የካቲት ፮ ( ስድስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህወሃት/ኢህአዴግን አገዛዝ በሁለገብ ትግል ለማስወገድ እየታገለ ያለው አርበኞች ግንቦት7 ባለፈው ቅዳሜና እሁድ 46 ከተሞችን ያሳተፈ ስብሰባና የድጋፍ ማሰባሰብ ስራ መስራቱን ታውቋል። የአርበኞች ግንቦት7 ሊ/መንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በምስል ስልክ በተለያዩ አህጉራት ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን በቀጥታ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ ከሁሉም አካባቢዎች ለተነሱላቸው ጥያቄዎችም መልስ ሰጥተዋል። ፕ/ር ብርሃኑ ድርጅታቸው ስላለበት ወቅታዊ ሁኔታ፣ ከተለያዩ ድርጅቶች ...
Read More »Amsterdam
ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው የዋስትና መብት ተከለከለ
የካቲት ፮ ( ስድስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሕግ አግባብ ውጪ የሸብር ክስ ተመስርቶበት በእስር ላይ የሚገኘው የነገረ-ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው የዋስትና መብት ተከልክሏል። ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ያቀረበውን የዋስትና መብት ጥያቄ የተመለከተ ሲሆን፣ ”ተከሳሹ በዋስ ቢወጣ በሕጋዊም ሆነ በሕገ ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ ስለሚችል የዋስትና ጥያቄውን አልተቀበልነውም” የሚል ውሳኔ ሰጥቷል። ይግባኝ ...
Read More »የሶማሊ ልዩ ሃይል ታጣቂዎች በኦሮምያ ፖሊሶች ላይ ጥቃት ፈጸሙ
የካቲት ፫ ( ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ የኢሳት ወኪል እንደዘገበው ከፍተኛ የህወሃት ድጋፍ ባላቸው በሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ ሙሃመድ የሚመራው ልዩ ሃይል በኦሮሞያ ክልል ከባቢሌ በ18 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በሚገኙት በአውሸሪፍና ደረሬ ቀበሌዎች በመግባት ከኦሮምያ ፖሊስ ጋር የተዋጋ ሲሆን ፣ በውጊያውም አንድ የኦሮምያ ፖሊስ ሲገደል ፣ ሁለት ፖሊሶች ተማርከው ተወስደዋል። ይሁን እንጅ በሁሉቱ ሃይሎች መካከል ...
Read More »ብአዴን የሚያስተዳድራቸው ሰባቱ ድርጅቶች ኪሳራ ውስጥ ገብተዋል ተባለ
የካቲት ፫ ( ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል ብአዴን ያቋቋማቸው ከ16 በላይ የልማት ድርጅቶች ያሉ ሲሆን፣ 7ቱ በከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ ናቸው። ድርጅቶቹ በመነሻ ካፒታል በአምስት ነጥብ ሰባት ቢልየን ብር ከህዝብ በጀት ተበድረው ቢቋቋሙም፣ የብአዴን ባለስልጣናት እንደልባቸው የሚዘርፏቸው ተቋማት መሆናቸውን ምንጮች ይገልጻሉ። ለዝርዝሩ ፋሲል የኔዓለም በኮንስትራክሽን ፣ በማማከር ፣ በማሽነሪ ኪራይ ፣ በፋብሪካ ምርቶች ፣ በውሃ ጉድጓድ ...
Read More »አቃቢ ህግ ነጻ መረጃ አላገኘሁም በሚል የፈታቸው ባለስልጣናት በድጋሜ ታሰሩ
የካቲት ፫ ( ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በ2007 ዓም በሃመር ወረዳ ተነስቶ የነበረውን ተቃውሞ ተከትሎ ተቃውሞ ባሰሙ ወጣቶች ላይ አፋጣኝ እርምጃ ባለመውሰድ ወይም እንዳይወሰድ በማድረግ ለወጣቶቹ በቀጥታም ሆነ ተዘዋዋሪ ድጋፍ ሰጥታችኋል ተብለው ታስረው የነበሩ የወረዳው ባለስልጣናት መረጃ የለም በሚል አቃቢ ህግ ክስ እንደማይመሰርት ማስታወቁን ተከትሎ ባለስልጣኖቹ ቢፈቱም፣ በድጋሜ እንዲታሰሩ ተደርጓል። ፋይሉን የመረመሩ ዐቃቢያነ ህጎች ደግሞ ከሥራና ደመወዝ ...
Read More »በመላ ሃገሪቱ በሚታየው የነዳጅ እጥረት ተጓዦች ከታሪፍ በላይ በመክፈል መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡
የካቲት ፫ ( ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በበርካታ የሃገሪቱ ከተሞች የሚታየው የነዳጅ እጥረት ተባብሶ በመቀጠሉ ምክንያት ተጓዦች ከመደበኛ ታሪፍ በላይ እንዲከፍሉ እየተገደዱ መሆኑን ለኢሳት ገለጹ፡፡ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት ከወራት በፊት የተከሰተው የነዳጅ እጥረት ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ በተለይ በአማራ ክልሏ በበርካታ ከተሞች የቤንዚን አገልግሎት ከተቋረጠ ሳምንታት መቆጠሩን አሽከርካሪዎች ተናግረዋል። በባህር ዳር፣ጎንደር ፣ወልዲያና ደሴ በመሳሰሉት ትልልቅ ከተሞች የነዳጅ አገልግሎት ...
Read More »በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያ ኤንባሲ ውስጥ በመግባት ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ
የካቲት ፫ ( ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በሱዳን ውስጥ ለሚፈጸምባቸው ኢሰብዓዊ የመብት ጥሰቶች ኤንባሲው ለስደተኞች ምንም ዓይነት እገዛ አለማድረጉን በመቃወም ኤንባሲው ግቢ ውስጥ በመግባት በሰላማዊ ሰልፍ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ኢትዮጵያውያኑ ኤንባሲው አካባቢ ያሉ የደህንነት አባላት በቪዲዮ ምስል እንዳይቀርጹ ካሜራዎችን በመቀማት ለመከልከል ሙከራ አድርገዋል። ኢትዮጵያን ስደተኞች በሱዳን በኡንዱርማን እና በተለያዩ ...
Read More »እንደ ኦሮምያና አማራ ሁሉ የደቡብ ክልል የመንግስት ሰራተኞችም በጥልቅ ተሃድሶ ስም የቀረበውን ሪፖርት ተቃወሙ
የካቲት ፪ ( ሁለት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን በጂንካ ከተማ በዞኑ የሚገኙ ሰራተኞች ጥልቅ ተሃድሶ ለማድረግ በሚል ከሰኞ ጥር 29 ቀን 2009 ዓም ጀምሮ በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ አዳራሽ እያደረጉት ባለው ስብሰባ ላይ ፣ ለውይይት መነሻ ሆኖ የቀረበውን ጽሁፍ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርገውታል። የውውይት መነሻ ጽሁፉ በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ከቀድሞ ስርአቶች ጋር ሲነጻጻር የተሻለ ድል ...
Read More »በሚዳ ወረሞ የቅስቀሳ ወረቀቶች ተበትነው ማደራቸውን ተከትሎ ወጣቶች ታሰሩ
የካቲት ፪ ( ሁለት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ሬማ ንኡስ ወረዳ ህዝቡ ለመብቱ እንዲነሳ የሚያሳስቡ በራሪ ወረቀቶች ተብትነዋል። ይህንን ተከትሎ ወጣት አብዩ ሰኢድና ወጣት ግርማ ፈሊ በፖሊሶች ተይዘው ወደ እስር ቤት የተወሰዱ ሲሆን ግርማ ማምሻውን መፈታቱ ታውቋል። ወረቀቱ ከወረዳ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ህዝቡ ለተቃውሞ ሰልፍ እንዲወጣ የሚቀሰቅስ ቢሆንም፣ “በጎንደር የፈሰሰው የህዝብ ደም በከንቱ ...
Read More »በጅቡቲ መስመር ፍተሻው ተጠናክሮ ቀጥሎአል
የካቲት ፪ ( ሁለት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከጅቡቲ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ እቃዎችን የሚያመላልሱ የከባድ ተሽከርካሪ ሹፌሮች እንደተናገሩት ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ በአዋሽ 7 ኬላ ላይ ከፍተኛ ፍተሻ እየተካሃደ በመሆኑ በስራቸው ላይ ችግር እየፈጠረ ነው። በአሁኑ ሰአት መኪኖች ከ3 እስከ 5 ኪሜትሮች የሚደርስ ሰልፍ ሰርተው ለመፈተሽ ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ሲሆኑ፣ ፍተሻው ከዚህ ቀደም ከነበረው የተጠነከረ ነው ይላሉ። ...
Read More »