ዘመቻ ነጻነት መሰረታዊ የመብት ጥያቄዎችን ይዞ አንደሚነሳ የፍኖተነጻነት ዋና አዘጋጅ ተናገሩ

መስከረም ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የአንድነት ልሳን የሆነው የፍኖተነጻነት ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ነብዩ ሀይሉ ለኢሳት እንደገለጠው የፍኖተነጻነትን የህትመት እግድ ለመቃወም የታቀደው የዘመቻ ነጻነት እንቅስቃሴ ሌሎች የመብት ጥያቄዎችን እብሮ እንደሚያነሳ ተናግሯል።

ጋዜጠኛ ነብዩ  በኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ የሚባሉት ጋዜጦች በሙሉ ከጨዋታ ውጭ በመሆናቸው፣ ዘመቻ ነጻነት ሰላማዊ ሰልፍ እስከ ማድረግ በሚደርስ የትግል እንቅስቃሴ መጀመሩን  ተናግሯል

የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የህትመት እገዳውን በመቃወም ለአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ እና ለሌሎችም የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ደብዳቤ ቢጽፉም እስካሁን ድረስ እግዱን የሚያነሳ ወይም እግዱን የሚያጸና መልስ አላገኙም።

የዘመቻ ነጻነትን ዝርዝር ሂደት ለመገናኛ ብዙሀን ይፋ ለማድረግ አለመፈለጉን የገለጠው ጋዜጠኛ ነብዩ፣ በሂደት ህዝቡን እና ጋዜጣቸው የታፈኑባቸውን ወገኖች በማስተባባር የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ማቀዳቸውን ጠቁመዋል

በኢትዮጵያ ውስጥ ከአቶ መለስ ዜናዊ ጤና ጋር በተያያዘ ባቀረቡት ዘገባ ፍትህ እና ፍኖተ ጋዜጦች እንዲታገዱ መደረጋቸው ይታወሳል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide