በደቡብ ክልል ባስኪቶ ልዩ ወረዳ ላይ ተቃውሞ ሲካሄድ ዋለ

በደቡብ ክልል ባስኪቶ ልዩ ወረዳ ላይ ተቃውሞ ሲካሄድ ዋለ
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 16 ቀን 2010 ዓ/ም ) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት የባስኪቶ ሁለት ፖሊሶች ማሎ ወረዳ ላይ መታሰራቸውን ተከትሎ የባስኪቶ ወረዳ ነዋሪዎች ተቃውሞአቸውን ለማሰመት አደባባይ ወጥተዋል። መንገዶች ተዘግተው መዋላቸውን እንዲሁም በማሎ ወረዳ ተወላጆች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በጥይት የተጎዱ ነዋሪዎች መኖራቸውም አካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።