የአፋር ክልል ገዥ ፓርቲ አብዴፓ አዲሱን የአቶ አብይ አህመድን አስተዳደር እንዳይቀበል በህወኃት በኩል አፍራሽ ተግባራት እየተፈጸሙ ነው ሲሉ በአውሮፓ የአፋር ማህበረሰብ ተወካይ ገለጹ። (ኢሳት ዜና ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ/ም) ተወካዩ አቶ ገአስ አህመድ ዛሬ በተለይ ለኢሳት እንደገለጹት ላለፉት 27 ዓመታት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቅሙ ክፉኛ የደቀቀው የአፋር ህዝብ እውነተኛ ለውጥ እየጠየቀ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ገዥው የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ -ከህወኃት ...
Read More »የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጋትሎክ ቱት ውጭ አገር ሄደው እንዲታከሙ የክልሉ ካቢኔ ከክልሉ መጠባበቂያ በጀት 1 ሚሊዮን ብር ወጪ እንዲሆን ወሰነ።
የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጋትሎክ ቱት ውጭ አገር ሄደው እንዲታከሙ የክልሉ ካቢኔ ከክልሉ መጠባበቂያ በጀት 1 ሚሊዮን ብር ወጪ እንዲሆን ወሰነ። (ኢሳት ዜና ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ/ም) የክልሉ ምክር ቤት ለክልሉ ፋይናንስ ክፍል በላከው ደብዳቤ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ ዶ/ር ጋትሎክ ቱት ህክምናቸውን በጦር ሃይሎች ሆስፒታል ሲከታተሉ ቢቆዩም፣ ለውጥ ሊታይ ስላልቻለ ወደ ውጭ አገር ሄደው የተሻለ ህክምና እንዲያገኙ 1 ሚሊዮን ...
Read More »ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በ35ኛው የሰሜን አሜሪካ ስፖርት ፌስቲቫል ላይ እንዲገኙ የቀረበው ጥያቄ በማህበሩ በኩል ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱ ተገለጸ።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በ35ኛው የሰሜን አሜሪካ ስፖርት ፌስቲቫል ላይ እንዲገኙ የቀረበው ጥያቄ በማህበሩ በኩል ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱ ተገለጸ። (ኢሳት ዜና ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ/ም) ዶክተር አብይ አህመድ በዳላሱ ዝግጅት ላይ እንዲገኙ ጥያቄ የቀረበው በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በቁጥር ዋሸ 09-620-2010 በጻፈው ደብዳቤ አማካይነት ነው።የማህበሩ አመራሮች ይህን ጥያቄ ተከትሎ ባሰባሰቡት ድምጽ 65 በመቶ ያህሉ ድምጽ ሰጭ እንዲገኙ ፍላጎቱን የገለጸ ቢሆንም፣ ...
Read More »ዶክተር አብይ አሕመድ በኢትዮጵያውያን ፌስቲቫል ላይ እንዲገኙ የቀረበው ጥያቄ ውድቅ ሆነ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 23/2010) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ በኢትዮጵያውያን ፌስቲቫል ላይ እንዲገኙ የቀረበውን ጥያቄ አለመቀበሉን የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ። 31 አባላት ያሉት የፌዴሬሽኑ ቦርድ ጥያቄውን ያልተቀበለው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ቢጋበዙ ቀሪው ጊዜ አጭር በመሆኑ ሊፈጠር የሚችለውን የሰው ብዛት መጨናነቅና የቦታ ጥበት ምክንያት በማድረግ ነው ብሏል። እናም የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጥያቄ ለሚቀጥለው አመት ቢቀርብ ጉዳዩን እንደገና እንደሚያጤነው ...
Read More »በዚምባቡዌ በመጪው ሃምሌ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሊካሄድ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 22/2010) ዚምባቡዌ በመጪው ሃምሌ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንደምታካሂድ አስታወቀች። የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ እንዳሉት በሃገሪቱ የሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊና የፓርላማ ምርጫ ግልጽ በሆነ መንገድ እንዲካሄድ አለም አቀ ታዛቢ ቡድኖችምእንዲገኙ ይደረጋል ብለዋል። እንደ አውሮፓውያኑ ከ2002 በኋላም ለመጀመሪያ ጊዜ በጋራ የበለጸጉ ሃገራት ታዛቢ ቡድን እንዲገኝ ግብዣ እንደሚያደርጉም ምናንጋግዋ አስታውቀዋል። በመጪው ሃምሌ ይካሄዳል የተባለው ይህ ምርጫ በሃገሪቱ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ የሚባሉት ሙጋቤና ...
Read More »የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቤተሰቦች ለኢትዮጵያ ህዝብ ምስጋና አቀረቡ
የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቤተሰቦች ለኢትዮጵያ ህዝብ ምስጋና አቀረቡ (ኢሳት ዜና ግንቦት 22 ቀን 2010 ዓ/ም) የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር መፈታታቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያን ላዳረጉት ድጋፍ ቤተሰቦቻቸው ምስጋናቸውን ገልጸዋል። የአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት ወ/ሮ የምስራች ሃይለማርያም እንዲሁም ታላቅ እህቱ ወ/ሮ ብዙአየሁ ጽጌ፣ ደስታቸውን በመግለጽ፣ ላለፉት 4 አመታት ህዝቡ ሲያደርገው ለነበረው ትግል ደስታቸውን ገልጸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ አርበኞች ግንቦት7 በአቶ ...
Read More »ከቤንሻንጉል ጉሙዝና ኦሮምያ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች የመፍትሄ ያለህ እያሉ ነው
ከቤንሻንጉል ጉሙዝና ኦሮምያ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች የመፍትሄ ያለህ እያሉ ነው (ኢሳት ዜና ግንቦት 22 ቀን 2010 ዓ/ም) በመቶዎች የሚቆጠሩ ከቤንሻንጉል ጉሙዝና ከኦሮምያ ክልል ቡኖ በደሌ ወረዳ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች በአሁኑ ሰዓት በባህርዳር ከተማ በጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እንዲሁም በተለምዶ አባይ ማዶ እየተባለ በሚጠራው በምግብ ዋስትና ግቢ ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ። በምግብ ዋስትና ግቢ ውስጥ ተጠልለው የሚገኙት ተፈናቃዮች፣ ከሳምንታት በፊት ወደ ትውልድ ቀያቸው ...
Read More »በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ ነው
በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ ነው (ኢሳት ዜና ግንቦት 22 ቀን 2010 ዓ/ም) በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማፈን ነባር የብአዴን እና የህወሃት አባላት በሙሉ ሃይላቸው እየተንቀሳቀሱ ነው። ለውጥ የሚፈልጉ የኢህአዴግ አባላት ቁጥራቸው እየጨመረ ቢሆንም፣ ነባር የኢህአዴግ አመራሮች ከአዲሶቹ የድርጅቱ አመራሮች ጋር ተስማምተው ለመጓዝ ተቸግረዋል። ህወሃት በብአዴን ውስጥ ያለውን ክፍፍል ለራሱ ጥቅም ለማዋል እየተንቀሳቀ ሲሆን በተለይ የለውጡን እንቅስቃሴ አይደግፉም ...
Read More »የፌደራል ፖሊስ ሶስት ከፍተኛ ሃላፊዎች ተነሱ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 22/2010) የፌደራል ፖሊስ ሶስት ከፍተኛ ሃላፊዎች ከስልጣን ተነሱ። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ወደ ፌደራል ፖሊስ ሲዛወሩ፣ የቤተመንግስት አስተዳደር ሃላፊም ተሽረው ፣በምትካቸው አዲስ ሃላፊ ተሹሟል። ከሁለት ዓመት በፊት ከብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ሃላፊነት የተባረሩት ኢሳያስ ወልደጊዮርጊስ የአንድ ኤጀንሲ ሃላፊ ሆነው መሾማቸውም ታውቋል። በአዲስ አበባ የሚታተመው ሳምንታዊ የእንግሊዝኛ ጋዜጣ አዲስ ፎርቹን እንደዘገበው በፌደራል ፖሊስ ውስጥ ለረጅም አመታት የወንጀል መከላከል ሃላፊ ...
Read More »በመላው ዓለም ኢትዮጵያውያን ደስታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 22/2010) በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መፈታት ደስታቸውን በመግለጽ ላይ መሆናቸው ታወቀ። በአውሮፓ፣ በአውስትራሊያ፣ በአሜሪካ፣ በካናዳ፣ በደቡብ አፍሪካ፣ በእስራኤልና በሌሎች የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ስነስርዓቶች ደስታቸውን እየገለጹ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በሌላ በኩል በጓዳችን መፈታት ደስ ብሎናል፤ የሚጠብቀን ብዙ መሆኑን እናውቃለን ሲል አርበኞች ግንቦት ሰባት መግለጫ አውጥቷል። የአቃቤ ህግ መግለጫ ከተሰጠበት ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ የኢትዮጵያውያን ...
Read More »