(ኢሳት ዲሲ– ነሃሴ 4 /2010)በሶማሌ ክልል ያለውን የጸጥታ ሁኔታ ለመቆጣጠር ወታደራዊ ዕዝ ወይንም ኮማንድ ፖስት ተቋቋመ። ከመከላከያ ሃይል ፣ከፌደራል ፖሊስ እና ከሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል የተውጣጣው ኮማንድ ፖስት በደቡብ ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል በላይ ስዩም እንደሚመራም ታውቋል። የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት በዛሬው እለት በክልሉ ጸጥታ ጉዳይ ላይ መወያየቱም ተገልጿል። የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር እና ሌሎች የፀጥታ ሃይል አዛዦች በተገኙበት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በኢትዮ-ሶማሌ ክልል አሁንም ዜጎች ወደ ሃረር ከተማ እየተሰደዱ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 4/2010)በኢትዮ-ሶማሌ ክልል ተከስቶ ከነበረው ቀውስ ጋር ተያይዞ አሁንም ዜጎች ወደ ሃረር ከተማ እየተሰደዱ ነው ተባለ። ሐረር ከገቡት ስደተኞች መካከልም ወደ አዲስ አበባ የተጓዙ መኖራቸው ታውቋል። በጅጅጋ በአብያተክርስቲያናት ተጠልለው የሚገኙት ዜጎች አሁንም ምንም አይነት እርዳታ እንዳልተሰጣቸውና ሕይወታቸው አደጋ ላይ መሆኑ ተሰምቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን የፌደራሉ መንግስት በጅጅጋ ከተማ ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ80 ሚሊየን ብር የሚበልጥ የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ኣያደረገ ...
Read More »የሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት በኦሮምያ ክልል ወረዳዎች ላይ ጥቃት ለመፈጸም ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ቀረ
የሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት በኦሮምያ ክልል ወረዳዎች ላይ ጥቃት ለመፈጸም ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ቀረ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 04 ቀን 2010 ዓ/ም ) ትናንት ነሃሴ 3 ቀን 2010 ዓም በምስራቅ ሃረርጌ መዩ ወረዳ ላይ በህዝቡ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ሞክረው በአካባቢው ህዝብና በኦሮምያ ፖሊስ ጥረት ከሽፏል። ተመሳሳይ ሙከራ ቁምቢ ወረዳ ላይ ተካሂዶ የነበረ ቢሆንም፣ ይህኛውም ጥቃት ሳይሳካ ቀረ። የሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት ...
Read More »ሰመጉ በሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞን ከህዳር 24 እስከ የካቲት 4 ቀን 2010 ዓ.ም 17 ሰላማዊ ዜጎች በፀጥታ ሃይሎች በግፍ መገደላቸውን አስታወቀ
ሰመጉ በሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞን ከህዳር 24 እስከ የካቲት 4 ቀን 2010 ዓ.ም 17 ሰላማዊ ዜጎች በፀጥታ ሃይሎች በግፍ መገደላቸውን አስታወቀ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 04 ቀን 2010 ዓ/ም ) በአማራ ክልል በሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞን በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈፀመውን ኢሰብዓዊ የመብት ጥሰቶች አስመልክቶ ሰመጉ በ145ኛው ልዩ መግለጫው፣ ከህዳር 24 እስከ የካቲት 4 ቀን 2010 ዓ.ም በሰሜን ወሎ ...
Read More »በሽብር ወንጀል ተከሰው በቅርቡ ከእስር የተፈቱት ሰራተኞች ወደ ስራቸው መመለስ አለመቻላቸውን ተናገሩ
በሽብር ወንጀል ተከሰው በቅርቡ ከእስር የተፈቱት ሰራተኞች ወደ ስራቸው መመለስ አለመቻላቸውን ተናገሩ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 04 ቀን 2010 ዓ/ም ) በአማራ ክልል ነዋሪ የሆኑ ሃሳባቸውን በመግለጻቸው በሽብርተኝነትና በተለያዩ ወንጀሎች ታስረው በእስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ ስቃይ ከደረሰባቸው በሁዋላ ከእስር የተፈቱት የመንግስት ሰራተኞች፣ ቀድሞ ወደ ነበሩበት የስራ ቦታ መመደብ ባለመቻላቸው ለችግር መደረጋቸውን ለኢሳት ተናግረዋል። በአርበኞች ግንቦት7 ስም ተከሶ 5 አመታት ከ6 ...
Read More »ሃረር ከተማ በቆሻሻ የተነሳ ወረርሽኝ ያሰጋታል ተባለ
ሃረር ከተማ በቆሻሻ የተነሳ ወረርሽኝ ያሰጋታል ተባለ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 04 ቀን 2010 ዓ/ም ) በሃብሊና በኦህዴድ መካከል ያለውን አለመግባባት ተከትሎ የከተማው ቆሻሻ ይደፋበት የነበረው በከር የሚባለው አካባቢ ላይ ቄሮዎች ቆሻሻ እንደማይደፋ በመከልከላቸው ምክንያት በከተማው ያለው ቆሻሻ መብዛት ለበሽታ እየዳረጋቸው ነው። ወኪላችን እንደገለጸው መንግስት ቆሻሻውን ወስዶ መድፋት ባለመቻሉ ቆሻሻው ከተማ ውስጥ እንዲከበር ሆኗል። በተለይ ትልቁ የገበያ ማእከል በሆነው ሸዋበር ...
Read More »በደቡብ ሱዳን ለተቀናቃኞች ምህረት የሚያስገኝ አዋጅ ይፋ ሆነ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 3/2010) የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ለተቀናቃኞቻቸው ምህረት የሚያስገኝ አዋጅ ይፋ አደረጉ። ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ሙሉ የምህረት አዋጁን ይፋ ያደረጉት ከካርቱሙ የሰላም ስምምነት በኋላ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የምህረት አዋጁ በደቡብ ሱዳን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ይፋ ተደርጓል። ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር የሰጡት ምህረት የቀድሞው የደቡብ ሱዳንን ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻርን ጨምሮ የትጥቅ ትግል ይሚያደርጉ አማፅያን ጭምር የሚያካትት ነው። የምህረት አዋጁ ይፋ የተደረገው በደቡብ ሱዳን ...
Read More »ሰንደቅ ጋዜጣ ተዘጋ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 3/2010) በሰንደቅ የህትመትና የማስታወቂያ ድርጅት ላለፉት 14 ዓመት ያህል በየሳምንቱ ረቡዕ እየታተመ የሚወጣው “ሰንደቅ” ጋዜጣ ተዘጋ። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በአማርኛ ቋንቋ ታትመው ለገበያ የሚቀርቡ የግል ሳምንታዊ ጋዜጦችም “ሪፖርተር እና “አዲስ አድማስ” ብቻ ሆነዋል፡፡ ሰንደቅ ጋዜጣ የተዘጋው በየጊዜው እየናረ ከመጣው የሕትመት ዋጋ ጋር ተያይዞ ባጋጠመው ኪሳራ ምክንያት መሆኑን የሰንደቅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ አቶ ፍሬው አበበ ገልጸዋል፡፡ ጋዜጣው በሳውዲ አረቢያ ...
Read More »የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ አማካሪ ምክር ቤት ተቋቋመ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 3/2010)የ“ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ” አማካሪ ምክር ቤት ተቋቋመ። 15 አባላት ያሉት የዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ምክር ቤት መቋቋሙ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ይፋ ሆኗል። ምክር ቤቱ በታዋቂው ምሁር ዶክተር አለማየሁ ገብረማርያም ሊቀመንበርነት የሚመራ ይሆናል። በምክር ቤቱ ውስጥ ከታዋቂ ዲያስፖራ አባላት መካከል አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ እና አቶ ኦባንግ ሜቶ ይገኙበታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተለያዩ ሃገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ...
Read More »በምዕራብ ጉጂና ጌዲዮ አካባቢ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ተደረገ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 3/2010) አለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማህበርና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ከደቡብ ክልልና ኦሮሚያ አወሳኝ ቦታዎች በምዕራብ ጉጂና ጌዲዮ አካባቢ ለተፈናቀሉ ሰዎች ድጋፍ አደረጉ። ቀይ መስቀል በምዕራብ ጉጂና ጌዲዮ አዋሳኝ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ መስጠት መጀመሩን አስታወቋል። በኦሮሚያና ደቡብ አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠረ ግጭት ባለፈው ሚያዚያና ሰኔ ወር ላይ እስከ 1 ሚሊዮን የሚደርሱ የአካባቢው ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል፡፡ በግጭቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ ...
Read More »