አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት

(ኢሳት ዲሲ– ሐምሌ 17/2010) አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ በኢትዮጵያና በኤርትራ መሀል ለተደረሰው የሰላም ስምምነት ላበረከተው አስተዋጾ የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት። በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የኤርትራውያን ፌስቲቫል ላይ ተገኝተው የእውቅና ሽልማቱን የተረከቡት የንቅናቄው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ናቸው። በፌስቲቫሉ ላይ የሁለቱ ሀገራትንና የአፍሪካውን ቀንድ ሰላም የተመለከተ ጉባዔ ተካሄዷል። በምሁራን ጥናታዊ ጽሁፎችም ቀርበዋል።

Read More »

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን ለውጥ እንደግፋለን አሉ

(ኢሳት ዲሲ– ሐምሌ 17/2010) በዋሽንግተን ዲሲ ሜሪላንድና ቨርጂኒያ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን የለውጥ እንቅስቃሴ እንደሚደግፉ ገለጹ። የወንጌል አማኞቹ ኢትዮጵያ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማሕበራዊ መስኮች በተወጠረችባቸው ጊዚያት ሁሉ በጸሎትና በምልጃ  ልመና ሲያደርጉ እንደነበረ ጠቅሰው አሁንም ለተጀመረው የሰላምና የእርቅ ጉዞ የሚችሉትን ሁሉ ለማድረግ ቃል በመግባት መግለጫ አውጥተዋል። እሁድ ዕለት በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ጉባዔ ላይ በኢትዮጵያና በኤርትራ መሀል የተደረሰው የሰላም ...

Read More »

በፍኖተሰላም ህዝቡ በህወሀት ላይ ከፍተኛ ቁጣ አሰማ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 17/2010) በምዕራብ ጎጃም ፍኖተሰላም በተካሄደ ስብሰባ ህዝቡ በህወሀት ላይ ከፍተኛ ቁጣ ማሰማቱ ተገለጸ። ላለፉት 27 ዓመታት በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸምው ግፍና መከራ በህዝቡ በዝርዝር ተነስቶ የህወሀት አገዛዝ ላይ ውግዘት መቅረቡን ያገኘነው መረጃ ያምለክታል። በህዝብ ላይ ይሄ ሁሉ መከራ ሲደርስ ብአዴን የት ነበረ በሚል በአመራሮቹ ላይ ተቃውሞ መሰማቱን ለማወቅ ተችሏል። ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስተዳደር ድጋፍ ለማሳየትና ከለውጡ ለመጓዝ ...

Read More »

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት አምጽ ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዲሲ– ሐምሌ 17/2010) በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከትላንት ሌሊት ጀምሮ አምጽ መቀስቀሱ ተሰማ። በጥይትና በአስለቃሽ ጢስ በርካታ እስረኞች ተጎድተዋል። በዞን አራት የሚገኙ እስረኞች እንፈታ የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውን ተከትሎ የተጀመረው አመጽ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከፍተኛ ውጥረት ማንገሱን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በአከባቢው መንገዶች መዘጋታቸው ተገልጿል። እስረኞች የድረሱልን ጩሀት እያሰሙ መሆኑም ታውቋል።በተመሳሳይ በደብረማርቆስ ማረሚያ ቤት  በተቀሰቀሰ አመጽ ቤቶች መቃጠላቸውን ለማወቅ ተችሏል። በአርባምንጭ እስር ...

Read More »

በወለጋ ደምቢዶሎ አንዲት ነፍሰጡር ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ– ሐምሌ 17/2010) በወለጋ ደምቢዶሎ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት አንዲት ነፍሰጡር ተገደሉ። ቁጥራቸው ለጊዜው በውል ያልታወቁ ሰዎችም ህይወታቸው ማለፉ ታውቋል። በባሌ ጎባ የተከሰተው ግጭት ዛሬም መቀጠሉን የገልጹት ነዋሪዎች መንግስት በአስቸኳይ ይድረስልን ሲሉ ጥሪ አድርገዋል። በባቢሌ በጭናክሰን ውጥረቱ መባባሱን ያገነኘው መረጃ ያመልክታል። በተያያዘ ዜናም በደሴ ባልታወቁ ሃይሎች በተፈጸመ የስለት መሳሪያ ጥቃት በርካታ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ታውቋል።

Read More »

ሁለቱ ሲኖዶሶች ወደ አንድ ሲኖዶስ መጡ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 17/2010) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን አባቶች መካከል የተጀመረው የእርቅ ጉባኤ ሁለቱ ሲኖዶሶች ወደ አንድ ሲኖዶስ እንዲመጡ ከስምምነት ላይ መደረሱ ተገለጸ። የእርቅ ጉባኤው ከመካሄዱ በፊት አስቀድሞ የሁለቱም አባቶች የተገናኙበት የጋራ የጸሎት ስነስርአት ተካሂዶ አንደነበር ታውቋል። ከሐገር ቤት የመጡት አባቶች በውጪ ሲኖዶስ በሚመሩ አብያተ ክርስቲያናት የጸሎት ስነስርአት ላይ ሲገኙ የውጪ ሲኖዶሱ አባላት ደግሞ በሐገር ቤቱ ሲኖዶስ በሚመሩ አብያተ ክርስቲያናት ጸሎት ...

Read More »

በካናዳ አንድ ግለሰብ በከፈተው ተኩስ አንድ ሴትን ሲገል 13 ሰዎች ቆሰሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 16/2010) በካናዳ ሕዝብ በሚበዛበት አካባቢ አንድ ግለሰብ በከፈተው ተኩስ አንድ ሴትን ሲገል 13 ማቁሰሉ ተገለጸ። የግለሰቡ ጥቃት ያነጣጠረው በሁለት ምግብ ቤቶች ላይ መሆኑ ደግሞ አነጋጋሪ አድርጎታል። ግለሰቡ በከፈተው ተኩስ ከቆሰሉት መካከል ሕጻናት እንደሚገኙበትም የተገለጸ ሲሆን ሕይወቷ አስጊ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሴትም መኖሯ ታውቋል። የ29 አመቱን ተጠርጣሪ ሞቶ መገኘቱንና ከዛ በፊት ግን ከፖሊስ ጋር የተኩስ ልውውጥ ሲያደርግ እንደነበርም ተገልጿል። ...

Read More »

ሕገ ወጥ የመሳሪያና የገንዘብ ዝውውር እየጨመረ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 16/2010) በኢትዮጵያ ሕገ ወጥ የመሳሪያና የገንዘብ ዝውውር እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ። ይህ በሃገሪቱ ሰላምና ኢኮኖሚ ላይ ተጽእኖ ለማድረግ ያለመ ስለመሆኑም የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ገልጸዋል። የጦር መሳሪያዎቹ ከቱርክ ተነስተው በሱዳንና በጅቡቲ በኩል እየገቡ መሆናቸውንም ከኮሚሽነሩ መግለጫ መረዳት ተችሏል። ይህ በእንዲህ እንዳለም በጥቁር ገበያና በመደበኛ የሚመነዘረው የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተቀራራቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸው ታወቋል። በዶላር እስከ 10 ብር የነበረው ልዩነት ወደ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የተከሰተው የፖለቲካ ሁኔታ ሰራዊቱን ሊጎትተው አይገባም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 16/2010) በኢትዮጵያ የተከሰተው የፖለቲካ ሁኔታ ሰራዊቱን ሊጎትተው አይገባም ሲሉ ጠቅላይ ኢታማጆር ሹሙ አሳሰቡ። ኢታማጆር ሹሙ ጄኔራል ሰአረ መኮንን በኢትዮጵያ የታየው ለውጥ ከዘራችን ይልቅ በኢትዮጵያዊነታችን እናስብ የሚል ነው በማለትም ተናግረዋል። በፓርቲዎች ስኩቻ ውስጥ ግን አያገባንም ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ከሐገር መከላከያ ሰራዊት መኮንኖች ጋር የተወያዩትና በመከላከያ ሰራዊቱ ፕሮግራም ላይ በተላለፈው መልዕክታቸው ሰራዊቱ ከፖለቲካ ነጻ ሆኖ ለሕገመንግስቱና ለሕገመንግስታዊ ስርአቱ እንደሚቆም አረጋግጠዋል። ...

Read More »

ሁለቱ ሲኖዶሶች ወደ አንድ ሲኖዶስ እንዲመጡ ከስምምነት ተደረሰ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 16/2010) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን አባቶች መካከል የተጀመረው የእርቅ ጉባኤ ሁለቱ ሲኖዶሶች ወደ አንድ ሲኖዶስ እንዲመጡ ከስምምነት ላይ መደረሱ ተገለጸ። በዚህም የቀድሞው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዎስ የቤተክርስቲያኒቱን መንበር እንዲይዙ ይደረጋል ማለት ነው። አሁን በሃገር ቤት ባለው ሲኖዶስ ያሉት አቡነ ማቲያስ ደግሞ የቤተክርስቲያኒቱን የአስተዳደር ስራ እንዲሰሩ ተወስኗል ተብሏል። ለሰላም ድርድሩ ተቀምጠው የነበሩት አባቶችም በጉዳዩ ዙሪያ ...

Read More »