ጥር ፬ (አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ከተነሳው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ጋር በተያያዘ ለወራት በእስር ላይ የነበሩ ሶስት ግብጻዊያን ዜጎች ከእስር መስፈታታቸውን የግብጽ ውጪ ጉዳይ ሚንስቴር መስሪያ ቤት አስታወቀ። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች ከተገደሉበት የኢሬቻ እልቂት በኋላ ካለምንም ጥፋታቸው በኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር ውለው ምንም ዓይነት ክስ ያልቀረበባቸው መሆኑንም መግለጫው አትቷል። ሶስቱም ግብጻዊያን በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ...
Read More »Amsterdam
አልሸባብ ሁለት ግብረሰዶማዊያንን እና አንድ ለኢትዮጵያ መንግስት ሲሰልል ነበረ ያለውን ግለሰብ ገደለ
ጥር ፫ (ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ማክሰኞ እለት ጽንፈኛው ቡድን አልሸባብ 20 ዓመት ወጣት ኢሳቅ አብሽሮ እና የ15 ዓመት ታዳጊ አብዱረዛቅ ሸክ ዓሊ ግብረሰዶማዊ ምግባር ሲፈጽሙ በአልሸባብ ፖሊሲሶች ተይዘው ሞት ተፈርዶባቸው አንገታቸውን ተቀልተዋል። ከሁለቱ ወጣቶች በተጨማሪ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ጦር አሚሶን ስር ለሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር ሲሰልል ነበር በማለት ሰኢድ መሀመድ ዓሊ የተባለ አንድ የአካባቢው ...
Read More »በጎንደር የቦንብ ፍንዳታ ደረሰ
ጥር ፪ (ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ማምሻውን በደረሰን ዜና መሰረት በጎንደር ቀበሌ 18 በሚገኘው ኢንታሶል ሆቴል ቦንብ ፈንድቶ ሰዎች መጎዳታቸው ታውቋል። በሆቴሉ ውስጥ ፋሲል የእግር ኳስ ቡድን የባንክን ቡድን ማሸነፉን ተከትሎ የሚዝናኑ ወጣቶች ነበሩ። ከ5 በላይ በጽኑ የቆሰሉ ሰዎች ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ለማውቅ የተቻለ ሲሆን፣ ወታደሮችና ፖሊሶች አካባቢውን በመክበባቸው በትክክል የሞቱና የቆሰሉ ሰዎችን ቁጥር ለማወቅ አልተቻለም። ዛሬ ማክሰኞ ...
Read More »ከህዝባዊ ተቃውሞው በሁዋላ በርካታ ድርጅቶች ሃብታቸውን ማሸሽ ቀጥለዋል።
ጥር ፪ (ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ውስጥ ህዝባዊ አመጽ ከተነሳበት ጊዜ ጀምሮ በአገዛዙ ተስፋ በመቁረጥ ሃብታቸውን የሚያሸሹ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮአል። ስማቻው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የባንክ ባለሙያ እንደገጸሉት፣ ባለፉት 4 ወራት በርካታ የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ገንዘባቸውን እያወጡ ጥገኝነት ወደ ሰጣቸው አገር ሲመለሱ፣ ሌሎች ደግሞ ወደ ጎረቤት አገራት በመሄድ በንግድ እንቅስቃሴ ለመሳተፍ እየሞከሩ ነው፡። ...
Read More »የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ
ጥር ፪ (ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላው ኢትዮጵያ በነዳጅ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ መደረጉን ንግድ ሚንስቴር አስታውቋል። በዚህም መሰረት ቤንዚን በሊትር 16 ብር ከ61 ሳንቲም የነበረው አንድ ብር ከ13 ሳንቲም ጨማሪ ተደርጎበት17 ብር ከ92 ሳንቲም እንዲሸጥ ተብሎአል። ነጭ ናፍጣ 14 ብር ከ16 ሳንቲም የነበረው አንድ ብር ከ02 ሳንቲም ጭማሪ ተደርጎበት 15 ብር ከ18 ሳንቲም ይሸጣል። ኬሮሲን በሊትር 13 ...
Read More »የወልድያ ነዋሪዎች ለስታዲያም ማሰሪያና ለምረቃ በሚል ገንዘብ እንዲያዋጡ መገደዳቸውን ተናገሩ
ጥር ፪ (ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለሀብቱ ሼክ ሁሴን አላሙዲን በራሳቸው ወጪ ወልድያ ከተማ ላይ ዘመናዊ ስታዲየም እንደሚያስገነቡ በተናገሩት መሰረት፣ የስታዲየም ግንባታው ተጠናቆ ጥር 6 ቀን 2009 ዓም ይመረቃል። ምንም እንኳ ባለሀብቱ የግንባታውን ሙሉ ወጪ እንደሚሸፍኑ ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም፣ የመንግስት ሰራተኛው የ1 ወር ደሞዙን በአመት፣ የከተማው ነጋዴዎችም እንዲሁ የተለያዩ መጠን ያላቸውን መዋጮዎች ሲከፍሉ ቆይተዋል። አሁን ደግሞ ለስታዲየሙ ...
Read More »በጂጂጋ የተደረገው የጦር አዛዦች ስብሰባ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የሚደረገው ዘመቻ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ውሳኔ አሳለፈ
ጥር ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት በጂጂጋ ከተማ በተደረገው የከፍተኛ የጦር አዛዦች ስብሰባ ላይ በሰሜን ጎንደር የሚደረገውን ተቃውሞ ተከትሎ መወሰድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች ውሳኔዎችን አሳልፏል። የምእራብ እዝ ማሰልጠኛ ሰሜን ጎንደር በሚገኘው ሰራባ በሚባለው ቦታ ላይ እንዲሆን የመጨረሻ ውሳኔ በደቡብ ምስራቅ እዝ በ13ኛ እና 32ኛ ክፍለ ጦሮች ስር የሚገኙ ሁለት ሬጀመንት ጦር ወደ ሰሜን ጎንደር በማምጣት፣ ሰሜን ጎንደርን ...
Read More »በአማራና ኦሮምያ ክልሎች አዲስ የእስር ዘመቻ ተከፈተ
ጥር ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በሳምንቱ መጨረሻ በኦሮምያ በተለይም በአዳማ ፣ ጉጂ እና ቦረና ዞኖች፣ በአማራ ክልል ደግሞ በጎንደር እና አዊ ዞኖች በርካታ ወጣቶች ተይዘው ታስረዋል። 10 ሺ ወጣቶች ከእስር መፈታታቸውን ባስታወቀ ሁለት ሳምንት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ አዲስ የተጀመረው የእስር ዜና በነዋሪዎች ላይ ጫና እየፈጠረ ነው። በአማራ ክልል በተለይ ከወራት በፊት ተደርጎ በነበረው ህዝባዊ ...
Read More »በአዳማ እና አካባቢው የውሃ እጥረቱ ተባብሶ ቀጠለ
ጥር ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዳማ ወረዳ አካባቢዎች የውሃ እጥረቱ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን ነዋሪዎቹ ለከፍተኛ ወጪና እንግልት ተዳርገዋል። በተለይ በአዳማ ናዝሬት ከተማ ውስጥ ያሉት የውሃ መስመሮች በአብዛሃኛው አገልግሎት አይሰጡም። ከዓመት በአል ዋዜማ ቀናት ጀምሮ ከተማ እና በአጎራባች ቀበሌዎች ውሃ ለማግኘት ረዥም ሰዓታት ወረፋ ለመያዝ ተገደዋል። የከተማዋ አስተዳደር ለውሃ ችግሩ እልባት ከመስጠት ይልቅ አሁንም በአዳዲስ የሹም ሽር ሹመት ...
Read More »በአዲስ አበባ ከተማ ከንግድ ይዞታቸው የተፈናቀሉ ነጋዴዎች ለከፍተኛ ስቃይ ተዳረጉ
ጥር ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በልማት ስም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለዘመናት ሃብት አፍርተው በንግድ ስራ ላይ ይተዳደሩበት ከነበሩት ይዞታቸው የተፈናቀሉ ነጋዴዎች ለሶስት ዓመታት በስቃይ ላይ መሆናቸውን አስታወቁ። ነጋዴዎቹ ቤተሰባቸውን ከሚያስተዳድሩበት ይዞታቸው ተነስተው በምትኩ ተለዋጭ ቦታ ይሰጣችኋል ቢባሉም እስካሁን ድረስ መስተዳድሩ የገባላቸውን ቃል አላከበረም። ቁጥራቸው ከአንድ ሺሕ በላይ የሚሆኑት እነዚህ ነጋዴዎች ከአስር በላይ የአክሲዮን ማኅበራትን መስረተው ተደራጅተው ...
Read More »