.የኢሳት አማርኛ ዜና

በአዲስ አበባ የሚፈርሱትን ቤቶች ተከትሎ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እየተፈጸመ ነው ተባለ

ህዳር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለህዳሴው ግድብ ማሰሪያ ቃል ከተገባው ገንዘብ ውስጥ እስካሁን  የተሰበሰበው  አነስተኛ መሆኑ ታወቀ ሙስሊሙ ኀብረተሰብ በትናንትናው ዕለት የታሰሩትን የሙስሊም ችግሮች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ለመጠየቅ ቃሊቲ እስር ቤት ማጨናነቃቸውን የዓይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ ዜና 1 በአዲስ አበባ የሚፈርሱትን ቤቶች ተከትሎ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እየተፈጸመ ነው ተባለ ሰሞኑን ገርጂ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከ2 ሺ ያላነሱ ...

Read More »

ለህዳሴው ግድብ ማሰሪያ ቃል ከተገባው ገንዘብ ውስጥ እስካሁን የተሰበሰበው አነስተኛ መሆኑ ታወቀ

ህዳር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት “የአቶ መለስን ራዕይን ለማሳካት” በሚል መፈክር ለህዳሴ ግድብ ማሰሪያ የሁለተኛ ዙር መዋጮ የማሰባሰብ ዘመቻ በይፋ ጀምሯል፡፡ ባለፈው ዓመት ለግድቡ ማሰሪያ የመንግስትና የግል ድርጅቶች ሰራተኞች በዓመት የሚከፈል የአንድ ወር ደመወዝ በስጦታ መልክ ቢለግሱም ገዥው ፓርቲ ቁጠባን ለማበረታት በሚል ስጦታው ወደ ቦንድ ግዥ እንዲቀየር በወሰነው መሰረት ክፍያቸውን ላጠናቀቁ ተቋማትና ሰራተኞች የቦንድ ሰርተፊኬት በመስጠት ...

Read More »

በቶሮንቶ ካናዳ የተሰራው ዘመናዊ ቤተክርስቲያን ተመረቀ

ህዳር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ተደርጎበት በቶሮንቶ ከተማ ላይ የተሰራው ዘመናዊው የመንበረ ብርሃን ቅድስት ማርያም ካቴድራል በብፁ አቡነ መርቆርዮስ  ቅዳሜ ኖቬምበር  17 ቀን 2012 ዓም ተመርቆ ሥራውን ጀመረ። ከተለያዩ ክፍላተ ዓለም የመጡ ጳጳሳት፣ ቀሳውስት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ምዕመናንና ካናዳውያን ባለስልጣናት በተገኙበት እሁድ ኖቬምበር  18 ቀን 2012 ዓ ም በሰፊው ቀጥሎ በዋለው የምረቃ ስነስርዓት ...

Read More »

በአባይ ግድብ ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች በብዛት እየለቀቁ ነው

ህዳር ፰ (ሰምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአባይ ግድብ ላይ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በውጭ አገር አሰሪዎችና ተባባሪ በሆኑት ኢትዮጵያውያን ተቆጣጣሪዎች በሚፈጸም በደል ስራቸውን እየለቀቁ መሆኑን በድርጅቱ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ገልጸዋል። በመጀመሪያዎቹ የግንባታ ወራት አገራዊ ስሜቱ ፈንቅሎት ወደ አካባቢው በመሄድ ከአንድ አመት ከስድስት ወራት በላይ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ወጣት ፣  ሰራተኛው በየጊዜው  በሚደርስበት በደል በቀን ውስጥ ከ30 እስከ 40 የሚደርሱ ሰራተኞች ...

Read More »

አቶ ሀይለማርያም ፦ኢትዮጵያ ኑክሌርን ጥቅም ላይ ለማዋል ቁርጠኛ ናት አሉ

ህዳር ፰ (ሰምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-<<ኢትዮጵያ የኑክሌር ቴክኖሎጂን  ሰላማዊ የልማት አጀንዳዋን ለማሳካት ብቻ ጥቅም ላይ ለማዋል ቁርጠኛ ናት>>ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ። መንግስታዊው  የኢትዮጵያ  ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃለማሪያም  ይህን ያሉት፤የአለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዩኪያ አማኖን ሰሞኑን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው። <<ኑክሌርን ለሰላማዊ አገልግሎት ብቻ በመጠቀም ረገድ ኢትዮጵያ ከኤጀንሲው ጋር ምንጊዜም ...

Read More »

የጸጥታው ምክር ቤት በአወዛጋቢዋ የአቢይ ግዛት ጦሩን ለማቆየት ወሰነ

ህዳር ፰ (ሰምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰሜንና ደቡብ ሱዳንን በማወዛገብ ላይ ባለችው የአቤይ ግዛት ላይ የሰፈረው 4 ሺ የሚጠጋው የኢትዮጵያ ጦር ለተጨማሪ ስድስት ወራት ባለበት እንዲቆይ አርብ ውሳኔ አሳልፎአል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ የሆኑት ባንኪ ሙን በአወዛጋቢዋ አቤይ ግዛት አንጻራዊ ሰላም ቢታይም ሰሜንና ደቡብ ሱዳን ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በቂ ትኩረት አለመስጠታቸውን ገልጸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአቤይ የተመድን ጦር ...

Read More »

በደራ ወረዳ በተፈጸመው ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ኢትዮጵያውያን ቁጣቸውን መግለጽ ቀጥለዋል የዞኑ አስተዳዳሪ በግለሰቡ ላይ አፋጣኝ ፍርድ ይሰጣል ብለን እንጠብቃለን ይላሉ

ህዳር ፰ (ሰምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በአንድ አርሶአደርና ባለቤታቸው ላይ የተፈጸመውን ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ይፋ ካደረገ በሁዋላ ኢትዮጵያውያንን ከያቅጣጫው እያስቆጣ መሆኑን ኢሳት ያነጋገራቸው እንዲሁም ለኢሳት መልእክቶችን የሚተው ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ አንድ አስተያየት ሰጪ በድርጊቱ ማዘን ብቻውን በቂ አለመሆኑን ገልጸው ወደ ተግባር መግባት አለብን ሲሉ አሳስበዋል። ሌላው  በዳላስ ቴክሳስ የሚኖሩ ግለሰብ ...

Read More »

የዓረና ትግራይ ፓርቲ የፕሮፖጋንዳና የፖለቲካ ጉዳይ ተጠሪ የሆነው ወጣት ዓምዶም ገ/ስላሴ ታሰረ

ህዳር ፰ (ሰምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአረና የተላከው መረጃ እንደሚያመለክተው ፣ ወጣቱ የታሰረው በተከራየው ግቢ ውስጥ ነዋሪ የሆነችው የህወሓት አባል “በግቢያችን ፖለቲካ እየሰበክ ሌሎች ሰዎችን ወደ ዓረና ትግራይ ልትወስድ ነው በማለት ባነሱት ኣታካራ ” ነው። ያለ ምንም መጥሪያና በቅርብ ይጠባበቁ የነበሩ ፖሊሶች ይዘዋቸው በመሄድ ዓዲ ሀቂ ፖሊስ ጣብያ በተባለ እስር ቤት አስረዋቸውል ይላል መግለጫው። የዓረና ትግራይ  የፅሕፈት ቤት ዶኩሜንትና ...

Read More »

የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ለኢትዮጵያ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ተገቢውን ዕውቅና እየሰጡ አይደለም ተባለ

ህዳር ፰ (ሰምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ ዜናዊ  ከዚህ ዓለም በሞት ከተሰናበቱ ወዲህ ሕዝቡ ሐዘኑን ከመግለጹ ጋር ተያይዞ “የመለስን ራዕይ ሳይበረዝ፣ሳይከለስ እናስፈጽማለን” ወደሚል ቅዥት ውስጥ መገባቱን የሚያስታውሱት ዘጋቢያችን የናጋገራቸው ባለሙያዎች ይህንን አጀንዳም እንደ ኢትዮጽያ ቴሌቪዥን ያሉ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ክፉኛ እያራገቡት፣በአንጻሩ ደግሞ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር መኖራቸው እንኳን እየተረሳ የመጣበት ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል፡፡ “የኢትዮጵያን ህዳሴ እናበስራለን” የሚለው ኢቲቪ በአሁን ሰዓት ...

Read More »

የሺ ጋብቻ ቅዳሜ ይከናወናል

ህዳር ፰ (ሰምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኤሚነንስ ሶሻል ኢንተርፐርነርስ በኢትዮጽያ በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ፤መመዝገቡ የማይቀር ነው ያለውን የአንድ ሺ ጥንዶች ጋብቻ ቅዳሜ ህዳር 8 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስአበባ ጎተራ ማሳለጫ የብሄር ብሄረሰቦች መንደር ተብሎ በሚታወቀው ሜዳ ላይ እንደሚያከናውን አስታወቀ፡፡ በኢትዮጽያ በዚህ ደረጃና ዓይነት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ጥንዶች በአንድነት ሲዳሩ የመጀመሪያው ሲሆን ሥነሥርዓቱም ሁሉም ተጋቢዎች የመጡበትን አካባቢ ወይም ክልል ባህል፣አለባበስ በሚያንጸባርቅ መልኩ እንደሚካሄድ ...

Read More »