በሽብር ወንጀል ተከሰው በቅርቡ ከእስር የተፈቱት ሰራተኞች ወደ ስራቸው መመለስ አለመቻላቸውን ተናገሩ

በሽብር ወንጀል ተከሰው በቅርቡ ከእስር የተፈቱት ሰራተኞች ወደ ስራቸው መመለስ አለመቻላቸውን ተናገሩ
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 04 ቀን 2010 ዓ/ም ) በአማራ ክልል ነዋሪ የሆኑ ሃሳባቸውን በመግለጻቸው በሽብርተኝነትና በተለያዩ ወንጀሎች ታስረው በእስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ ስቃይ ከደረሰባቸው በሁዋላ ከእስር የተፈቱት የመንግስት ሰራተኞች፣ ቀድሞ ወደ ነበሩበት የስራ ቦታ መመደብ ባለመቻላቸው ለችግር መደረጋቸውን ለኢሳት ተናግረዋል።
በአርበኞች ግንቦት7 ስም ተከሶ 5 አመታት ከ6 ወር በእስር ቤት ያሳለፈው አቶ አሸናፊ አካሉ እንደገለጸው፣ መንግስት አሸባሪው እኔ ነኝ ብሎ ካመነ በሁዋላ፣ ለእኛ አስፋለጊውን የሞራል ካሳ ክሶና የአለፉትን ክፍያዎች አስቦ በመክፈል ወደ ስራችን መመለስ ሲገባው፣ ይህን ባለማድረጉ፣ ያለስራ እንድንቀመጥና ለችግር እንድንዳረግ አድርጎናል ብለዋል።
“ ተርበን ከሰውነት ተራ ወጥተን ከእስር ቤት ብንወጣም አሁንም በችግር እየተጎሳቆልን” ነው የሚሉት አቶ አሸናፊ፣ ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች በችግር ተጠብሰው ጎዳና ላይ እየሄዱ ነው ብለዋል።