የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መምሪያ አዛዥ ተጨማሪ ጊዜ ተጠየቀባቸው ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 17 ቀን 2010 ዓ/ም ) ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓም በመስቀል አደባባይ ላይ በደረሰው ፍንዳታ በመምራትና በማስተባበር እጃቸው አለበት የተባሉት የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መምሪያ አዛዥ ጌታቸው ኡርጌ ላይ ተጨማሪ የምርምራ ጊዜ በተጠየቀባቸው መሰረት ፍርድ ቤት የ2 ሳምንታት የቀጠሮ ጊዜ ሰጥቷል። የተጠርጣሪው ጠበቆች ግለሰቡ ከተያዘ 43 ቀናት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የሶማሌ ክልል ሕዝብ በአቶ አብዲ ኢሌይ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ሢደርስበት የቆየውን ግፍና በደል ያለማሳለስ ሲታገሉና ሲያጋልጡ የቆዩት አክቲቪስት ሙስጠፋ ኡመር በርዕሰ ብሔርነት ክልሉን እንዲያስተዳድሩ ተመረጡ።
የሶማሌ ክልል ሕዝብ በአቶ አብዲ ኢሌይ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ሢደርስበት የቆየውን ግፍና በደል ያለማሳለስ ሲታገሉና ሲያጋልጡ የቆዩት አክቲቪስት ሙስጠፋ ኡመር በርዕሰ ብሔርነት ክልሉን እንዲያስተዳድሩ ተመረጡ። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 17 ቀን 2010 ዓ/ም ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስብዓዊ ድጋፍ አገልግሎት ክፍል ውስጥ በጎረቤት ሀገራት እያገለገሉ የነበሩት የ 45 አመቱ አቶ ሙስጠፋ ኡመር ፣በአብዲ ኢሌይ ለስደት ከተዳረጉ የክልሉ ምሁራን መካከል አንዱ ...
Read More »ሶማሊ ላንድ ሲያመልጡ የነበሩ ሁለት የኢትዮጵያ ባልስልጣናትን ይዛ አሰረች።
ሶማሊ ላንድ ሲያመልጡ የነበሩ ሁለት የ ኢትዮጵያ ባልስልጣናትን ይዛ አሰረች። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 17 ቀን 2010 ዓ/ም ) ሀልቤግ የተሰኘው የሀገሪቱ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው፣ የሶማሊላንድ የደህንነት ባለስልጣናት ሀርጌሳ ውሰጥ ነው ሁለት የአብዲ ኢሌይ የካቢኔ አባላትን ይዘው ያሰሩት። የታሰሩት ባለስልጣናት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ የነበሩት ኢብራሂም አድም ማሃድ እና የፍትህ ቢሮ ሃላፊው አብዲልማጅድ አህመድ ጃማ ናቸው። ባለስልጣናቱ የተያዙት፤የክልሉ ርእስ መስተዳድር ...
Read More »ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከስልጣን ከተነሱ አሜሪካ የኢኮኖሚ አደጋ ያጋጥማታል አሉ
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከስልጣን ከተነሱ አሜሪካ የኢኮኖሚ አደጋ ያጋጥማታል አሉ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 17 ቀን 2010 ዓ/ም ) ፕሬዚዳንቱ ከፎክስ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እርሳቸውን ከስልጣን ለማንሳት ሙከራ የሚደረግ ከሆነ የአገሪቱ ኢኮኖሚ አደጋ ውስጥ ሊወድቅ ይችላል። ፕሬዚዳንቱ በምርጫ ዘመቻ ወቅት ለሁለት ሴቶች ገንዘብ መክፈላቸውንም የቀድሞው ጠበቃቸውና ጉዳይ አስፈጻሚያቸው ሚካኤል ኮኸን ካጋለጡ በሁዋላ ነው። ፕሬዚዳንቱ በጠበቃቸው አማካኝነት የከፈሉት ገንዘብ ከሁለቱ ሴቶች ...
Read More »የሶማሊ ክልል የመብት ተሟጋቾች እየተካሄደ ባለው የሶህዴፓ ግምገማ ደስተኞች እንዳልሆኑ እየገለጹ ነው
የሶማሊ ክልል የመብት ተሟጋቾች እየተካሄደ ባለው የሶህዴፓ ግምገማ ደስተኞች እንዳልሆኑ እየገለጹ ነው ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 16 ቀን 2010 ዓ/ም ) ክልሉን ለረጅም ጊዜ ሲያስተዳድር የነበረው ሶህዴፓ፣ በሊቀመንበሩ በአቶ አብዲ ሺዴ አማካኝነት ግምገማ እያካሄደ ቢሆንም፣ የመብት ተሟጋች የክልሉ ተወላጆች እንደሚሉት ግን በክልሉ መሰረታዊ የሆነ መዋቅራዊ ለውጥ የማምጣት ፍላጎት ይኖራል ብለው ለማመን እየተቸገሩ ነው። የሶህዴፓ አመራሮች እና አባላት በግምገማው ወቅት እጅግ ...
Read More »በደቡብ ክልል ባስኪቶ ልዩ ወረዳ ላይ ተቃውሞ ሲካሄድ ዋለ
በደቡብ ክልል ባስኪቶ ልዩ ወረዳ ላይ ተቃውሞ ሲካሄድ ዋለ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 16 ቀን 2010 ዓ/ም ) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት የባስኪቶ ሁለት ፖሊሶች ማሎ ወረዳ ላይ መታሰራቸውን ተከትሎ የባስኪቶ ወረዳ ነዋሪዎች ተቃውሞአቸውን ለማሰመት አደባባይ ወጥተዋል። መንገዶች ተዘግተው መዋላቸውን እንዲሁም በማሎ ወረዳ ተወላጆች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ነዋሪዎች ገልጸዋል። በጥይት የተጎዱ ነዋሪዎች መኖራቸውም አካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
Read More »በሃረር አካባቢ የሚኖሩ የትግራይ ባለሀብቶችና ተወላጆች ወደ ክልላቸው እየተመለሱ ነው
በሃረር አካባቢ የሚኖሩ የትግራይ ባለሀብቶችና ተወላጆች ወደ ክልላቸው እየተመለሱ ነው ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 16 ቀን 2010 ዓ/ም ) ወኪላችን እንደዘገበው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የትግራይ ተወላጅ ባለሀብቶችና ነዋሪዎች ንብረቶቻቸውን እየሸጡ ወደ ክልላቸው በመመለስ ላይ ናቸው። ህወሃት በኢትዮጵያ ውስጥ ጦርነት ሊነሳ ይችላል በሚል ቅስቀሳ የትግራይ ተወላጆች ከአካባቢው እንዲለቁ ማድረጉን የሚገልጸው ወኪላችን፣ ይህንን በማመን ባለፉት 3 ሳምንታት በርካታ ባለሀብቶች መውጣታቸውን ገልጿል። በህወሃት ...
Read More »አቃቢ ህግ በሰኔ 16 የመስቀል አደባባይ ፍንዳታ ክስ መመስረት አለመቻሉ ተዘገበ
አቃቢ ህግ በሰኔ 16 የመስቀል አደባባይ ፍንዳታ ክስ መመስረት አለመቻሉ ተዘገበ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 16 ቀን 2010 ዓ/ም ) የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መርማሪ ቡድን በሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ በደረሰው የቦምብ ፍንዳታ ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራውን አጠናቆ ለዓቃቤ ሕግ ቢያስረክብም፣ ዓቃቤ ሕጉ ክስ ከመመስረት ለድጋሚ ምርመራ ለመርማሪ ቡድኑ መዝገቡን መመለሱን ለፍርድ ቤት ማስታወቁን ሪፖርተር ዘግቧል። አቃቢ ...
Read More »የዚምባቡዌ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት በምርጫው ውጤት ላይ ዋነኛው ተቃዋሚ ፓርቲ ያቀረበውን ክስ አዳመጠ።
የዚምባቡዌ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት በምርጫው ውጤት ላይ ዋነኛው ተቃዋሚ ፓርቲ ያቀረበውን ክስ አዳመጠ። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 16 ቀን 2010 ዓ/ም ) የዲሞክራሲ ለውጥ ንቅናቄ ትብብር ወይም በምህጻረ ቃሉ- ኤም፣ዲ ሲ ፕሬዚዳንት ምናንጋግዋን አሸናፊ ያደረገውን የምርጫ ውጤት በመቃወም ነው ክስ ያቀረበው። ምናንጋዋ ምርጫውን ያሸነፉት በ 30 ሺህ የድምጽ ብልጫ እንደሆነ ነው በምርጫ ኮሚሽኑ የተገለጸው። የተቃዋሚ ፓርቲው አመራሮች ግን ፣ ...
Read More »የኢትዮጵያ የእስልምና አባቶች እስልምና የሰላምና የአንድነት ምንጭ መሆኑን ሰበኩ
የኢትዮጵያ የእስልምና አባቶች እስልምና የሰላምና የአንድነት ምንጭ መሆኑን ሰበኩ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 15 ቀን 2010 ዓ/ም ) ዛሬ በአዲስ አበባ ተከብሮ በዋለው 1ሺ 439ኛው የኢድ አል አድሃ ( አረፋ) በአል ላይ የተገኙት የሃይማኖቱ አባቶች እስልምና የሰላምና አንድነት መሰረት መሆኑን ተናግረዋል። ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሰላምን በመጠበቅ፣ የአገሩን አንድነት በመጠበቅ አገሩን ማሳደግ እንዳለበት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተወካይ ተቀዳሚ ሙፍቲ ...
Read More »