ወጣት ቱፋ መልካ ጥፋተኛ ተባለ

ወጣት ቱፋ መልካ ጥፋተኛ ተባለ (ኢሳት ዜና ግንቦት 01 ቀን 2010 ዓ/ም) በ2009 ዓም ተካሂዶ በነበረውና በርካታ ዜጎች ባለቁበት የኢሬቻ በአል ላይ ህዝብን ለአመጽ የሚያነሳሳ ንግግር አድርገሃል ተብሎ የሽብር ክስ የቀረበበት ቱፋ መልካ ሚያዚያ 30 ቀን 2010 ዓም የዋለው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ጥፋተኛ ብሎታል። ፍርድ ቤቱ ለ55 ሰዎች ህይወት መጥፋት ተጠያቂ ያደረገው ቱፋ፣ ሟቾቹ በጥይት ተደብድበው ...

Read More »

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈታ በማህበራዊ ሚዲያ የተካሄደው ዘመቻ የተሳካ እንደነበር ወ/ት እየሩሳሌም ተስፋው ገለጸች

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈታ በማህበራዊ ሚዲያ የተካሄደው ዘመቻ የተሳካ እንደነበር ወ/ት እየሩሳሌም ተስፋው ገለጸች (ኢሳት ዜና ግንቦት 01 ቀን 2010 ዓ/ም) በቅርቡ በሽብር ወንጀል ተከሳ የፍርድ ጊዜዋን ጨርሳ ከእስር የተፈታችው ወጣት እየሩሳሌም ተስፋው ለኢሳት እንደገለጸችው አቶ አንዳርጋቸው ከእስር እንዲፈታ ሰደረግ የነበረው የ3 ቀናት ዘመቻ ዛሬ ረቡዕ የሚጠናቀቅ ሲሆን፣ እስካሁን በነበረው ዘመቻ በአብዛኛው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች ዘመቻውን ተቀላቅለው ድምጻቸውን በማሰማታቸው ...

Read More »

በአዶላ የአጋዚ ወታደሮች እርምጃ መውሰድ ጀመሩ

በአዶላ የአጋዚ ወታደሮች እርምጃ መውሰድ ጀመሩ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 30 ቀን 2010 ዓ/ም) ለሳምንት የቀጠለውን የምስራቅ ጉጂ ዞን ተቃውሞ ተከትሎ የአጋዚ ወታደሮች በህዝቡ ላይ በመተኮስ እርምጃ የወሰዱ ሲሆን፣ እስካሁን ሁለት ህጻናትን ጨምሮ 4 ሰዎች ተገድለዋል፣ በርካቶችም ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች የኦህአዴድ ባለስልጣናት አካባቢውን ለቀው መውጣታቸውንና በአጋዚ ወታደሮችና በህዝቡ መካከል የሚካሄደው ፍልሚያ መቀጠሉን ተናግረዋል። ህዝቡ በድንጋይ ራሱን ለመከላከል ሲሞክር፣ አጋዚዎች ...

Read More »

በሶማሊ ክልል ጠንካራ ተቃውሞ ሲካሄድ ዋለ

በሶማሊ ክልል ጠንካራ ተቃውሞ ሲካሄድ ዋለ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 30 ቀን 2010 ዓ/ም) የአብዲ ኢሌን ፍጹማዊ አገዛዝ በመቃወም በሶማሊ ክልል የሚካሄደው ተቃውሞ አድማሱን እያሰፋ በመምጣት ላይ ነው። በዛሬው እለት ከዚህ በፊት ተቃውሞ ባልተካሄደባቸው ቦታዎች ጠንካራ ተቃውሞ ሲካሄድ ውሎአል። የአብዲ ኢሌ ተጣቂዎች ተቃውሞአቸውን በሚገልጹ ዜጎች ላይ በወሰዱት እርምጃም ሰዎች ተገድለዋል። ቶጎ ወጀሌንና ጂግጂጋን ከመሃል አገር ጋር የሚያገናኘው መንገድም ተዘግቷል። በጅግጅጋ ዞን ...

Read More »

በቂሊንጦ ቃጠሎ ሰበብ ከተከሰሱት የህሊና እስረኞች መካከል ብዙዎቹ በመደበኛ ወንጀል እንዲካላከሉ ተበየነ

በቂሊንጦ ቃጠሎ ሰበብ ከተከሰሱት የህሊና እስረኞች መካከል ብዙዎቹ በመደበኛ ወንጀል እንዲካላከሉ ተበየነ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 30 ቀን 2010 ዓ/ም) የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት በቂሊንጦ ቃጠሎ ሰበብ ታስረው አሁንም ድረስ ጉዳያቸውን በፍርድ እየታየ ከሚገኙት መካከል መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጠኝ፣ ዶክተር ፍቅሩ ማሩን፣ አግባው ሰጠኝን፣ ወልዴ ሞቱማን፣ ሚስባህ ከድርን፣ ፍቅረማርያም አስማማውን፣ ደረጀ መርጋንና፣ ከበደ ጨመዳን፣ ጨምሮ 28 ...

Read More »

የታገዱት የአየር ሃይል አብራሪዎች መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠየቁ

የታገዱት የአየር ሃይል አብራሪዎች መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠየቁ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 30 ቀን 2010 ዓ/ም) በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተካሄዱትን ተቃውሞዎች ተከትሎ ከ2 አመት ላላነሱ ጊዜ ከስራ የታገዱ የአማራ እና የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ የሆኑ የአየር ሃይል አብራሪዎች ለምን እንደታገዱ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠየቁ። በምስራቅ አየር ምድብና በማእከላዊ አየር ምድብ ያገለገሉ የነበሩት አብራሪዎች “ ጥፋታችን ምንድነው? ስራ እንድናቆም የታዘዝነውስ ለምንድነው?” የሚል ጥያቄ አቅርበዋል። የስርዓቱ ...

Read More »

ሳኡዲ አረቢያ-ከሶማሊያ የቀንድ ከብት ወደ ሀገሯ እንዳይገባ የጣለችውን እግድ ልታነሳ መሆኗን አስታወቀች።

ሳኡዲ አረቢያ-ከሶማሊያ የቀንድ ከብት ወደ ሀገሯ እንዳይገባ የጣለችውን እግድ ልታነሳ መሆኗን አስታወቀች። (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 30 ቀን 2010 ዓ/ም) የመካከለኛዋ ምሥራቅ ሀገር “ከብቶቹ በሽታ ተገኝቶባቸዋል” በሚል ምክንያት ከሶማሊያ የቀንድ ከብት ማስገባት ያቆመችው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2016 ነው። ሳኡዲ አረቢያ የበርበራ፣ የቦሳሶ፣ የሞቃዲሾ እና የሌሎች ከተሞች ወደቦችን በመጠቀም 80 በመቶ የሚሆኑትን የሶማሊያ ቀንድ ከብቶች ወደ ሀገሯ ስታስገባ ወይም ኢምፖርት ስታደርግ ቆይታለች። ...

Read More »

ሞዛምቢክ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪውን በክብር እንዲቀበሩ አዘዘች

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 30/2010)ሞዛምቢክ በሞት ለተለዩት የተቃዋሚ ፓርቲው ብሄራዊ የቀብር ስነስርአት አወጀች። የአማጺው ሃናም መሪም የነበሩት አፎንሶ ደሃለካማ በ65 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ነበር። የሞዛምቢክ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለእኚህ የቀድሞ የአማጺ መሪ እና በአሁኑ ወቅት ስልጣን ላይ ያለው ቡድን ዋና ተቀናቃኝ ፓርቲ መሪ ለሆኑት አፎንሶ ዳህላካም ብሔራዊ የቀብር ስነስርአት እንዲካሄድላቸውም ወስኗል። እኚህ የቀድሞ አማጺ መሪ አፎንሶ ዳህላካማ ...

Read More »

ዶክተር አብይ አህመድ በመጪው ነሃሴ አሜሪካን ይጎበኛሉ ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 30/2010)  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በመጪው ነሃሴ አሜሪካን እንደሚጎበኙ ከዲፕሎማቲክ ምንጮች የተገኘ መረጃ አመለከተ። ይህ በእንዲህ እንዳለ አምባሳደር ቲቦር ናዢ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር እንዲሆኑ  መታጨታቸው ተነግሯል። በኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት ቲቦር ናዥ የአፍሪካ ጉዳዮች ሃላፊ እንዲሆኑ በአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት  ወይንም ሴኔት በቅርቡ ይጸድቅላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። አዲሱ የአፍሪካ ጉዳዮች ሃላፊ ከተሾሙ በኋላ ...

Read More »

ተከሳሾች በችሎት ውስጥ ተቃውሞ አሰሙ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 30/2010) በቂሊንጦ ቃጠሎ ሰበብ ጥፋተኛ ተብለው ተከላከሉ የተባሉ ተከሳሾች በችሎት ውስጥ ተቃውሞ አሰሙ። ተከሳሾቹ የፍርድቤቱን ውሳኔ አልቀበልም በማለታቸው ችሎቱ ተረብሾ እንደነበር ያገኘነው መረጃ ያመልክታል። በችሎቱ የነበሩ ታዳሚዎችን ፌደራል ፖሊስ ሲበትን እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል። በቂሊንጦ ቃጠሎ ተከሰው ፍርድ ቤት ሲመላለሱ የነበሩት 38ቱ እስረኞች በችሎቱ ጥፋተኛ ሲባሉ ውሳኔውን በመቃወማቸው ረብሻ ተፈጥሮ ነበር። በቂሊንጦ ቃጠሎ ወቅት በተገደሉት ሰዎች ምክንያት ከተከሰሱትና እንዲከላከሉ ...

Read More »