Amsterdam

በፌደራል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባህርዳር ከተማ ተወካይ የነበሩት ወይዘሮ አዲሴ ዘለቀ አሟሟት አነጋጋሪ ሆኗል ።

ኅዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህር ዳር ከተማ  ሰፈነ ሰላም ክፍለ ከተማ ነዋሪ የነበሩትና የባህር ዳርን ህዝብ በመወከል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያገለግሉ የነበሩት ወይዘሮ አዲሴ ዘለቀ ባልታወቀ ሁኔታ በአዲስ አበባ ከተማ በትላንትናው እለት ማለትም ማክሰኞ ህዳር 6 /2009 ዓም. በጽ/ቤታቸው ሞተው ከተገኙ በሁዋላ ፣ ጉዳዩ የባህርዳርን ህዝብ እያነጋገረ ነው። ወ/ሮ አዲሴ በፓርላማው በቆዩበት ወቅት ጠንከር ...

Read More »

በስዊዲን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የርሃብ አድማ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል

ኅዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ገዥዎች በዜጎች ላይ የሚያደርሱትን ኢሰብዓዊ የመብት ጥሰቶች በማውገዝ ከትናትና ማክሰኞ ረፋድ ላይ የጀመረው የርሃብ አድማ ለሁለተኛ  ቀንም ቀጥሏል። ከተለያየ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ኢትዮጵያዊያን አስቸጋሪው የአየር ንብረት ሁኔታ ሳይበግራቸው ለወገኖቻቸው አጋርነታቸውን አሳይተዋል። በስዊድ ፓርላማ ፊትለፊት በመገኘት የስዊዲን መንግስት አንባገነኑን የህወሃት ኢህአዴግ የሚያደርገውን የገንዘብ እና ማንኛውንም ድጋፍ እንዲያቆም ሲሉ ጠይቀዋል። የድማው ተሳታፊ ...

Read More »

አልሸባብ በሶማሊያ እና ኢትዮጵያ ድንበር ላይ የምትገኘውን የታይገሎ ከተማን በቁጥጥሩ ስር አዋለ

ኅዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በበቆል ክልል በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ አዋሳኝ ድንበር አዋሳኝ ላይ የምትገኘውን የታይገሎ ከተማን በከፍተኛ ውጊያ አስለቅቆ አልሸባብ ድጋሜ በቁጥጥሩ ስር ማዋሉን ሸበሌ ሚዲያ ዘግቧል። ከቅርብ ወራት ወዲህ ሃይሉን እያጠናከረ የመጣው አልሸባብ ቀድሞ በኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ስር የነበረችውን የታይገሎ ከተማን ለማስለቀቅ በመኪና ላይ በተጠመደ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት መታገዙን ሪፖርቶች አመላክተዋል። ማክሰኞ እለት በከተማዋ ...

Read More »

በደቡብ ኦሞ ዞን የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ታሰሩ

ኅዳር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኮማንድ ፖስት ስም የደቡብ ኦሞን ዞን የሚመሩት የህወሃት የደህንነት ሰራተኞች፣ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችንና ወጣቶችን እየያዙ በማሰር ላይ ናቸው። የኦሞ ህዝብ ዲሞክራሲ ህብረት ም/ሊቀመንበርና የዞኑ ተጠሪ መምህር አለማየሁ፣ የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ የዞን ተጠሪ የነበሩት አቶ ስለሺ ጌታቸው እንዲሁም የኦሞ ህዝብ ስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ዳዊት ካብት ይመር ትናናት ከንጋቱ 12 ሰአት ...

Read More »

በደቡብ ምስራቅ የአገሪቱ ክፍል ከፍተኛ ድርቅ መከሰቱ ተዘገበ

ኅዳር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመረጃ ኔትወርክ እንዳስታወቀው በኦሮምያ በተለይም በቦረና አካባቢ፣ በደቡብና ሶማሊ አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ የምግብና የውሃ እጥረት ተከስቷል። አርብቶአደሮች እንስሶቻቸውን ይዘው ምግብ እና ውሃ ፍለጋ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የገለጸው ድርጅቱ፣ አፋጣኝ አለማቀፍ እርዳታ ካልተገኘ ድርቁ የከፋ ጉዳት ያስከትላል ብሎአል። የአለማቀፉ የምግብ ድርጅት ለአስቸኳይ እርዳታ በሚል 14 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ...

Read More »

በስዊድን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለሁለት ቀናት የሚቆይ የርሃብ አድማ አደረጉ

ኅዳር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አምባገነኑ የህወሃት ኢህአዴግ መንግስት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚያካሂደውን የጅምላ ጭፍጨፋ፣ እስራት እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በማውገዝ በስዊድን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ለሁለት ቀናት የሚቆይ የርሃብ አድማ እያደረጉ ነው። ቁጥራቸው ከሰላሳ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በስዊድን ፓርላማ ፊት ለፊት ቀዝቃዛው በረማው የአየርንብረት ሳይበግራቸው ለወገኖቻቸው አጋርነታቸውን አሳይተዋል። ከተለያዩ የሲቪክ ማኅበረሰቦች የተውጣጡት እነዚህ የርሃብ አድማ ...

Read More »

የኢትዮ ምዳር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ የአንድ ዓመት እስር እና የገንዘብ መቀጮ ተፈረደበት

ኅዳር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አራዳ የሚገኘው 6ኛ የፌደራሉ አንደኛ ደረጃ ወንጀል ችሎት ህዳር 6 ቀን 2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት የኢትዮ ምዳር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ ላይ የአንድ ዓመት እስር እና የ1 ሽህ 500 ብር በግል እና በድርጅቱ ስም ደግሞ የ10 ሽህ ብር መቀጮ እንዲከፍል ሲል ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አሳልፎአል። ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁን ለእስራት ...

Read More »

አልሸባብ ወደ ማእከላዊ ሶማሊያ እየገሰገሰ ነው

ኅዳር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ጦር አሚሶን ቁጥጥር ስር የነበሩ የሶማሊያ ግዛቶች በአልሸባብ ቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው። በደባቡባዊ እና ማእከላዊ ሶማሊያ አካባቢዎች በኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ጦር እጅ የነበሩ አስር ከተሞችን አሸባሪው አልሸባብ ዳግም በቁጥጥሩ ስር ማድረጉን አልጀዚራ ከስፍራው ዘግቧል። ባለፈው ወር ብቻ የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ጦር የለቀቋቸው አራት ከተሞች ሙሉ ...

Read More »

በእንቀሽ በወታደሮችና ራሳቸውን ባደራጁ ሃይሎች መካከል ያለው ፍጥጫ እንደቀጠለ ነው።

ኅዳር ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ እንቃሽ አካባቢ ራሳቸውን ያደራጁ የነጻነት ሃይሎች ከአገዛዙ ወታደሮች ጋር ለሳምንት የዘለቀው ፍጥጫ ዛሬም ቀጥሎአል። የቡድኑ አስተባባሪ ለኢሳት እንደገለጸው፣ ቀደም ብሎ ተደርጎ በነበረው የተኩስ ልውጥ በአገዛዙ ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል። ምንም እንኳ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች አካባቢውን ከበው በመጠባበቅ ላይ ቢሆንም፣ ጫካ የገቡት ሃይሎች አሁንም በጥሩ ...

Read More »

የኦጋዴን ነጻአውጪ ግንባር በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ የደፈጣ ጥቃት መሰንዘሩን አስታወቀ

ኅዳር ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኦጋዴን ነጻአውጪ ግንባር የሃለጋ ክንፍ ታጣቂዎች በዱሁሁን አውራጃ ውስጥ በገጠር መንደሮች በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ሰቆቃ ሲፈጽሙ ነበሩ ባላቸው የመንግስት ወታደሮች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን አስታውቋል።በዱሁሁን በሚገኙ ሰላማዊ ዜጎች ላይ አስገድዶ መድፈር፣ ድብደባ እና የጅምላ እስራት ሲፈጽሙ ከነበሩት ውስጥ በደፈጣ ውጊያ 5ቱ መገደላቸውንና 7 ቱ ደግሞ መቁሰላቸውን የግንባሩ ወታደርዊ ክንፉ ገልጿል። አስቸኳይ ...

Read More »