በአዲስ አበባ ከጊዜ ወደ ጊዜ የተቃውሞ ሰልፎች የሚያደርጉ አካላት እየጨመሩ መጥተዋል።

በአዲስ አበባ ከጊዜ ወደ ጊዜ የተቃውሞ ሰልፎች የሚያደርጉ አካላት እየጨመሩ መጥተዋል።
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 11 ቀን 2010 ዓ/ም ) የዶክተር አብይ አስተዳደር መጥቶ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተነሳ ወዲህ ተደጋጋሚ ሰልፎች እየተደረጉ ሲሆን፤ ፖለቲከኞች በሽግግር ጊዜ እንዲህ ያሉ ክስተቶች የሚጠበቁ ናቸው ይላሉ።
በአፈና ውስጥ ያለፈ ሕዝብ ትንሽ ነጻነት እንደተሰማው ሲቆጥር የዚህ ዓይነት ክስተቶች መብዛታቸው አይገርምም የሚሉት ፖለቲከኞች፣አስፈላጊው እና ትኩረት የሚያስፈልገው ጉዳይ ሰልፎቹ -የመብት ጥያቄ አቅራቢዎቹም ሆነ የህዝቡ ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ በሰላም መከናወናቸው ላይ ነው ብለዋል።
ዛሬም በአዲስ አበባ በአምስት አካባቢ ሠራተኞች “መብታች ይከበር!”በማለት በሰልፍ ሲጠይቁ ተደምጠዋል።