(Sept. 8) የፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ፤ አቶ ብዙአየሁ ወንድሙ፤ የግድያ ዛቻ እንደደረሰበት ሲናገር፤ እንዳትታም የተከለከለችውን ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ሕትመትና ህልውና ለመቀጠል፤ “ዘመቻ ነፃነት” የተሰኘ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን በአዲስ አበባ የሚገኙት የጋዜጣዋ ዋና አዘጋጆች ገለፀ። ምክትል ዋና አዘጋጁ አቶ ብዙአየሁ ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ፤ በብርሃንና ሰላም እምቢታ ላለፉት ሁለት ሣምንታት እንዳትታተም የተከለከለችውን ጋዜጣ ህልውና ለመቀጠል፤ ፍትህ ሚኒስትርን ጨምሮ፤ ለተለያዩ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
3.7 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል
(Sept. 8) ድርቅ አሁንም ለኢትዮጵያ ፈተና ሆኖ እንደሚቀጥልና፤ ከነሀሴ እስከ መጪው ታህሳስ ድረስ፤ 3.7 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው፤ የግብርና ሚኒስቴር አቶ ምትኩ ካሳ ገለጡ። ከነሀሴ በፊት በነበሩት ስድስት ወራት ውስጥ፤ የምግብ ተረጂዎች ቁጥር 3.2 ሚሊዮን የነበረ ሲሆን፤ በቀጣዮቹ 4 ወራት ግን የተረጂዎች ቁጥር 16 በመቶ ጨምሮ፤ በአሁኑ ሰዓትና እስከሚቀጥለው ታህሳስ መጨረሻ፤ የተረጂዎች ቁጥር 3.7 ሚሊዮን እንደሚደርስ፤ የግብርና ሚኒስትሩ መናገራቸውን ...
Read More »በኢህአዴግ ውስጥ የስልጣን ሽኩቻ ቀጥሏል
(Sept. 9) አቶ መለስ ዜናዊን ለመተካት፤ በኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አባላት መካከል የተፈጠረው ሽኩቻ እንደቀጠለ ሲሆን፤ በመጪው የኢትዮጲያ አዲስ አመት የመጀመሪያ ሳምንት፤ 180 የኢህአዴግ ማእከላዊ ምክር ቤት አባላት፤ ጉዳዩን እልባት ለመስጠት እንደሚሰበሰቡ ለማወቅ ተችሏል። የ4 ፓርቲዎች ግንባር የሆነው ኢህአዴግ፤ ከያንዳንዱ ፓርቲ የተውጣጡ 45 የማእከላዊ ም/ቤት ዓባላት፤ በድምሩ 180 የምክር ቤት አባላት ተሰብስበው ላለፉት ሁለት ሳምንታት ሲያከራክር የቆየውን፤ የኢህአዴግ ሊ/መንበርና፤ የጠ/ሚ/ርነት ቦታን ...
Read More »በኢትዮጽያ የዋጋ ንረት በ30 በመቶ አሻቀበ
ጳጉሜን ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የነሐሴ ወር 2004 ዓ.ም የ12 ወራት ተንከባላይ አማካይ አገራዊ አጠቃላይ የዋጋ ግሸበት በ30 ነጥብ 2 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ይፋ አደረገ ኤጀንሲው ትላንት ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚጠቁመው ከ12 ወራቱ አጠቃላይ አገራዊ የዋጋ ግሸበት ውስጥ የምግብ ዋጋ ግሸበት 36 ነጥብ 5 በመቶ፣ምግብ ነክ ያልሆኑ 20 ነጥብ 9 በመቶ ጭማሪ ሲያሳይ ከምግብ ውስጥ ...
Read More »በኢትዮጵያ ውስጥ ፈጣን ለውጥ ለማምጣት አስፈላጊው ስራ እየተሰራ ነው ሲሉ የግንቦት7 አመራሮች ተናገሩ
ጳጉሜን ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የግንቦት7 ከፍተኛ የአመራር አባላት የሆኑት አቶ አበበ ቦጋለ እና ዶ/ር ታደሰ ብሩ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጡት፣ ንቅናቄው በስልጣን ላይ ያለውን ሀይል አስገድዶ ከተቻለ ወደ ድርድር ካልተቻለም ለማስወገድ፣ ፈጣን የሆነ ውጤታማ ስራ የሚሰራበትን ዝግጅት እያደረገ ነው። ገዢው ፓርቲ ህልውናውንም አገሪቱንም ከጥፋት ለመከላከል በአፋጣኝ የፖለቲካ ለውጥ በማድረግ ሁሉም በእኩል የሚሳተፉበት የሽግግር ጊዜ አስተዳደር እንዲመሰረት ...
Read More »ኢህአዴግ የዩኒቨርስቲ መምህራንን ለስብሰባ ጠራ
ጳጉሜን ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ምንጮቻችን እንደገለጡት መምህራኑ ከመስከርም ሶስት ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚቆይ ስብሰባ ላይ ይሳተፋሉ። የስብሰባው አጀንዳ ባይታወቅም የአገዛዙ ተተኪ አመራሮች ልክ አቶ መለስ ወደ ስልጣን ሲመጡ እንዳደረጉት ሁሉ ራሳቸውን ከምሁራን ጋር በማስተዋወቅ፣ ተቀባይነት ለማግኘት ነው የሚል መላምት አለ። በተለያዩ አገራት የሚገኙ የዩኒቨርስቲ መምህራን በሚሳተፉበት በዚህ ስብሰባ ላይ ምሁራኑ በአገራቸው መጻኢ እድል ላይ ገንቢ አስተያየቶችን ...
Read More »“ወደ ሥልጣን የመጣው አመራር ባለፈው መንገድ ሊቀጥል አይችልም” ሲሉ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ አስጠነቀቁ
ጳጉሜን ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “በቀጣይ በኢትዮጵያ የተሸለ ነገር የሚመጣው፤ የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ ተገናኝተው፣ በክብ ጠረጴዛ ዙሪያ ተመካክረው መፍትሔ ማምጣት የሚችሉበት ዕድል ሲፈጠር ብቻ ነው።” ሲሉ አቶ ቡልቻ ወደ ሥልጣን እየመጣ ላለው አዲስ አመራር ቡድን መልዕክት አስተላለፈዋል። የቀድሞው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀ-መንበር ይህን ያሉት፤ዛሬ ለንባብ ከበቃው ሰንደቅ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው። “ከጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት ...
Read More »ኢትዮጵያዊው አርሶአደር የእንግሊዝን መንግስት ሊከስ ነው
ጳጉሜን ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አንድ ኢትዮጵያዊ አርሶአደር በእንግሊዝ የገንዘብ ድጋፍ የተቋቋመ ድርጅት የሰብአዊ መብቴን ጥሶብኛል ሲሉ ነው ክስ ለማቅረብ የተነሳሱት ። ሚስተር ኦ የተባሉት ሰው ለእንግሊዝ ጠበቆች እንደተናገሩት በመንደር ምሰረታ መርሀ ግብር የተነሳ ከመሬታቸው ተፈናቅለዋል፣ ተገርፈዋል እንዲሁም አስገድዶ መድፈሮች ሲፈጸሙ ተመልክተዋል። የአርሶአደር ኦ ጠበቆች እንዳሉት የመንደር መስረታው መርሀ ግብር ከእንግሊዝ አለማቀፍ የልማት ዲፓርትመንት የገንዘብ ድጋፍ አግኝቷል። የልማት ...
Read More »በአቶ በረከት ስምኦንና በህወሀት መካከል ያለው ፍጥጫ ተካሯል
ነሀሴ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሁለት ሳምንት በፊት አቶ በረከት ስምኦን ፣ የአቶ መለስ ዜናዊ የቀብር ስነስርአት እንደተፈጸመ ፣ የአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የጠቅላይ ሚኒስትርነትን ስልጣን ፓርላማው በአስቸኳይ ተጠርቶ ያጸድቀዋል የሚል መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ የመንግስቱ የመገናኛ ብዙሀን አቶ ሀይለማርያምን ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር እያሉ እስከመጥራት ደረሱ። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረትም አቶ ሀይለማርያም እስከ 2007 ዓም የጠቅላይ ሚኒሰትርነቱን ቦታ ...
Read More »በአማራ ክልል የመንግስት ስራተኛዉ የወር ደሞዙን እንዲለግስ ተጠየቀ
ነሀሴ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰራተኛው ለአባይ ግድብ ማሰሪያ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀዱትን ልማት ለማስቀጠል በሚል ሰበብ የወር ደሞዙን በግድ እንዲለግስ እየተገደደ መሆኑን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል። የመንግስት ሰራተኛዉ በኑሮ ዉድነት እየተንገላታ ባለበት ባሁኑ ወቅት እንዲህ አይነቱን ውሳኔ ማስተላለፍ እጅግ የሚዘገንን ነው በማለት አንድ የመንግስት ሰራተኛ ምሬታቸውን ለኢሳት ገልጠዋል። ከዚህ ቀደም ለአባይ ግድብ ማሰሪያ የከፈሉት ገንዘብ አራቁቷቸው መሄዱን የገለጡት ...
Read More »