Amsterdam

ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ከባንክ አክሲዮን ለማስወጣት የተወሰደው እርምጃ በግል ባንኮች ላይ ስጋት አሳደረ፡፡

የካቲት ፪ ( ሁለት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጥቅምት 22 ቀን 2009 ዓ.ም ባወጣው መመሪያ የኢትዮጵያዊያን ዜግነት የሌላቸው ግለሰቦች በባንኮችና የመድን ሽፋን ሰጪ ኩባንያዎች ውስጥ ያላቸውን የባለቤትነት ድርሻ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2009 ዓ.ም እንዲመልሱ ባዘዘው መሠረት በተለይ አንዳንድ ባንኮች የካፒታል አጣብቂኝ ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ የዘርፉ ባለሙያዎች አስጠነቀቁ፡፡ ባለሙያዎቹ እንደሚሉት አንዳንድ ባንኮች በርካታ ቁጥር ያላቸው ...

Read More »

“ በተለይ ጊዜው ለትግራይ አስተማማኝ አይደለም” ሲል ብአዴን አስታወቀ

የካቲት ፩ ( አንድ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብአዴን ሰሞኑን በክልሉ የተደረጉ ስብሰባዎችን በማስመለክት ባወጣው የማጠቃለያ ሪፖርት ላይ “ የሰላም መናጋት ለገዢው ፓርቲ አመራሮች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ህብረተሰብ የሚተርፍ ነው። በተለይ ለትግራይ ጊዜው አስተማማኝ አይደለም” ሲል ገልጿል። “የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ማበር ካልቻለ በስተቀር፣ ጊዜው አስተማማኝ” አይደለም የሚለው ብአዴን፣ የክልሉ ህዝብ በህወሃት ላይ ያለውን ጥላቻ በሪፖርቱ ላይ ...

Read More »

የኦሮምያ ከተማ ልማት ቢሮ ሰራተኞች በጥልቅ ተሃድሶ ስም የቀረበውን ሪፖርት ተቃወሙ

የካቲት ፩ ( አንድ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሁለት ሳምንት በፊት በአዳማ ከተማ ቶኩማ ሆቴል የተሰበሰቡት የኦሮምያ ከተማ ልማት ቢሮ ሰራተኞች፣ በአዲሱ ሃላፊያቸው የቀረበውን ሪፖርት አጣጥለውታል። ሃላፊው ፣” መንግስት ደሞዝ በመጨመር፣ ቤት ሰርቶ በመስጠትና የኑሮ ሁኔታችሁ እንዲሻሻል ቢያደርግም ፣ እናንተ ግን በተቀራኒው የምትሰሩት ስራ መንግስትን የሚያስወቅስ በመሆኑ ይህ እንዳይቀጥል ቃል መግባት አለባችሁ” ብለው ሲናገሩ፣ ሰራተኞቹ በበኩላቸው “ እርስዎ ...

Read More »

አወዛጋቢው የትራፊክ ህግ ጸድቆ በስራ ላይ ዋለ

የካቲት ፩ ( አንድ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በየካቲት ወር 2008 ዓ.ም በአዲስአበባ ከተማ ተግባራዊ ሊሆን ሲል በታክሲ አሽከርካሪዎች የሥራ ማቆም አድማ መንግሥት ተገዶ አፈጻጸሙ እንዲራዘም የወሰነው የትራፊክ ደህንነት ደንብ ቁጥር 208/2003 ጥቂት ማሻሻያዎችን በማድረግ ሰሞኑን ጸድቆ በሥራ ላይ ውሎአል፡፡ ደንቡ በተደጋጋሚ ጥፋት የሚገኝባቸው አሽከርካሪዎችን መንጃ ፈቃድ እስከመንጠቅ የሚደርስ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ሲሆን ፣ ባለፈው ዓመት ተግባራዊ ሊሆን ...

Read More »

ወደ የመን ከሚሰደዱት ስደተኞች ውስጥ 80 በመቶ ኢትዮጵያውን መሆናቸውን ተመድ አስታወቀ

የካቲት ፩ ( አንድ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለዓመታት በእርስበርስ ጦርነት ወደምትታመሰው የመን የሚሰደዱ ስደተኞች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የሚገልጸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽነር /UNHCR/ ፣ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ከገቡት 87 000 ስደተኞች መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት ወይም ከ69 600 በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ናቸው ብሎአል። ቀጥሎ ያለውን ደረጃ የሚይዙት ሶማሊያውያን ስደተኞች ናቸው። በኢትዮጵያ ተከታታይ እድገት ተመዘገበ እየተባለ ...

Read More »

በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዳይነሳ “ኮማንድ ፖስቱ” አስጠነቀቀ

ጥር ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል የሚታየውን የጸጥታ ሁኔታ ለመገምገም ከፌደራል የተላከው የኮማንድ ፖስቱ አጣሪ ቡድን ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቢነሳ ህዝቡ በቀጥታ በመንግስት ላይ ከእስካሁኑ የከፋ ጥቃት ሊሰነዝር ይችላል ሲል አስጠንቅቋል። ኮማንድ ፖስቱ “ የክልሉን ህዝብ ገትቶ የያዘው መሳሪያ ነው” ያለ ሲሆን፣ አዋጁ ቢነሳ ከእስካሁኑ በከፋ ሁኔታ አመፁን ለማስቀጠል ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠናል” ብሎአል፡፡ ለአንድ ወር ...

Read More »

ለኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ የተላከውና በአገዛዙ ላይ የቦንብ ናዳውን የሚያወርደው የመምህራን ግምገማ ሪፖርት ኢሳት እጅ ገባ

ጥር ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቁጥር ብአዴን/ማዕ.ኮ/2131ሪ በቀን 23/05/2009 ዓ/ም ለኢህአዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት እንዲደርስ የተጠቃለለው የጥልቅ ትሃድሶ የመምህራን መድረክ ማጠቃላያ ሪፓርት ኢሳት እጅ ገብቷል፡፡ ይህ በኢሜል የተላከው ሰነድ እንደሚያሳያው ከ8 ሺ በላይ መምህራን በዞን ደረጃ ቀጠና ተለይቶ ውይይት አድርገዋል፡፡ በአምስት ዋና ዋና ምድቦች አርዕሰተ ጉዳዮች እየተመራ የተካሄደ ሲሆን ኢህአዴግ አደጋ ውስጥ መግባቱን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ መምህራን ስለድህነት፣ ...

Read More »

በትግራይና አማራ ድንበር አካባቢ የተነሳውን ግጭት እንዲያዩ ከተመረጡት የኮሚቴ አባላት መካከል አንደኛው በድጋሜ ታፈኑ

ጥር ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ እና በትግራይ ድንበር አካባቢ አወዛጋቢ ከሆኑት ቦታዎች መካከል አንዱ የሆነውንና የትግራይ ክልል የእኔ ነው በማለት ወደ ክልሉ እንዲገባ የሚጠይቀውን ግጨው እየተባለ የሚጠራውን ቦታ ሁኔታ ለማየት ከተመረጡት የኮሚቴ አባላት መካከል አቶ ዋኘው ደሳለኝ ጥር 26 ቀን 2009 ዓም ማክሰኚት ላይ በድጋሜ በህወሃት የደህንነት አባላት ታፍነው ተወስደዋል። ግለሰቡ ያሉበት ቦታ እስካሁን አልታወቀም። ኢህአዴግ ...

Read More »

በምስራቅ አፍሪካ የርሃብ አደጋው እንደ አዲስ ማገርሸቱን ተከትሎ ሰብዓዊ ቀውስ ሊፈጠር ይችላል ሲል የዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት አስጠነቀቀ።

ጥር ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቀጠናው በተከሰተው አዲሱ ድርቅ ምክንያት ቁጥራቸው 11.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች ለከፍተኛ የርሃብ አደጋ ተጋላጭ ሆነዋል። እንደ ድርጅቱ መግለጫ በኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ እና ኬንያ አፋጣኝ የረድኤት እርዳታ ጠባቂ ዜጎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን እና የድርቁ ደረጃ በርሃብ መለኪያ Integrated Phase Classification (IPC) ከሶስት ነጥብ በላይ መሆኑን አስታውቋል። በሶማሊያ 2.9 ሚሊዮን፣ በኬንያ 2.7 ...

Read More »

በኢትዮጵያ በአንድ አመት ውስጥ ከአራት ሺ በላይ ዜጎች በተሽከርካሪ አደጋ ሕይወታቸውን ማጣታቸውን የትራንስፖርት ሚንስቴር ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርቱ አስታወቀ።

ጥር ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ዓመት ውስጥ 2008 ዓ.ም ብቻ በመላው ኢትዮጵያ ባጋጠመ ከተሽከርካሪ ጋር ተዛማጅ በሆኑ በደረሱ አደጋዎች በድምሩ 4 ሽህ ዜጎች ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን ከ10 ሺህ በላይ ዜጎች ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት አጋጥሟቸዋል። ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ የትራፊክ አደጋ ከዓመት ወደ ዓመት እየተባባሰ መምጣቱን እና አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አገራት ጥቂት ...

Read More »