው ነዋሪዎች ቤታቸውን ዘግተው ለመቀመጥ መገደዳቸውን የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ የሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት መንገድ ላይ ...
Read More »በአባይ ግድብ የምንጣሮ ስራ የሰሩ መለስተኛ ተቋራጮች ገንዘባቸው መዘረፉን ገለጹ ሜቴክ የተባለውን ተቋም ዋና ተጠያቂ አድርገዋል
በአባይ ግድብ የምንጣሮ ስራ የሰሩ መለስተኛ ተቋራጮች ገንዘባቸው መዘረፉን ገለጹ ሜቴክ የተባለውን ተቋም ዋና ተጠያቂ አድርገዋል (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 25 ቀን 2010 ዓ/ም) ቅሬታ አቅራቢዎች እንደሚሉት በህወሃቱ ጄ/ል ክንፈ ዳኘው ይመራ የነበረው ሜቴክ የአባይ ግድብ ውሃ የሚተኛበትን ደን እንዲመነጥሩ ጡረታ ከወጡ የህወሃት ነባር ታጋዮች ጋር ስምምነት አድርጎ ነበር። ከሜቴክ ጋር ስምምነቱን የፈጸሙት በአቶ ጉኡሽ ካህሳይ ባለቤትነት የሚመራው ጀዲጂ ኮንስትራክሽን ሃላፊነቱ ...
Read More »በሊቢያ ትሪፖሊ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት 12 ሰዎች ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 24/2010) በሊቢያ ትሪፖሊ የምርጫ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት ላይ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት 12 ሰዎች ተገደሉ። ጥቃቱን ፈጽመዋል ከተባሉት አሸባሪዎች አንዱ ራሱ ላይ የተጠመደውን ቦምብ በማፈንዳት እራሱን ማጥፋቱ ታውቋል። አብረውት የነበሩት ሌሎች ግብረ አበሮቹም ሕንጻው ላይ ተኩስ በመክፈትና ሕንጻውን በማቃጠል ተባብረውታል ብሏል ዘገባው። ለ42 አመታት በሙሀመድ ጋዳፊ አመራር ስር የነበረችው ሊቢያ የጋዳፊን መውደቅ ተከትሎ ከ2011 ጀምሮ በቀውስ ውስጥ ትገኛለች። ...
Read More »ኢሰማኮ ሀገር አቀፍ የስራ ማቆም አድማ እጠራለሁ አለ
(ኢሳት ዲሲ –ሚያዚያ 24/2010) የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን/ኢሰማኮ/ በአዲሱ የሰራተኛ አዋጅ ላይ ያለውን ቀሬታ በማንሳት ሀገር አቀፍ የስራ ማቆም አድማ እጠራለሁ ሲል አስጠነቀቀ ። አዲስ የተዘጋጀው የሰራተኛ ረቂቅ አዋጅ ቀድሞ የነበረውን የሰራተኞች መብቶችን የሚያስቀረና ጥቅማጥ ቅማቸውን የሚሳጣ ነውም ብሏል። የሰራተኛው የደሞዝ ወለል በአዲሱ የሰራተኛና አሰሪ አዋጅ ላይ ይካተት የሚለው ጥያቄም እስካሁን ምላሽ አለማግኘቱ ሌላ ቅሬታ የፈጠረ ጉዳይ ነው ተብሏል። በኢትዮጵያ ...
Read More »ሕወሃት ኤርትራ ጥቃት ልትፈጽምብን ትችላለች የሚል ስጋት ውስጥ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 24/2010) የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ መሪዎች ኤርትራ ጥቃት ልትፈጽምብን ትችላለች የሚል ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ምንጮች ገለጹ። ጦርነቱ ቢነሳ በጦርነቱ አፍራሽ ሚና ሊኖራቸው ይችላሉ የተባሉ በርካታ መኮንኖች እየተመነጠሩ በመታሰር ላይ መሆናቸው ታውቋል። ጥቂት ወታደሮችና የበታች ሹሞችም በተመሳሳይ መታሰራቸው ታውቋል። የሰራዊቱን መኮንኖች እየመነጠሩ የማሰሩ ርምጃ የተከተለው በኦሮሚያና በአማራ ክልል በተለይም በአማራ ክልል ከወልቃይት ጋር በተያያዘ ያልተጠበቀ ተቃውሞና አመጽ ሊከተል ይችላል ...
Read More »በጉጂ ዞን የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 24/2010) የሜድሮክ የወርቅ ማዕድን ኩባንያ ኮንትራት መራዘሙ ያስቆጣቸው የጉጂ ዞን ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን ለሶስተኛ ቀን መቀጠላቸው ታወቀ ። በሃረቃሎ ዘጠኝ የካቢኔ አባላት በኮማንድ ፖስቱ መታሰራቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ዛሬ በበርካታ የዞኑ አካባቢዎች ተቃውሞው ተጠናክሮ በመካሄድ ላይ መሆኑም ተመልክቷል። በተቃውሞ የሀገር ሽማግሌዎችና አባገዳዎች ሳይቀር መሳተፋቸው እየተነገረ ነው። በአንዳንድ አካባቢዎችም የአገዛዙ ታጣቂዎች ህዝቡ ላይ ጉዳት ማድረሳቸው ታውቋል። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ማንኛውም ...
Read More »ከቤንሻንጉል ጉምዝ የተፈናቀሉ የአማራ ክልል ተወላጆች እየታፈኑ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 24/2010)ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ክልል ተወላጆች በደህንነቶች በመታፈን ላይ መሆናቸው ታወቀ። ከ500 በላይ የሚሆኑት ተፈናቃዮች ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሆኑም የኢሳት ወኪል ያነጋገራቸው ገልጸዋል። በተለይ ከተፈናቃዮች መካከል ወንዶች እየተለዩ በመታፈን ላይ መሆናቸው ታውቋል። ከህዝብ እንዳይገናኙ በህወሃት ደህንነቶችና በኮማንድ ፖስቱ ወታደሮች ወከባ እየተደረገባቸው ነው ተብሏል። ህወሀት የሰገሰጋቸውና በተፈናቃይ ስም የተደባለቁ የደህንነት ሰራተኞች ወደ መጣንበት እንመለስ የሚል ቅስቀሳ የጀመሩ በመሆኑ ...
Read More »በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ ግጭት ተቀሰቀሰ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 24/2010)በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ ግጭት መቀስቀሱ ተሰማ። የፌደራል ፖሊስ ወደ ግቢ በመግባት በርካታ ተማሪዎችን በመደብደብ ጉዳት ማደረሱንም ለማወቅ ተችሏል። የግለሰቦች ጸብ መነሻ እንደሆነ ቢገለጽም ግጭቱ ወደ እርስ በእርስ ተቀይሮ የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዲቆም ማድረጉን ነው የኢሳት ምንጮች የገለጹት። ባለፈው ሳምንት ከግቢው እንዲወጣ በተማሪዎች ተቃውሞ የደረሰበት የፌደራል ፖሊስ የዛሬውን ግጭት ተከትሎ ግቢውን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩም ተገልጿል። ተማሪዎች ከግቢያቸው እንዳይወጡ ተደርገዋል። የታሰሩም ...
Read More »በቤንሻንጉል ጉሙዝ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች “ልጆቻቸውን ይዘው በረሃ ለበረሃ መንከራተቱ እንዲያበቃላቸው” ጠየቁ
በቤንሻንጉል ጉሙዝ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች “ልጆቻቸውን ይዘው በረሃ ለበረሃ መንከራተቱ እንዲያበቃላቸው” ጠየቁ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 24 ቀን 2010 ዓ/ም) ከተለያዩ የአማራ ክልል የገጠር አካባቢዎች ተጉዘው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በእርሻ እና በሌሎችም ስራዎች ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የአማራ ተወላጆች፣ በክልሉ ውስጥ የሚደርስባቸው በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ አስከፊ እየሆነ መምጣቱን ኢሳት ያነጋገራቸው የክልሉ ተወላጆች ገልጸዋል። “በአንዳንድ ወረዳዎች ብቻ በያመቱ ከ30-50 የሚጠጉ የአማራ ተወላጆች ...
Read More »