ታህሳስ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሽብረተኝነት ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት የኦፌዴንና የኦህኮ የአመራር አባላት የሆኑት አቶ በቀለ ገርባና አቶ ኦልባና ሊሊሳ ከሌሎች 7ተከሳሾች ጋር ዛሬ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀርበው የ8 እና የ13 ዓመት እስር ተፈርዶባቸዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት የኦፌዴን ም/ል ሊቀመንበርና የመድረክ አመራር አባል የሆኑት አንደኛው ተከሳሽ አቶ በቀለ ገርባ በ8 አመት ፣ ሁለተኛው ተከሳሽ የኦህኮ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የ50 ሺ ብር ዋስ እንዲያቀርብ ታዘዘ
ታህሳስ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በ50 ሺ ብር ዋስ በማስያዝ ክሱን በውጭ ሆኖ እንዲከራከር ትእዛዝ አስተላልፎአል። ዳኛው በመዝገብ ቁጥር 123 ሺ 875 የተከሰሰው ጋዜጠኛ ተመስገን ከዚህ ቀደም ለብይን ተቀጥሮ እያለ አቃቢ ህግ ክሱን በማንሳቱ የተቋረጠ ቢሆንም አቃቢ ህግ እንደገና ክሱን በመቀስቀሱ ነው ለዛሬ የተቀጠረው ብሎዋል። የአቃቢ ህግን የክስ አስተያየት ...
Read More »ኦህዴድ በውስጥ ያለውን ክፍፍል ለማብረድ አባላቱን ሰበሰበ
ታህሳስ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት አቶ ሙክታር ከድር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ በመካከለኛው ደረጃ ያለውን አመራር የማጠናከር፣ የማረጋጋትና የማጽዳት እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው። ከፍተኛ ችግር በሚታይበት በምስራቅ ኦሮሚያ እና በሀረሪ ክልል የሚገኙ በመካከለኛ ደረጃ የሚገኙ የኦህዴድ አመራሮች ፣ መምህራንና ርእሰ መምህራን፣ የወረዳ አስተዳዳሪዎችና የድርጅት አባላቶች ከህዳር 27 ጀምሮ ስብሰባ ላይ ናቸው። በሀረሪ ክልል በአሚር አብዱላሂ ...
Read More »የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሮች ውዝግብ መሥሪያ ቤቱን እያመሰው ነው
ታህሳስ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰንደቅ በህዳር 25፣ 2005 ዓም እትሙ እንዳስነበበው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በሚኒስትሩና በሚኒስትር ዴኤታው መካከል ከፍተኛ ውዝግብ ተቀስቅሷል። በሁለቱ ሚኒስትሮች የተፈጠረው አለመግባባት በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ላይ ግራ መጋባትን መፍጠሩን የጠቀሰው ሰንደቅ፣ ወደ 1 ሺህ 800 የሚጠጉ የሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞችም ስራቸውን በአግባቡ ማከናወን አልቻሉም ብሎአል። የጸቡ ምክንያት የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንትና ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ...
Read More »የአዲስ አበባ ወጣቶች የአንድነት የቃሊቲ ጉብኝት እንዲካሄድ ጠየቁ
ታህሳስ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ወጣቶቹ ለኢሳት በላኩት መልእክት እንደገለጡት በመጪው እሁድ ታህሳስ 7፣ 2005 ዓም አለአግባብ የታሰሩ የሙስሊም ማህበረሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን፣ ጋዜጠኞችንና የተቃዋሚ መሪዎችን በቃሊቲ ተገኝተው ለመጠየቅና ለመዘከር አስበዋል። ማንኛውም የህገመንግስቱን የእምነት እና ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት መከበር እንዳለበት የሚደግፍ ኢትዮጵያዊ በሙሉ ወደ ቃሊቲ በመሄድ ድጋፉን እንዲያደርግ እንጠይቃለን ያለው መግለጫ፣ እነዚህ ታሳሪዎች ህገመንግስቱ የሰጣቸውን መብት በመጠቀም ...
Read More »መስተዳድሩ የሚድሮክን ሁዳ ሪል ስቴት መሬት ነጠቀ
ታህሳስ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሪፖርተር እንደዘገበው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሥር ለሚገኘው ሁዳ ሪል ስቴት ሜክሲኮ አደባባይ ከዋቢ ሸበሌ ሆቴል አጠገብ ሰጥቶት የነበረውን የግንባታ መሬት የነጠቀው መሬቱን ከተረከበ ካለፉት 8 አመታት ጀምሮ ግንባታ ባለማካሄዱ ነው፡፡ 6ሺ 400 ሄክታር ስፋት ያለው መሬት የተሰጠው ከፍታቸው ከ20 ፎቅ በላይ የሆኑ መንትያ ሕንፃዎች እንደገነቡበት ነበር። ሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ ...
Read More »ፕሬዚዳንት ሞርሲ መከላከያ ሰራዊቱ ህግ እንዲያስከብር ጠየቁ
ታህሳስ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በግብጽ የተጀመረው ተቃውሞ የፕሬዚዳንቱን ስልጣን አደጋ ውስጥ እየከተተው መምጣቱን ተከትሎ ፕሬዚዳንቱ የጤር ሀይሉ ህግ እንዲያስከብር፣ የመንግስት ተቋማትን እንዲጠብቅና አጥፊዎችን እንዲያስር ስልጣን ሰጥተዋል። ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሞርሲ በቅርቡ ከፍተኛ ስልጣን የሚሰጣቸውን ህግ በመሰረዝ የህዝቡን ቁጣ ለማብረድ የሞከሩ ቢሆንም ፣ የህዝቡ ቁጣ ግን አሁንም ሊበርድ አልቻለም። ተቃዋሚዎች ለአዲሱ ህገመንግስት ድምጽ ለመስጠት የፊታችን ቅዳሜ የተያዘውን ቀጠሮ እንዲሰረዝ ቢጠይቁም፣ ...
Read More »ጠቅላይ ሚ/ር ሀይለማርያም ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ለምታደርገው የእግር ኳስ ጨዋታ ቦታ እንዲለወጥ መጠየቁን አላውቅም አሉ
ህዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ይህን የተናገሩት ከአልጀዚራ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው። ረዩተር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቃል አቀባይ የሆኑትን አቶ መላኩ አየለን በመጠቀስ ” ለተጫዋቾች ደህንነት ሲባል እግር ኳስ ፌደሬሽኑ የጨዋታው ቦታ እንዲቀየር መጠየቁን ” ዘግቦ ነበር። ቢቢሲና አልጀዚራን የመሳሰሉ ታላላቅ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀንም ለጉዳዩ የዜና ሽፋን መስጠታቸው ይታወቃል። በኢትዮጵያ በኩል የቀረበውን ...
Read More »በባህርዳር ለሚከበረው 7ኛው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ዝግጅት 200 ሚሊየን ብር ወጪ መደረጉ ታወቀ
ህዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት የመረጃ ምንጮች እንደገለጡት በአሉን ለማክበር የወጣው ገንዘብ እስካሁን ባለው ግርድፍ መረጃ 200 ሚሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ሂሳቡ ሲወራረድ ወጪው ከዚህም ከፍ ሊል ይችላል ተብሎአል። በትናንትናው ዕለትም በ20 ሚሊየን ብር የተሰራችው ህዳሴ የተሰኘች መርከብ የከተማዋ ነዋሪዎች፣እንግዶች፣ባለስልጣናት በተገኙበት ተመርቃለች፡፡ህገመንግስቱ የጸደቀበት ህዳር 29 የብሔርብሔረሰቦች በዓል ሆኖ እንዲከበር የፌዴሬሽን ም/ቤት በወሰነው መሰረት በዓሉ በፈንጠዝያና በግብዣ ...
Read More »በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ የንብረት ውርስ ላይ ትእዛዝ ተሰጠ
ህዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከፍተኛው ፍርድ ቤት በ1ኛ ተከሳሽ በአቶ አንዷለም አራጌ ባለቤት ስም የተመዘገበው የቤት መኪና ፤ በ7ኛ ተከሳሽ አቶ እስክንድር ነጋ ስም የተመዘገበ 1 ቤትና ከእናታቸው በውርስ ያገኙት ተዳምሮ 2 መኖሪያ ቤቶች እና በባለቤታቸው ስም የተመዘገበ 1 የቤት መኪና ፤ እንዲሁም በሌሉበት በተከሰሱት በ16ኛ ተከሳሽ በአቶ አበበ በለው ባለቤት ስም ፥ የተመዘገበ መኖሪያ ቤት ...
Read More »