መስከረም ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሙስሊሞቹ በፌዴራል ፖሊሶች ክፉኛ የተደበደቡት፤ <መመራት የምንፈልገው ራሳችን በመረጥነው መጂሊስ ነው!፤ መንግስት በሀይማኖታችን ጣልቃ አይግባብን!>በማለት ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ በማንሳታቸው ነው። ቪዲዮውን ለኢሳት ያደረሱ አንድ የደሴ ነዋሪ<በአወሊያ ከተጀመረ ዘጠኝ ወራት ያስቆጠረው የሙስሊሞች መብት የማስከበር እንቅስቃሴ አንድም ጊዜ ከህጋዊና ሰላማዊ ማዕቀፍ አፈንግጦ የታየበት ጊዜ ባይኖርም፤መንግስት ግን ሲፈልግ መሪዎቻችንን ያስራል፤ሲያሻው ይደበድበናል>>ብለዋል። <<ሌላው ቢቀር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
አቶ መለስ በመጨረሻው የስልጣን እድሜያቸው በፕሮፓጋንዳ ሰራተኞቻቸው ተስፋ ቆርጠው እንደነበር ታወቀ
መስከረም ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የኢህአዴግ ምንጮች እንደገለጡት ኢህአዴግ በፕሮፖጋንዳው መስክ ለደረሰበት ኪሳራ አቶ መለስ አቶ በረከትን ተጠያቂ አድርገው ነበር። በአንድ የግንባሩ ስብሰባ ላይ በመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሠራተኞች ብቃት ማነስ የተበሳጩት አቶ መለስ ‹‹እዚህ ተቋም ላይ ከሰበሰብካቸው ሰዎች ይልቅ ያ የግል ጋዜጣ የሚያዘጋጀው ልጅ የበለጠ ኮሚትመንት አለው፣ እሱ የሚሰራውን ያውቃል፣ ያንተ ሰራተኞች የሚሰሩትን አያውቁም›› በማለት አቶ ...
Read More »የጋዜጠኛ ግሩም ተክለሐይማኖት ደህንነት አደጋ ላይ ነው ተባለ
መስከረም ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአስኳልና ሳተናው ዋና አዘጋጅ የነበረው በየመን አገር በስደት ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሐማኖት በየመን ፖሊሶች እየተዋከ ነው። ጋዜጠኛው ጳጉሜ 3 ቀን 2004 ዓም ቤቱ በሌሊት በፖሊስ እንደተፈተሸበት ለኢሳት ተናግሯል:: ጋዜጠኛ ግሩም ችግሩን ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ቢያመለክትም ጽሁፍ መጻፉን እንዲያቆምና ቤት እንዲቀይር ከመጠየቅ ውጭ ችግሩን የሚያቃልል መልስ ሊሰጠው አልቻለም፡። ጋዜጠኛ ግሩም ኢትዮጵያውያን ...
Read More »በቁም እስር ላይ የነበሩ ሶስት ጄኔራሎች ተለቀቁ
መስከረም ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ ዜናዊ መታመምን ተከትሎ በገዢው ፓርቲ ውስጥ የተፈጠረው መከፋፈል፣ ጠቅላይ ሚንስትሩ መሞታቸው ከተረጋገጠና ከተገለጸ በኋላም የተባባሰ ደረጃ ላይ መድረሱ የኢህአዴግ የዜና ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ በዚህ ክፍፍል ላይ እስካሁን ድረስ አቋማቸውን በግልጽ ካላሳዩት የሀገሪቱ ከፍተኛ ጄነራሎች ውስጥ የተወሰኑት እንደተቃወሙትም ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ተቃውሟቸውን በይፋ ካሰሙት ውስጥ ሦስት ጀነራሎች ከሰኞ ጠዋት ጀምሮ በቢሯቸው የቁም እስረኛ ተደርገው ...
Read More »በመጪው አርብ ለሚካሄደው የሙስሊሞች ተቃውሞ ወረቀቶች እየተበተኑ ነው
መስከረም ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ መንግሥት የኢትዮጵያ ሙስሊም ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትንና የመስኪድ ኡላማዎችን የክስ ሂደት በመጪው ጥቅምት 2 ቀን 2005 ዓ.ም ፒያሳ በሚገኘው በአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለማድረግ ጊዜ ቀጠሮ መያዙ መታወቁን ተከትሎ፤ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በመጪው የዓርብ /ጁምዓ/ ጸሎት በየመስኪዱ የተጠናከረ የተቃውሞ ትይንት ለማድረግ ዝግጅት ጀምረዋል። ባለፈው ሳምንት ህዝበ ሙስሊሙ አራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ...
Read More »የነ አቶ አንዷለም አራጌ ንብረት ታገደ
መስከረም ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሀሰት የሽብር ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት የነ አቶ አንዷለም አራጌ የአቶ እስክንድ ነጋ ንብራት ሊወረስ እንደሆነ ታውቋል:: የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ባስተላለፈው ውሳኔ በአቶ አንዷአለም ስም የተመዘገበው የቤት መኪና በአቶ እስክንድር ነጋ ስም የተመዘገበው የተመዘገበው ባለ አንድ ፎቅ ቤትና በውርስ በስማቸው የተመዘገበ ቤት እንዲታገድ ተደርጓል:: በውጭ በሚገኙት በአቶ አበበ በለው ባለቤት ...
Read More »ኢህአዴግ በአገራዊ ፖሊሲዎችና ውሳኔዎች ዙሪያ ለመምህራን ገለጻ እየሰጠ ነው
መስከረም ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ መንግሥት ከቅዳሜ መስከረም 5 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በሀገሪቱ የሚገኙ የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራንን ለትምህርት ጥራት ምክክር ብሎ ለአንድ ሣምንት የሚቆይ ሥልጠና በየትምህርት ቤቱ በመሰብሰብ ላይ ይገኛል፡፡ ቅዳሜ እና እሁድን በትምህርት ጥራት ላይ ያወያዩት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኃይለሥላሴ ፍሰሃ ናቸው ሲል ለዘጋቢያችን የገለጸው አንድ የማህበራዊ ...
Read More »አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን በይፋ ጠቅላይ ሚኒስትር ለማድረግ ሩጫው ቀጥሎአል
መስከረም ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰሞኑን በኢህአዴግ ምክር ቤት አባላት በከፍተኛ ደረጃ የተሾሙትን አቶ ሀለማርያም ደሳለኝንና ምክትላቸውን አቶ ደመቀ መኮንንን ጠቅላይ ሚኒሰትር አድርጎ ለማሾም ሽርጉዱ መቀጠሉን የኢሳት ምንጮች ገልጠዋል። አቶ በረከት ስምኦን ከፍተኛ ድል እንዳገኙ በተነገረበት በዚህ ሹመት፣ አቶ ሀይለማርያምን በያዝነው ሳምንት መጨረሻ ወደ ፓርላማ አቅርቦ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ በይፋ ለማሾም የሩጫ ዝግጅት እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል። የአገሪቱ ...
Read More »የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ስለታሰሩት የሙስሊም አመራሮች የሰጠውን መግለጫ የታሳሪዎቹ ቤተሰቦችና ሙስሊሞች ተቃወሙት
መስከረም ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአምባሳደር ጥሩነህ ዜና የሚመራው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከሙስሊሞች መብት የማስከበር እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ስለታሰሩት የሙስሊም አመራሮች የሰጠውን መግለጫ የታሳሪዎቹ ቤተሰቦችና ሙስሊሞች ተቃወሙት። ኮሚሽኑ ከታሳሪዎች የወንጀል ምርመራ ሀላፊዎች የነገሩትን ቃል እንደወረደ ነው መግለጫ ብሎ የሰጠው። ከመብት ማስከበሩ ትግል ጋር በተያያዘ የታሰሩት ሙስሊሞች ከ 100 በላይ መሆናቸውን ቤተሰቦቻቸው እየገለጹ ባለበት ሁኔታ፤ ኮሚሽኑ <የታሰሩት 30 ...
Read More »ዘመቻ ነጻነት መሰረታዊ የመብት ጥያቄዎችን ይዞ አንደሚነሳ የፍኖተነጻነት ዋና አዘጋጅ ተናገሩ
መስከረም ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአንድነት ልሳን የሆነው የፍኖተነጻነት ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ነብዩ ሀይሉ ለኢሳት እንደገለጠው የፍኖተነጻነትን የህትመት እግድ ለመቃወም የታቀደው የዘመቻ ነጻነት እንቅስቃሴ ሌሎች የመብት ጥያቄዎችን እብሮ እንደሚያነሳ ተናግሯል። ጋዜጠኛ ነብዩ በኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ የሚባሉት ጋዜጦች በሙሉ ከጨዋታ ውጭ በመሆናቸው፣ ዘመቻ ነጻነት ሰላማዊ ሰልፍ እስከ ማድረግ በሚደርስ የትግል እንቅስቃሴ መጀመሩን ተናግሯል የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ...
Read More »