በጎንደር የስራ ማቆም አድማው ለ3ኛ ቀን ቀጥሎ ዋለ (ኢሳት ዜና የካቲት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) በአማራ ክልል የተጠራውን የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ የጎንደር ከተማ ህዝብ አድማውን ለ3ኛ ቀን ሲያካሂድ ውሎአል። ከፍተና ቁጥር ያላቸው ወታደሮች በከተማዋ እየተንቀሳቀሱ የስነ ልቦና ጫና ለመፍጠር ሙከራ ቢያደርጉም፣ ነጋዴዎች በአቋማቸው በመጽናት የመጨረሻውን ቀን የአድማ ጥሪ ተግባራዊ አድርገዋል። አድማውን አስተባብረዋል የተባሉ አንዳንድ ወጣቶች መታሰራቸው ታውቋል። በባህርዳር ከተማ ...
Read More »Amsterdam
በጉራጌ ዞን የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ የደህንነት ተቋማቱን ማስጨነቁን ምንጮች ገለጹ
በጉራጌ ዞን የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ የደህንነት ተቋማቱን ማስጨነቁን ምንጮች ገለጹ (ኢሳት ዜና የካቲት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) ለ7 ቀናት በወልቂጤና ሌሎችም የጉራጌ ከተሞች የተካሄደው የስራ ማቆም አድማና የአደባባይ ላይ ተቃውሞ ለአገዛዙ የደህንነት አባላት ፈተና ሆኖ መሰንበቱን ምንጮች ገለጹ። ተቃውሞውን ለማስቆም የተለያዩ ሙከራዎችን ሲያደርጉ የነበሩ የደህንነት አባላት፣ የተጠቀሙባቸው ዘዴዎች ሁሉ ባለመስራታቸውና አድማው አዲስ አበባ ባሉ የጉራጌ ተወላጆች ዘንድም ተግባራዊ ሊሆን ...
Read More »የክልል መንግስታት በጸጥታ ጉዳይ መግለጫ እንዳይሰጡ ታገዱ
የክልል መንግስታት በጸጥታ ጉዳይ መግለጫ እንዳይሰጡ ታገዱ (ኢሳት ዜና የካቲት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) ለሁለተኛ ጊዜ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ የአዋጁን ተግባራዊነት ከሚከታተለው እዝ ውጭ ማንኛውም የክልል ባለስልጣን በክልሉ ስላለው የጸጥታ ሁኔታ ምንም አይነት መግለጫ መስጠት እንደማይችል አግዷል። ከዚህ ቀደም የክልል ፕሬዚዳንቶች፣ የኮሚኔከሽን ሃላፊዎች እንዲሁም የዞን የጸጥታ ባለስልጣናት ሳይቀሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሚወስዱት እርምጃ ላይ መግለጫዎችን ሲሰጡ ቆይተዋል። የኦሮምያ ክልል ...
Read More »አራት የወልቃይት የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላትና በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተጠርጥረው የታሰሩ ሁለት ኮሎኔሎች ተፈቱ
አራት የወልቃይት የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላትና በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተጠርጥረው የታሰሩ ሁለት ኮሎኔሎች ተፈቱ (ኢሳት ዜና የካቲት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) ሕገመንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው የወልቃይት አማራ ማንነት ኮሚቴ በማዋቀር፣ የማንነት መብታቸውን በመጠየቃቸው ብቻ የታሰሩት አቶ መብራቱ ጌታሁን፣ አቶ አታላይ ዛፌ፣ አቶ ጌታቸው አደመ እና አቶ ተሻገር ወልደሚካኤል ዛሬ ክሳቸው ተቋርጦ ተፈትተዋል። ሰሞኑን በጎንደር እስር ቤት የነበሩት ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ...
Read More »በጉራጌ ዞን የተጀመረው አድማ ለ6ኛ ቀን ቀጥሎአል
በጉራጌ ዞን የተጀመረው አድማ ለ6ኛ ቀን ቀጥሎአል (ኢሳት ዜና የካቲት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) በወልቂጤ፣ በጉብሬ፣ በአገናና በሌሎችም አካባቢዎች የተጀመረው የስራ ማቆም አድማና ተቃውሞ ለስድሰተኛ ቀን መቀጠሉን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የስራ ማቆም አድማው ወደ አደባባይ ተቃውሞ ተሸጋግሮ የተወሰኑ ሰዎች በጸጥታ ሃይሎች መገደላቸው ይታወሳል። ተቃውሞው አድማሱን በማስፋት ወደ እዣ፣ ቺሃ፣ እምድብር፣ እነሞር እና ኢነር ወረዳ የጉመር ወረዳን መቀላቀላቸውን ወኪላችን ገልጿል። ...
Read More »በጎንደርና ባህርዳር የስራ ማቆም አድማው ለሁለተኛ ቀን ቀጥሏል
በጎንደርና ባህርዳር የስራ ማቆም አድማው ለሁለተኛ ቀን ቀጥሏል (ኢሳት ዜና የካቲት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) በአማራ ክልል የተጠራው የስራ ማቆም አድማ በጎንደር ከተማ ለሁለተኛ ቀን በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥሎአል። በከተማው ምንም አይነት የንግድ እንቅስቃሴውም ሆነ የተሽከርካሪ አገልገሎት የለም። የአገዛዙ ካድሬዎች የንግድ ድርጅቶችን ለማስከፈት ያደረጉት ጥረት እንዳልተሳካ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክልታል። በባህርዳር ትናንት የተጀመረውን አድማ ተከትሎ የአገዛዙ ባለስልጣናትና ሰራተኞች የንግድ ድርጅት ባለቤቶችን ...
Read More »ወጣት ንግስት ይርጋን ጨምሮ የተወሰኑ እስረኞች ክሳቸው ተቋርጦ ተፈቱ
ወጣት ንግስት ይርጋን ጨምሮ የተወሰኑ እስረኞች ክሳቸው ተቋርጦ ተፈቱ (ኢሳት ዜና የካቲት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) በሰሜን ጎንደር ተጀምሮ በአማራ ክልል የተቀጣጠለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ፊት ሆነው ከመሩትና ካስተባበሩት መካከል በግንባር ቀደምነት የምትጠራዋ ወ/ት ንግስት ይርጋ ከሷ ተቋርጦ ከእስር ቤት ወጥታለች። በሽብር ወንጀል የተከሰሰችው ወ/ት ንግስት ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ ማእከላዊ እስር ቤት በተዘዋወረችበት ወቅት ከፍተኛ የሆነ ሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሞባታል።ወ/ት ...
Read More »እንግሊዝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ እንደሳዘናት ገለጸች
እንግሊዝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ እንደሳዘናት ገለጸች (ኢሳት ዜና የካቲት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) የአገሪቱ የውጭ ግንኙነት መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ፣ “ ወዳጃችን እና አጋራችን ኢትዮጵያ አሳሳቢ በሆነ ጊዜ ላይ ትገኛለች” ብሎአል። ስርዓት ባለው መልኩ የፖለቲካ ለውጥ ለማምጣት የሚደረገው ጥረት አወንታዊ ቢሆንም፣ ይህንን ጥረት የሚያበላሽ ፣ አሳሳቢና አሳዛኝ የሆነ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል ሲል በአዋጁ ላይ ያለውን ተቃውሞ ገልጽ አድርጓል። ...
Read More »በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የስራ ማቆም አድማ ተጀመረ
በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የስራ ማቆም አድማ ተጀመረ (ኢሳት ዜና የካቲት 12 ቀን 2010ዓ/ም) በጎንደር፣ በደብረታቦርና በባህርዳር ከተሞች ሰኞ የካቲት 12 ቀን 2010 ዓ.ም የስራ ማቆም አድማ ተጀምሯል። በጎንደር በመካሄድ ላይ ባለው አድማ የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል። የንግድ ድርጅቶችም እንዲሁ ተዘግተዋል። ወጣቶች በተለያዩ አደባባዮች ተሰባስበው በመታዬት የንግድ ድርጅቶችን ለማስከፈት የሚያስገድዱትን ባለስልጣናት ሲያስጠነቅቁ ታይተዋል። በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች የስራ ማቆም አድማው ...
Read More »ከሰሜን ወሎ የታፈሱት ወጣቶች በስልጠና ወቅት ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያሰሙ እንደነበር ታወቀ
ከሰሜን ወሎ የታፈሱት ወጣቶች በስልጠና ወቅት ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያሰሙ እንደነበር ታወቀ (ኢሳት ዜና የካቲት 12 ቀን 2010ዓ/ም) ከጥር 21 ቀን 2010 ዓም ጀምሮ ከወልድያ፣መርሳና ሮቢት የተሰባሰቡ ዜጎች ጃሪ በሚባል የስሪንቃ እርሻ ምርምር የንብ ማንባት ምርምር የሚያደርግበት ጫካ ውስጥ መጣላቸውን የሚገልጹት ከእስር የተፈቱት ወጣቶች፣ ቦታው ፈፅም ለማረሚያ ቤት ያልተዘጋጀ መፀዳጃ ቤት የሌለው፣ውሀ ፣የህክምና ቦታ የሌለው ነበር ይላሉ። እስረኞቹ ሁኔታዎች ካልተሻሻሉ ምግብ ...
Read More »