ግንቦት ፲፯ ( አሥራ ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረው ወጣቱ ፖለቲከኛ ዮናታን ታስፋየ ፌስቡክ ላይ በሚጽፋቸው ጽሁፎች ወንጀለኛ ተብሎ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የ6 አመታት ከ3 ወር እስር ተፈርዶበታል። ዮናታን በሰላማዊ ትግል ፍጹም የሚያምን ወጣት እንደነበር የሚናገሩት የቅርብ ጓደኞቹ፣ እንደሱ የፖለቲካ እምነት ቢሆን ኖሮ እንኳንስ እስር ቤት ሊያስገባው፣ ሰላማዊነቱ፣ የሰላም ተሸላሚ ባስደረገው ...
Read More »Amsterdam
ህወሃት የብዓላ ወረዳን ወደ ትግራይ ለማካለል እየተንቀሳቀሰ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ገለጹ
ግንቦት ፲፮ ( አሥራ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአፋር ክልል የምትገኘውን የብዓላ ወረዳን ወደ ትግራይ ክልል ለማካለል ሕወሃት የልዩ ወረዳ መብት እንዲፈቀድለት ጥያቄ አቅርቧል። የወረዳዋ ነዋሪ የሆኑ የትግራይ ብሔር ተወላጆች ነባር ነዋሪ የሆኑትን የአፋር ብሄር ተወላጆች በማግለል የስልጣን እና የሃብት ቅርምቱን በበላይነት ተቆጣጥረዋል። ባለፉት 26 ዓመታት ውስጥ በክልሉ በተለይም በጨው ምርታቸው በሚታወቁት አፍዴራ፣ ዳሉል፣ ኤርታአሌ፣ ፖታሽ፣ ...
Read More »በኢትዮጵያ አፋጣኝ የምግብ እርዳታ የሚፈልጉና በርሃብ የተጠቁት ዜጎች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ተዘገበ
ግንቦት ፲፮ ( አሥራ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፊውስ ኔት ፣ በኢትዮጵያ የተከሰተው ረሃብ ወደ አሳሳቢ ደረጃ እንደሚደርስና የምግብር እርዳታ የሚሹ ወገኖች ቁጥር ከዚህ በፊት ከተገለጸው እንደሚጨምር ዘግቧል። በቅርቡ 7 ሚሊዮን 700 ሰዎች አፋጣኝ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጾ ነበር። ድርቁ የቤት እንስሳትን ማውደሙን፣ የሚጥለው ዝናብ አስተማማኝ አለመሆኑንና የሚላከው እርዳታም በቂ አለመሆኑን የተመድ የመረጃ መረብ ገልጿል። በኢትዮጵያ ...
Read More »ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ጥፋተኛ ተባለ
ግንቦት ፲፮ ( አሥራ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከታህሳስ 15/2008 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኘው የነገረ ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ግንቦት16 ቀን 2009 ዓም በዋለው ችሎት ጥፋተኛ የተባለ ሲሆን፣ የቅጣት ውሳኔውን ግንቦት18፣ 2009 ዓም እንደሚሰማ ተነግሮታል። ፍርድ ቤቱ ፣ ጋዜጠኛው ከተለያዩ የሰማያዊ አባላት መረጃ በመሰብሰብ ኢሳት ለተሰኘ የቴሌቭዥን ጣቢያና ለግንቦት7 አመራሮች ማስተላለፉን ጠቅሷል። ...
Read More »መምህር የሰው ወንድሙ ከአራት ወራት እስር በኋዋላ በነጻ ተለቀቀ
ግንቦት ፲፮ ( አሥራ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት ቤት የሕክምና መምህር ፣ የተቋሙ ዲን እንዲሁም ተመራማሪ የሆነው ወጣት የሰው ወንድሙ ማሙዬ ለአራት ወራት በማእከላዊ እስር ቤት ሲሰቃይ ቆይቶ በነጻ ተለቋል። የሰው ወንድሙን የታሰረው “ አንድ ተጠርጣሪ የሆነ ግለሰብን መኖሪያ ቤትህ ለአንድ ቀን አሳድርሃል፣ እንዲሁም ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አለህ” የሚሉ መረተቢስ ውንጀላቸው ቀርበውበት ...
Read More »ሱዳን የግብጽን ተሽከርካሪዎችና ታንከሮች መማረኳን አስታወቀች
ግንቦት ፲፮ ( አሥራ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር በዳርፉር አካባቢ ሰሞኑን በተደረገው ጦርነት የሱዳን ጦር ሃይል የግብጽን ተሽከርካሪዎችና ታንከሮች ከአማጽያኑ እጅ ላይ መማረኩን ገልጸዋል። ፕሬዚዳንት አልበሽር “ በዙሪያችን ያሉ አገራት እየፈራረሱ ነው፣ ጦራቸውም እየፈራረሰ ነው፣ ነገር ግን የሱዳን መከላከያ ሰራዊት የቱንም ያክል ሴራ እና ተንኮል ይሸረብበት፣ አሁንም በጥንካሬ ዘልቋል።” ብለዋል። የሱዳን ጦር ...
Read More »በአገሪቱ ያሉ የደህንነት ሰራተኞች ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው
ግንቦት ፲፭ ( አሥራ አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሚያዚያ ወር መጀመሪያ ላይ በአገሪቱ የሚገኙ ዋና ዋና የደህንት አባላት ድሬዳዋ ውስጥ ለ9 ቀናት የቆየ የማጣሪያና የመለያ ስብሰባ አካሂደዋል። በስብሰባው ላይ የህወሃት አባል ያልሆኑ የሌሎች ብሄር ተወላጆች፣ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የደህንነት አባላትን ለጠላት አጋልጠው በመስጠት ህይወታቸው እንዲያልፍ እያደረጉ ነው በሚል ከፍተኛ ወቀሳ ደርሶባቸዋል። የደህንነት አባላቱ ለስርዓቱ ታማኝ ያልሆኑ ...
Read More »ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የአለም የጤና ድርጅት መሪ ሆነው ተመረጡ
ግንቦት ፲፭ ( አሥራ አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአለም የጤና ድርጅትን በዳይሬክተርነት ለመምራት ለመጨረሻው ዙር ውድድር የቀረቡት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ ከኢትዮጵያ ዶ/ር ዴቪድ ናባሮ ከእንግሊዝ እንዲሁም ዶ/ር ሳኒያ ኒሽታር ከፓኪስታን የመጨረሻውን የምረጡኝ ዘመቻ ቅስቀሳ ካደሩ በሁዋላ ዶ/ር ቴዎድሮስ ተመርጠዋል። ሁሉም ተወዳዳሪዎች የ15 ደቂቃ ንግግሮችን ያደረጉ ሲሆን፣ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ቢመረጡ ሁሉም ዜጎች የጤና ሽፋን እንዲያገኙ እንዲሁም ...
Read More »ኢትዮጵያ “ በኤርትራ ላይ አዲስ ፖሊስ አውጥቻለሁ” ማለቷ ባዶ ማዘናጊያ ነው ሲሉ የኤርትራው መሪ ተናገሩ
ግንቦት ፲፭ ( አሥራ አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኤርትራው ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ለአገር ውስጥ የሚዲያ አካላት እንደተናገሩት፣ ህወሃት በኤርትራ ላይ አዲስ ፖሊሲ ነድፌያለሁ ማለቱ ፣ በአገር ውስጥ የገባበትን የፖለቲካ አጣብቂኝ ተከትሎ ትኩረት ለማስቀየስ በሚል የሚለቀው ፕሮፓጋንዳ ነው። ይህ ትርጉም የለሽ ፕሮፓጋንዳ በኤርትራ ላይ የሚያመጣው ተጽኖ አይኖርም ሲሉም አቶ ኢሳያስ ተናግረዋል። ህወሃት የተከተለው የተሳሳተ ፖሊሲ በኤርትራና ...
Read More »በአውሮፓ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በስዊዘርላንድ ጄኔቭ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም እንዳይመረጡ ከፍተኛ ተቃውሞ አሰሙ
ግንቦት ፲፬ ( አሥራ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጽ/ቤት ፊት ለፊት በተካሄደው ተቃውሞ ኢትዮጵያውያን ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የአለም የጤና ድርጅት ሆነው ለመጨረሻው ዙር ውድድር መቅረባቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ተቃውመዋል። ዶ/ር ቴዎድሮስ እና እርሳቸው የሚወክሉትን የህወሃት /ኢህአዴግ አገዛዝ ፖሊሲዎችና በስልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ የሰሩዋቸውን ወንጀሎች እየጠቀሱ ውግዘታቸውን አሰምተዋል። ከለንደን ወደ ጀኔቫ በመሄድ ሰልፉን ሲያስተባብሩ ከነበሩት ...
Read More »