Amsterdam

በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የምስራቅ አፍሪካ ስደተኞች በባሕር ወደ የመን እየፈለሱ ነው

ኅዳር ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የምስራቅ አፍሪካ አገራት ስደተኞች ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው የተሻለ ኑሮ ፍለጋ በእርስበርስ ጦርነት ወደምትታመሰው የመን በብዛት እየገቡ  ነው። አስተማማኝ ባልሆኑ ጀልባዎች ተጭነው የመን የገቡ ኢትዮጵያዊያን እና ሶማሊያዊያን ስደተኞች በያዝነው ዓመት ብቻ ከመቶ ሽህ መብለጡን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳውቋል። እስካሁን ድረስ ቁጥራቸው ከ90 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን እና ከ17 ሽህ በላይ ሶማሊያዊያን ዜጎች ከሞት ...

Read More »

ጥንታዊው የገዳ ስርዓት በዩኔስኮ ቅርስነት ተመዘገበ

ኅዳር ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ተቋም ዩኔስኮ በመዲናችን አዲስ አበባ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኤኮኖሚክስ አዳራሽ ባደረገው 11ኛው መደበኛ ስብሰባው ላይ ጥንታዊውን የገዳ ስርዓትን በዓለም በማይዳሰሱ ቅርስነት መዘግቦታል። የገዳ ስርዓት በኢትዮጵያ የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ዘንድ ባሕላዊ አስተዳደራዊ ስርዓት ሆኖ  ለዘመናት እውቀትን ከትውልድ ወደ ትውልድ በማሸጋገር ያገለገለ ጥንታዊ አስተዳደራዊ መዋቅር መሆኑ ...

Read More »

በህወሃት/ ኢህአዴግ ኩባንያዎች ምርቶች ላይ የተጀመረው ማዕቀብ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ኅዳር ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ህወሃት/ ኢህአዴግ በሃገሪቱ ዜጎች ላይ በሚያካሂደው ግድያና ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ምክንያት የፓርቲውን ምርቶች አለመጠቀምና በሃብቶቹም ላለመገልገል የወሰነው የአማራ ክልል ነዋሪ ህዝብ፣ ይህን አቋሙን አጠናክሮ በመቀጠሉ በፓርቲው የግል ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያደረሰ ነው። በአማራ ክልል ዋና ዋና የንግድ መነኻሪያ ከተሞች ህብረተሰቡ የህወሃት/ ኢህአዴግ ኩባንያዎች ምርቶች የሆኑትን ዳሽን ቢራ፣ራያ ቢራ ፣መሰቦ ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር በነጻነት ሃይሎች እና በአገዛዙ ወታደሮች መካከል የሚካሄደው ጦርነት ቀጥሎ ዋለ

ኅዳር ፳ (ሃያ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በነጻነት ሃይሎች እና በገዢው ፓርቲ ወታደሮች መካከል ለሳምንታት የዘለቀው ጦርነት ዛሬ በደቡብ ጎንደርና በበለሳ መሃከል ዳዊጭ በሚባል አካባቢ ቀጥሎ ውሎአል። በሁለቱም ወገኖች ስለደረሰው ጉዳት ዝርዝር መረጃ አልደረሰንም። ይሁን እንጅ ጦርነቱ ከፍተኛ መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል። በሌላ በኩል አገዛዙ ሰራዊቱን ወደ ተለያዩ አካባቢዎች እያንቀሳቀሰ ሲሆን ፣ ትናንት ሰኞ ወታደሮችን የጫኑ ኦራል ...

Read More »

የጎንደር ማረሚያ ቤት ሃላፊ ታሰሩ

ኅዳር ፳ (ሃያ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፈው አርብ ጀምሮ በቁጥጥር ስር የሚገኙት ኢንስፔክተር ልጃለም መሰረት የታሰሩት ከኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ጋር በተያያዘ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። ኢንስፔክተሩ ባለፈው አርብ ኮሎኔል ደመቀ ፍርድ ቤት ቀርበው በነበረበት ወቅት እጃቸው በካቴና ሳይታሰር እንዳይቀርቡ አድርገዋል በሚል ነው። ኢንስፔክተሩ እስካሁን ደረስ ፍርድ ቤት አልቀረቡም። የአካባቢው ፖሊሶች የኢንስፔክተሩን መታሰር አጥብቀው እየተቃወሙት ነው።

Read More »

በኬንያ ቱርካና ሃይቅ ዳርቻዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች እየተሰደዱ ነው

ኅዳር ፳ (ሃያ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜናዊ ምዕራብ ኬንያ በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ዜጎች ቁጥራቸው ከ10 ሽህ በላይ የሚሆኑ ቤተሰቦች መኖሪያ ቀያቸውን በመተው ወደ ኡጋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ተሰደዱ። የአካባቢው ነዋሪዎችን ለስደት ያበቃቸው ለከብቶቻቸው የግጦሽ ፣ ለምግብ እና የመጠጥ ውሃ  ፍለጋ ሲሆን በድርቁ ምክንያት ከአንድ ሺህ በላይ የቤት እንስሳት ሞተዋል። ተፈናቃዮቹ በኡዳንዳ ከፍተኛ ተግዳሮቶች እንደተደቀኑባቸው ሲቲዝን ...

Read More »

ዓርበኞች ግንቦት 7 በለንደን በተሳካ ሁኔታ ሕዝባዊ ስብሰባውን አካሄደ

ኅዳር ፳ (ሃያ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዓርበኞች ግንቦት 7 በእንግሊዝ ዋና ከተማ ለንደን ውስጥ ሕዝባዊ ስብሰባውን  እ.ኤ.አ. ኖቨንበር 27 ቀን 2016 በድምቀት አካሄደ። በስፍራው ላይ የአፍሪካ ኢንስቲቱት ሴኩሪቲ ስተዲስ ዳሬክተር የሆኑት የተከበሩ ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ፣ ሚስ ካትሪን ፕሉየር በለንደን ዩናይትድ ኔሽን አሶሴሽን የሳውዝ ኢስት ሪጅን ዳሬክተር እና የዓርበኞች ግንቦት 7 ከፍተና አመራር አባል አቶ ብዙነህ ጽጌ በስብሰባው ላይ ...

Read More »

በነጻነት ሃይሎች እና በህወሃት/ኢህአዴግ  ወታደሮች መካከል የሚካሄደው ውጊያ እንደቀጠለ ነው

ኅዳር ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዳባት ወረዳ ድልድይና መንደርጌ አካባቢ በህዝብ በሚደገፉ የነጻነት ሃይሎችና በህወሃት/ኢህአዴግ ወታደሮች መካከል የተጀመረው ውጊያ ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ በአገዛዙ ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ህዝብ ሙሉ በመሉ ድጋፉን እየሰጠ ባለው ጦርነት ቁጥራቸው በውል ያልተገለጸ የአገዛዙ ወታደሮች መገደላቸውንና የጦር መሳሪያዎችን መማረካቸውን ምንጮች ገልጸዋል። በርካታ ወታደሮችን የጫኑ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ...

Read More »

በፍኖተሰላም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች ሰፈሩ

ኅዳር ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የከተማዋ ነዋሪዎች እንደገለጹት በደንብ የታጠቁ ወታደሮች ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ወደ ከተማው የገቡ ሲሆን፣ የጃቢ ጠናን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጽ/ቤት ግቢን ካምፕ አድርገውታል። በከተማው በብዛት የሚታዩት ወታደሮች ናቸው የሚሉት ነዋሪዎች፣ እነሱ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ በከተማው ውጥረት መጨመሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ወላጆችን “ልጆቻችሁን በጊዜ ወደ ቤታችሁ አስገቡ” እያሉ መሆኑን የተናገሩት ነዋሪዎች፣ ህዝቡ መታወቂያ እንዲያሳይ ...

Read More »

የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ በስዊድን የተሳካ ስብሰባ ማካሄዱን ገለጸ

ኅዳር ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በ4 የፖለቲካ ድርጅቶች የተመሰረተው የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ትናንት እሁድ በስቶክሆልም ከተማ የተሳካ ስብሰባ ማድረጉን ገልጿል። የአርበኞች ግንቦት7 መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር መሪ አቶ ሌንጮ ለታ እንዲሁም የአፋር ህዝብ ፓርቲ መሪ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ በስብሰባው ላይ የተገኙ ሲሆን፣ ስብሰባው በስቶክሆልም /ስዊድን የንቅናቄው አስተባባሪ አቶ ዘለሌ ጸጋ ስላሴ ንግግር ...

Read More »