.የኢሳት አማርኛ ዜና

በጅጅጋና በሌሎች የክልሉ ከተሞች የተቃጠሉትን አብያተክርስቲያናት መልሶ ለመገንባት እንቅስቃሴ ተጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 11/2010) የሶማሌ ክልል የሀገር ሽማግሌዎችና ህዝቡ በጅጅጋና በሌሎች የክልሉ ከተሞች የተቃጠሉትን አብያተክርስቲያናት መልሶ ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተገለጸ። በደገሃቡር ከተማ ከትላንት በስቲያ በተካሄደ ህዝባዊ ስብሰባ በአብዲ ዒሌ ተከታዮች የተፈጸመውን ጥቃት ዳግም እንዳይከሰት ለማድረግ ቃል መገባቱንም የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። በጥቃቱ የተጎዳውን ህዝብና የወደሙትን አብያተክርስቲያናት ለማቋቋም ሰፊ ስራ እንዲጀመር ከስምምነት ላይ መደረሱን ለማወቅ ተችሏል። ዛሬም በጅጅጋ ተመሳሳይ ህዝባዊ ስብሰባ መደረጉን ያገኘነው ...

Read More »

የመንግስት ከመጠን ያለፈ ትዕግስት ለሀገሪቱ አንድነትና ለዜጎች ደህንነት አደጋ ደቅኗል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 11 /2010) መንግስት እያሳየ ያለው ከመጠን ያለፈ ትዕግስት ለሀገሪቱ አንድነትና ለዜጎች ደህንነት አደጋ መደቀኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስተያን ዛሬ ገለጸች። በቅርብ ግዜያት ውስጥ በተፈጠሩ ግጭቶች ዘጠኝ አብያተ ክርስትያናት ሲወድሙ አምስት ካህናት በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውንም ቤተክርስትያኒቱ አስታውቃለች ። በባሌ፣ በሻሸመኔ፣ እንዲሁም በጣና በለስ በተለይም በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ያለውን ሁኔታ ትኩረት ሰጥታ የተመለከተችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተለይ በኢትዮጵያ ሶማሌ ...

Read More »

በአዲስ አበባ ከጊዜ ወደ ጊዜ የተቃውሞ ሰልፎች የሚያደርጉ አካላት እየጨመሩ መጥተዋል።

በአዲስ አበባ ከጊዜ ወደ ጊዜ የተቃውሞ ሰልፎች የሚያደርጉ አካላት እየጨመሩ መጥተዋል። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 11 ቀን 2010 ዓ/ም ) የዶክተር አብይ አስተዳደር መጥቶ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተነሳ ወዲህ ተደጋጋሚ ሰልፎች እየተደረጉ ሲሆን፤ ፖለቲከኞች በሽግግር ጊዜ እንዲህ ያሉ ክስተቶች የሚጠበቁ ናቸው ይላሉ። በአፈና ውስጥ ያለፈ ሕዝብ ትንሽ ነጻነት እንደተሰማው ሲቆጥር የዚህ ዓይነት ክስተቶች መብዛታቸው አይገርምም የሚሉት ፖለቲከኞች፣አስፈላጊው እና ትኩረት የሚያስፈልገው ...

Read More »

የብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ከወረዳ ጀምሮ በርካታ አመራሮቹን እያነሳ መሆኑን ተከትሎ በክልሉ አለመረጋጋት እንዳይከተሰት ጥንቃቄ ይደረግ ዘንድ ተጠየቀ።

የብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ከወረዳ ጀምሮ በርካታ አመራሮቹን እያነሳ መሆኑን ተከትሎ በክልሉ አለመረጋጋት እንዳይከተሰት ጥንቃቄ ይደረግ ዘንድ ተጠየቀ። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 11 ቀን 2010 ዓ/ም ) በድርጅቱ ውስጥ ያሉ የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ብአዴን በአሁኑ ወቅት በሁሉም ወረዳዎች የአመራር ለውጦችን እያደረገ ሲሆን፣ የለውጡ እንቅፋት ናቸው ተብለው የተለዮ ዋነኛ አመራሮቹንም ለመቀየር ዝግጅቶች አጠናቋል። ከደሴ ከ30፣ከሀይቅ ከ30፣ከኮምቦልቻ ከ40 በላይ አመራሮች በአዲስ ...

Read More »

ኢትዮጵያና ሱዳን በጋራ ድንበራቸው ላይ ከሁለቱ አገራት የተውጣጣ ጥምር ጦር ለማሰማራት መስማማታቸውን መንግስታዊ መገናኛ ብዙሀን ዘገቡ።

ኢትዮጵያና ሱዳን በጋራ ድንበራቸው ላይ ከሁለቱ አገራት የተውጣጣ ጥምር ጦር ለማሰማራት መስማማታቸውን መንግስታዊ መገናኛ ብዙሀን ዘገቡ። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 11 ቀን 2010 ዓ/ም ) ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር በገበሬዎች መካከል ግጭቶች ሲከሰቱ መቆየታቸው ይታወሳል። አሁን በድንበሮቻቸው ላይ ከሁለቱም ሀገራት የተውጣጣ ጦር ለማሰማራ የወሰኑት ፣ የሁለቱአገራት ጦር ኢታማዦር ሹሞች ትላንትናው ካርቱም ላይ ተገናኝተው ከመከሩ በኃላ ነው። በድንበር አካባቢ የሚሰፍረው ...

Read More »

ከቀናት በፊት ከእስር የተፈቱ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባላትን ለመቀበል አደባባይ ከወጣው የአርባ ምንጭ ነዋሪ ውስጥ በርካቶች መታሰራቸው ተገለጸ።

ከቀናት በፊት ከእስር የተፈቱ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባላትን ለመቀበል አደባባይ ከወጣው የአርባ ምንጭ ነዋሪ ውስጥ በርካቶች መታሰራቸው ተገለጸ። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 11 ቀን 2010 ዓ/ም ) ነሀሴ 8 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት ከእስር ከተለቀቁት የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ አባላት መካከል የአርባ ምንጭ ልጆች የሆኑትን ወጣት ተካልኝ መንግስቱ እና ወጣት አወቀ ደመቀን በልዩ ድምቀት ለመቀበል የከተማው ነዋሪ አደባባይ መውጣቱ ያስቆጣቸው ...

Read More »

በመሬት መንሸራተት አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት አለፈ

(ኢሳት ዲሲ–ነሀሴ 10/2010) በምስራቅ ጎጃም ዞን በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት አለፈ። በዞኑ ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ስድስት የቤተሰብ አባላትና ሌሎች ሁለት ልጆች  ሞተዋል፡፡ የብሔራዊ ሚትዮሮሎጂ ድርጅት በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች በክረምቱ ወራት የጎርፍ አደጋ እንደሚኖር አስቀድሞ ማስጠንቀቁም ታውቋል። በምስራቅ ጎጃም ዞን በእነገት ቀበሌ ልዩ ስሙ ወይን ውሃ በተባለ ጎጥ ነሀሴ 8/2010 ዓ.ም ከሌሊቱ 7 ...

Read More »

በምስራቅ ጎጃም ሁለት ትምህርት ቤቶች ስማቸው ሊቀየር ነው

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 10/2010) በምስራቅ ጎጃም ዞን የሚገኙ ሁለት ትምህርት ቤቶች ስማቸው ሊቀየር መሆኑ ተገለጸ። በአቶ መለስ ዜናዊና በግንቦት 20 ሲጠሩ የነበሩት ትምህርት ቤቶች ስያሜያቸው እንዲቀየር መወሰኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በሸበል በረንታና በአዋበል ወረዳዎች የሚገኙት የሁለተኛ ደረጃና የመሰናዶ ትምህርት ቤቶች እስካሁን ሲጠሩበት የነበሩበት ስያሜዎች የሚወክሉን አይደሉም በሚል እንዲቀየሩ ነው ከስምምነት የተደረሰው። በሌላ በኩልም በባህርዳር የሚገኘውና በግንቦት 20 ስም የሚጠራው አውሮፕላን ማረፊያ ...

Read More »

የአማራ ክልል ልዑካንና አዲሃን ምክክር ጀመሩ

(ኢሳት ዲሲ–ነሀሴ10 /2010) የአማራ ክልል ልዑክ በአስመራ ከተማ ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ /አዲሃን/ ጋር ምክክር መጀመሩ ተነገረ፡፡ አዴኃንና የአማራ ክልል መንግስት ልኡካን የአማራን ህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡበት ጉዳይ ላይ እየመከሩ መሆኑም ታውቋል በቅርቡ የአዴኃን አመራሮች በሰላም ለመታገል በመወሰናቸው ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው ከምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን እና ከአማራ ክልል ገዱ አንዳርጋቸው ጋር መምከራቸው ይታወሳል። በዚሁም አዲሃን ወደ ሀገሩ ገብቶ ...

Read More »

ሒዩማን ራይት ዎች የለውጥ ሒደት ላይ እንቅፋት እየተፈጠረ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 10/2010)በኢትዮጵያ እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶች በተጀመረው የለውጥ ሒደት ላይ እንቅፋት እየፈጠሩ መሆኑን ሒዩማን ራይት ዎች ገለጸ። ሒዩማን ራይትስ ዎች እንዳለው በኢትዮጵያ በብሔርና በሃይማኖት ሰበብ የሚካሄዱ ግድያዎች ከፍተኛ ውጥረት በመፍጠር ላይ ናቸው። በተለይም በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች የሚፈጸሙ ጥቃቶች በለውጡ ሂደት ላይ እንቅፋት እየፈጠሩ ነው ብሏል ሒዩማን ራይትስ ዎች። ይህ በእንዲህ እንዳለም መንግስት ለውጡን የሚያደናቅፉ ግጭቶችን እንዲያስቆም የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ ...

Read More »