Amsterdam

በባህርዳር ከተማ የህወሃት አባላት ጥቃት ደረሰባቸው

ጥር ፳፭ (ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትናንት ምሽት በአንድ ሆቴል ውስጥ ዳሸን ቢራ ሲጠጡ የነበሩ 9 የህወሃት አባላት በስካር መንፈስ ውስጥ ሆነው ክብርና ማንነትን የሚነካ ንግግር በመናገራቸው ስሜታቸውን መቆጣጠር ያልቻሉ በሆቴሉ ሲገለገሉ የነበሩ ወጣቶች ተጠራርተው በመሰባሰብ በህወሃት አባላቱ ላይ ጥቃት አድርሰውባቸዋል። የህወሃት አባላቱ “ አናፋችሁ አናፋችሁ አሁን ጸጥ አላችሁ፣ ድሮም ከእኛ አታመልጡም” እያሉ ሲዝቱ እንደነበር የሚገልጹት ምንጮች፣ ...

Read More »

የውጭ ዘርፍ ንግድ ገቢ እያሽቆለቆለ ነው

ጥር ፳፭ (ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዋንኛነት በኦሮሚያና እና በአማራ ክልሎች ባለፈው ዓመት የተቀጣጠለውን ሕዝባዊ አመጽ ተከትሎ በኢትዮጵያዊያን 2009 ግማሽ የበጀት ዓመት ከማምረቻ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተገኘው የኤክስፖርት ገቢ እያሽቆለቆለ ነው። ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ እንዳመለከተው ከሐምሌ 1 ቀን 2008 እስከ ታህሳስ 30/2009 ዓ.ም ባሉት ስድስት ወራት ከማምረቻ ኢንዱስትሪ ዘርፍ 349 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ዕቅድ ተይዞ የነበረ ...

Read More »

በባህርዳር ኬላ ላይ ለሁለተኛ ቀን ከባድ ፍተሻ እየተካሄደ ነው

ጥር ፳፬ (ሃያ አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ፖሊሶች ከትናንት ማክሰኞ ጀምሮ እስካ ዛሬ ድረስ የተጠናከረ ፍተሻ በማድረግ ላይ ሲሆኑ፣ በርካታ ተሽከርካሪዎች የመፈተሽ ተራ እስከሚደርሳቸው ረጃጅም ሰልፎችን ሰርተው ለሰዓታት ቆመው መዋላቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ዋናው ፍተሻ የሚካሄደው በመራዊ አቅጣጫ ባለው የአዲስ አበባ ባህርዳር መስመር ላይ ሲሆን፣ ወደ ከተማው የሚገቡና የሚወጡ መኪኖች ጥብቅ ፍተሻ ይደረግባቸዋል። በአካባቢው በርካታ የፌደራል ፖሊሶች ...

Read More »

በአርባምንጭ የሚገኘው የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ በመፍረስ ላይ ነው ተባለ

ጥር ፳፬ (ሃያ አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጹት ለአካባቢው ህዝብ የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ በቡልጋሪያና በዲሞክራቲክ ጀርመን ድጋፍ በደርግ መንግስት ተጀምሮ ፣ በ1985 ዓም የተመረቀው የአርባምንጭ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ በመፈራረስ ላይ ይገኛል። ሰራተኞች እንደሚሉት ፋብሪካው በሶስት ፈረቃ በሚሰራበት ወቀት ለ1500 ሰራተኞች የስራ እድል ፈጥሮ ነበር። ፋብሪካው ስራ እንደጀመረ ወዲያውኑ በፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ አማካኝነት ለህወሃቱ አልሜዳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ እንዲሸጥ ...

Read More »

በሰሜን ወሎ በጥልቅ ተሃድሶ ስም በተጠራው ስብሰባ ላይ ውዝግብ ተነሳ

ጥር ፳፬ (ሃያ አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ወሎ ትናንት ጥር 24 2009 ዓም በዞኑ ጽቤቶች የጥልቅ ተሀድሶ ስብሰባ የተጠራ ሲሆን፣ ሰራተኞችና አመራሩ መስማማት ሳይቸሉ ቀርተዋል ። አመራሩ “በሀገሪቲ በዚህ ደረጃ ለሚታየው ውድቀት ተጠያቂው ሲቪል ሰርቪሱ “ ሲል፣ ሰራተኛው ደግሞ ለውድቀቱ ተጠያቄው ሲቪል ሰርቪሱ ሳይሆን አመራሩ ነው “ በማለት ተከራክሯል። ሰራተኛውን ካስገረሙት ሹመቶች መካከል የዞን ማህበራት ሃላፊ ሆና ...

Read More »

ገዢው ፓርቲ በአማራ ክልል ያለውን ተቃውሞ መቆጣጠሩን ቢያስታውቅም ተቀባይነት አላገኘም

ጥር ፳፫ (ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደሴ ከተማ ከጥር 22 ቀን 2009 ዓም ጀምሮ “ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ” በሚል ሰበብ የፌደራል ባለስልጣናት እና ሌሎች የኢህአዴግ አባላት በተገኙበት በመካሄድ ላይ ባለው ስብሰባ ላይ፣ ገዢው ፓርቲ በአማራ ክልል በተለይም በጎንደርና በጎጃም ተነስቶ የነበረውን ህዝባዊ አመጽ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉን ለተሰብሳቢዎች ቢናገሩም፣ መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን ያንን እንደማያመልክት ተሰብሳቢዎች ...

Read More »

ዩኒሴፍ በምግብ እጥረት ለሚሰቃዩ የኢትዮጵያ ህጻናት ለመርዳት ጥያቄ አቀረበ

ጥር ፳፫ (ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም ሕጻናት አድን ድርጅት ዩኒሴፍ እ.ኤ.አ. 2017 አዲሱ ዓመት የኢትዮጵያዊያን ሕጻናት ሕይወት ለማትረፍ 110 ሚሊዮን 500 ሺ የአሜሪካ ዶላር ተጨማሪ አፋጣኝ እርዳታይስፈልገኛል ብሎአል። ከዚህ እርዳታ ውስጥ 17.3 ሚሊዮን ዶላር ለስደተኞች እገዛ ይውላል። 9.2 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ሕጻናት እና ቤተሰቦቻቸውን የተመጣጠነ ምግብ፣ የጤና፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃ፣ ለትምህርት እና ለቀጣይ ማኅበራዊ ...

Read More »

በአዲስ አበባ የተገነቡ ጥቂት ቤቶች ለቤት ፈላጊዎች ሊተላልፉ አልቻሉም ተባለ

ጥር ፳፫ (ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስአበባ የቤቶች ልማት መርሃግብር አንዱ በሆነውና 40 በ60 እየተባለ የሚታወቀው ፕሮግራም ከ160 ሺ በላይ ሕዝብ ተመዝግቦ ቤቱን ለማግኘት እየተጠባበቀ ቢሆንም፣ የከተማው አስተዳደር የገነባቸውን ጥቂት ቁጥር ያላቸው ቤቶቹን ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ለማስተላለፍ እንዳልቻለ ተመዝጋቢዎች ለዘጋቢያችን ገለጹ፡፡ አስተዳደሩ የ2007 ምርጫን ተከትሎ 1 ሺ 200 ገደማ ቤቶችን አስተላልፋለሁ በሚል ቃል የገባ ቢሆንም፣ ምርጫው ካለፈ ...

Read More »

በአዲስ አበባ በ13 ወረዳዎች የሚኖሩ ዜጎች ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብተናል ይላሉ

ጥር ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ከወረዳ አንድ እስከ ወረዳ 13 ባሉ አካባቢዎች በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቤታቸው እንደሚፈናቀሉ ከተነገራቸው በሁዋላ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብተዋል። ነዋሪዎች እንደገለጹት ከአራት ቀናት በፊት “ባለስልጣናቱ መሬቱ ለአረንጓዴ ልማት ይፈለጋል” በሚል ቤታቸው እንደሚፈርስባቸው ሰብስበው ነግረዋቸዋል። ይህን ተከትሎም ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጥሯል። ለረጅም ጊዜ የኖርንበትን ቀዬ ትለቃላችሁ በመባላችን ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብተዋል ...

Read More »

በኢትዮጵያ ስለተከሰተው ድርቅ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ

ጥር ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምስራቃዊ የኢትዮጵያ አካባቢዎች አዲስ ድርቅ መከሰቱንና 5.6 ሚሊዮን ዜጎች አፋጣኝ እርዳታ ካላገኙ የከፋ ሰብዓዊ ቀውስ ሊፈጠር ይችላል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስጠንቅቋል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ቀውስ ባለስልጣን ስቴፈን ኦብሪን በቀጠናው በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ባደረጉት ጉብኝት ሁኔታውን ሲገልፁ ”እዚህ አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በሕይወት ለመቆየት ፈታኝ በሆነ ትንቅንቅ ውስጥ ናቸው። ...

Read More »