ወደወህኒ የተጋዙ አራት አብራሪዎች አሁንም ከእስር አልተለቀቁም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 24/ 2010) የኢትዮጵያ አየር ሃይል አብራሪ የነበሩና ሥርዓቱን በመቃወማቸው ወደወህኒ የተጋዙ አራት አብራሪዎች አሁንም ከእስር እንዳልተለቀቁ ታወቀ። የፖለቲካ እስረኞች እንዲሁም በሌብነት ወንጀል ተጠርጥረው የነበሩና የተፈረደባቸው ጭምር ከእስር በተለቀቁበት በአሁኑ ሰዓት አራቱ የበረራ ባለሙያዎች በዝዋይና በቃሊቲ ማረሚያ ቤቶች ይገኛሉ። የመቶ አለቃ በሃይሉ ገብሬ በ1997 ምርጫ ማግስት በአዲስ አበባ ከተማና በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተካሄደውን ግድያ በመቃወም ሔሊኮፕተር ...

Read More »

ኤፈርት ከህግ ውጭ ከወጭ ሃገር ባንኮች ብድር ሲወስድ መቆየቱ ታወቀ

 (ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 24/2010) የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ንብረት የሆነው ኤፈርት ከህግ ውጭ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋስትና ከወጭ ሃገር ባንኮች ብድር ሲወስድ መቆየቱ ታወቀ። ይህንን ሁኔታ በማመቻቸት ለንግድ ባንክ ሃላፊዎች ትዕዛዝ ሲሰጡ የቆዩት የብሄራዊ ባንክ ገዢው አቶ ተክለወልድ አጥናፉ መሆናቸውም ተመልክቷል። ይኽው ህገ ወጥ ድርጊት በመቀጠሉ የኤፈርት ንብረት የሆነው አልመዳ ጨርቃጨርቅ አንድ መቶ ሚሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋስትና መውሰዱ ታውቋል። ...

Read More »

የሶማሌ ልዩ ሐይል እንዲፈርስ አምነስቲ ጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 24/ 2010)  በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ የሶማሌ ልዩ ሐይልን እንዲያፈርስ ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ። ተቋሙ ለጸረ ሽብር በሚል ሰበብ በሶማሌ የተቋቋመው ልዩ ሀይል ፈርሶ በህጋዊ የፖሊስ አባላት እንዲተካም ጠይቋል ። ልዩ ሃይሉ በሶማሌ መጠነ ሰፊ ጅምላ ግድያና ሰቆቃ በህዝቡ ላይ እየፈጸመ መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል። የሶማሌ ልዩ ሃይል የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር/ኦብነግን/ለመደምሰስ በሚል የተቋቋመ ...

Read More »

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በእንግሊዝ ለንደን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 24/ 2010) በቅርቡ ከእስር የተልቀቁት አቶ አንዳርጋጨው ጽጌ እንግሊዝ ለንደን ሲገቡ በአውሮፓና አካባቢው በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለአራት ዓመታት በእስር ምክንያት ከተለያዩቸው ባለቤታቸውና ልጆቻቸው ጋር በሰላም መገናኘታቸውም ታውቋል። ኢትጵያውያኑ ላደረጉላቸው አቀባበልም ሆነ እርሳቸው ከእስር እንዲፈቱ ላደረጉት ጥረት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል። ፍቺውን ለማስተጓጎል የተደረገው ሙከራ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መክሸፉንም አቶ አንዳርጋቸው ...

Read More »

ከአለም ሕጻናት ከግማሽ የሚበልጡት በጦርነትና በድህነት እየተሰቃዩ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 23/2010) ከአለማችን ሕጻናት ከግማሽ የሚበልጡት በጦርነትና በድህነት በመሰቃየት ላይ መሆናቸውን ሴቭ ዘ ችልድረን የተባለው አለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት ገለጸ። መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው ሴቭ ዘ ችልድረን ትላንት ይፋ ባደረገው ሪፖርት በትንሹ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን የአለማችን ሕጻናት ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል። 1 ቢሊየን ያህል ሕጻናት የሚኖሩት ድህነት በተስፋፋባቸው ሀገራት ነው። 240 ሚሊየን ሕጻናት ደግሞ ግጭት በቀጠለባቸው ሀገራት የሚኖሩ ...

Read More »

የሀና ማርያም ነዋሪዎች በፖሊስ ተደበደቡ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 23/2010) በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ ሀና ማርያም በተባለ አካባቢ ቤታቸው የፈረሰባቸው ከ2ሺህ በላይ አባወራዎች በቤተመንግስት አቤቱታ ለማቅረብ ሄደው በፖሊስ መደብደባቸው ተገለጸ። ትላንት ማምሻውን ወደ ቤተመንግስት ያመሩት የሃና ማርያም ተፈናቃዮች ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አቤቱታ ለማቅረብ ያደረጉት እንቅስቃሴ በወከባና ድብደባ ተበትኗል። አቤት የምንልበት ቦታ አጣን በሚል በምሬት የሚገልጹት ተፈናቃዮቹ የኢትዮጵያ ህዝብ ይድረስልንም ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። የሃና ማርያም አካባቢ መኖርያ ...

Read More »

በርካታ የሃና ማርያም ተፈናቃዮች ወደ ቤተመንግስት በመሄድ ተቃውሞ አሰሙ

በርካታ የሃና ማርያም ተፈናቃዮች ወደ ቤተመንግስት በመሄድ ተቃውሞ አሰሙ (ኢሳት ዜና ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ/ም) ከ3 ሺ የማያንሱ ቤታቸው የፈረሰባቸውና በከፍተኛ ችግር ላይ የሚገኙት ዜጎች ወደ ቤተ መንግስት አምርተው ጉዳያቸውን ለጠ/ሚኒስትሩ ለማቅረብ ቢፈልጉም አልተሳካላቸውም። ይህን ተከትሎ በቀጥታ ወደ አሜሪካ ኢምባሲ ሲያመሩ የፌደራል ፖሊሶች መንገድ ላይ በመጠባባቅ ሰልፈኞችን አግተው ውለዋል። ፖሊሶቹ በሰልፈኞች ላይ ያደረሱት ጉዳት የለም። ተፈናቃዮቹ ጥያቄያቸውን የሚሰማ አካል ...

Read More »

የብሔራዊ ባንክ ገዢው ከስልጣናቸው እንዲነሱ ተወሰነ

(ኢሳት ዲሲ– ግንቦት 23/2010)   የብሔራዊ ባንክ ገዢው አቶ  ተክለወልድ አጥናፉ  ከስልጣናቸው እንዲነሱ መወሰኑን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። ምክትል ገዢው ዶክተር ዮሃንስ አያሌው  በይፋ ከስልጣናቸው መነሳታቸው ታውቋል። በአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ ውስጥ የአፍሪካ ሃላፊ  አቶ አበበ አዕምሮ ሥላሴ ለብሔራዊ ባንክ ገዢነት  መጠየቃቸውም ተሰምቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለም የሃገሪቱ መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሪ ለሁለት ሳምንት ብቻ  የሚበቃ  መሆኑም ተመልክቷል። የብሄራዊ ባንክ ገዢዎች ...

Read More »

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በጽሕፈት ቤታቸው ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጋር በመወያዬታቸው በርካታ ኢትዮጵያውያን ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። አቶ አንዳርጋቸው ነገ ጧት ለንደን ይገባሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በጽሕፈት ቤታቸው ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጋር በመወያዬታቸው በርካታ ኢትዮጵያውያን ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። አቶ አንዳርጋቸው ነገ ጧት ለንደን ይገባሉ። (ኢሳት ዜና ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ/ም) የግንቦት 7 ዋና ጸሀፊና የሞት ፍርድ ተላልፎባቸው ባለፉት አራት አመታት በእስር የቆዩት አቶ አንዳርጋቸው ትናንት ከቀትር በኋላ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ለሁለት ሰዓታት የዘለቀ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ “መሰረታዊ ባሏቸው” ጉዳዮች ዙሪያ ስለደረጓቸው ...

Read More »

የአብዲ ኢሌ የደህንነት አባላት በዱልሚዲድ አመራር ላይ ያደረጉት የአፈና እርምጃ ከሸፈ

የአብዲ ኢሌ የደህንነት አባላት በዱልሚዲድ አመራር ላይ ያደረጉት የአፈና እርምጃ ከሸፈ (ኢሳት ዜና ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ/ም) ትናንት ምሽት የአብዲ ኢሌን ፍጹማዊ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ በመቃወም ዱል ሚዲድ እየተባለ በሚጠራው በኢትዮ-ሶማሊ ተወላጆች የተቋቋመውን ድርጅት ከሚመሩት ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑትን አቶ ካድር አዳንን ከአዲስ አበባ ወደ ጅግጅጋ አፍኖ ለመውሰድ የተደረገው ሙከራ በፌደራል የደህንነት መስሪያ ቤትና በአሜሪካ ኢምባሲ አማካኝነት ሊከሽፍ ችሎአል። ...

Read More »