.የኢሳት አማርኛ ዜና

የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሀመድ ኡመር የመንግስት ሰራተኞች የአባልነት ክፍያ በግዴታ እንደሚቆረጥባቸው ተናገሩ

ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት እጅ በገባው የፕሬዚዳንቱን ሚስጢራዊ ንግግሮች በያዘው  ፊልም ውስጥ እንደተመለከተው ፣ አቶ አብዲ የኢህአዴግ አጋር ድርጅት የሆነው የሶማሊ ህዝብ ዴሞክራሲ ፓርቲ ( ሶህዴፓ) አባላት በግዴታ የአባልነት መዋጮ እንዲከፍሉ መደረጋቸውን ተናግረዋል። ” መንግስት በአንድ በኩል ገንዘብ ይሰጣል በሌላ በኩል ደግሞ ገንዘብ ከፋዩዋ በግዴታ ከሰራተኞች እየቆረጠች ትወስዳለች” ብለዋል አቶ አብዲ። አቶ አብዲ ድርጅታቸው ሶህዴፓ 40 ...

Read More »

በአውሮፓ ህብረት መቀመጫ ብራሰልስ የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ

ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሆላንድ እና የቤልጂየም የኢትዮጵያውያን ማህበሮች ባዘጋጁት ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ኢትዮጵያዊያን ተገኝተው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ለአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት አቅርበዋል። ኢትዮጵያውያኑ በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን መፈናቀል እንዲሁም መንግስት በሀይማኖቶች ውስጥ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት አውግዘዋል። የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ፣ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱ ሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዲቆሙም ጠይቀዋል።

Read More »

የኢትዮጽያ መንግስት በሰሜን ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ የሠፈሩ ሰዎችን በአስቸኳይ እንዲወጡ ካላደረገ የፓርኩን የምዝገባ ዕውቅና እንደሚሰርዝ ዩኔስኮ አስጠነቀቀ፡

ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በፌዴራል መንግስት ስር ከሚተዳደሩ 13 ብሔራዊ ፓርኮች አንዱና ዋናው የሆነው የሰሜን ብሔራዊ ፓርክ በዩኔስኮ የተመዘገበ ሲሆን ፓርኩ ከመመስረቱ በፊት ጀምሮ ሰፍረው የነበሩ ሰዎችን ከአካባቢው ለማስወጣት ከዚህ ቀደም የተደረጉ ተደጋጋሚ ጥረቶች አለመሳካታቸውን ተከትሎ ዩኔስኮ በቅርቡ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ታውቋል፡፡ ከዩኔስኮ ማስጠንቀቂያ የደረሰው የኢትዮጵያ መንግስት በፓርኩ ክልል ውስጥ የሚገኙ ከ300 በላይ አባወራዎችን ለማስወጣት ጥረት መጀመሩን ...

Read More »

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩት ዳይሬክተር በርሳቸው ጥፋት ቤተሰቦቼ መታሰራቸው አግባብ አይደለም “ሀገሪቱ ምን አይነት ገር እየሆነች ነው” ሲሉ ለፍርድ ቤት ጥያቄ አቀረቡ

ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ ገብረዋሕድ ወ/ጊዮርጊስ የጉምሩክ ባለሥልጣን ም/ዳይሬክተር ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር የጠበቀ ግንኙነት አላቸው የሚባሉት ባለቤታቸው ኮ/ል ሃይማኖት ተስፋይ መታሰራቸውና ልጃቸውም መደገማቸው ፈጽሞ አግባብ አይደለም ካሉ በኋላ እኔ በጥፋቴ ልጠየቅ ቤተሰቦቼ ለምን? ምን አይነት ሀገር እየሆንን ነው በማለት ታላንት ከሰዓት ባስቻለው ችሎት ጠይቀዋል። የአቶ ገብረዋሕድ ወ/ጊዮርጊስ ባለቤት ኮ/ል ሃይማኖት ተስፋይ እናታቸው ወ/ሮ ንግሥቲና ልጃቸው ...

Read More »

በተያያዘ ዜና በጉምሩክ ባለሥልጣኖችና ባለሃብቶች ላይ የተጀመረው የምርመራ ሥራና ዘመቻ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ትዕዛዝና መመሪያ መሆኑ ተገለጠ

ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑትን አቶ ዓሊ ሱሌይማንን ጠቅሶ ሪፖርተር እንደዘገበው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሕይወት በነበሩበት ወቅት በሰጡት የሥራ መመሪያ መሰረት ጥናትተደርጎ የተከናወነ መሆኑን አስታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአመት ከአሥር ወር በፊት የሥራ መመሪያ መስጠታቸውን ለተወካዮች ምክር ቤት የተናገሩት ኮሚሽነሩ ጥናቱ ሲጠናቀቅ አቶ መለስ በመታመማቸው ውሳኔ አግኝቶ ወደሥራ ሳይገባ ቆይቷል ብለዋል።በኢትዮጵያ ባለው አሰራር ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሳተላይት ሬዲዮ፣ የሬዲዮ አድማጮቹን ቁጥር ለመጨመር በሚያደርገው ጥረት በአራት ተጨማሪ ሃገሮች በስልክ ሬዲዮውን የማሰራጨት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ

ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሳተላይት ሬዲዮ ማኔጅመንት ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ መሰረት በዩናይትድ ኪንግደም፣ በጀርመን፣ በደቡብ አፍሪካና በኖርዌይ አድማጮች የኢሳት ሬዲዮን ፕሮግራሞች በስልክ እንዲያዳምጡ የሚያስችል አገልግሎት ዘርግቷል። በዚህ መሠረት በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ የኢሳት ሬዲዮ አድማጮች በስልክ ቁጥር 44-203-519-7144፣ የጀርመን አድማጮች 49-230-218-590-0200፣ የደቡብ አፍሪካ አድማጮች 27-105-918-884፣ የኖርዌይ አድማጮች ደግሞ በስልክ ቁጥር 47-219-532-14 ደውለው ፕሮግራሞችን ማድመጥ የሚችሉ መሆኑን ...

Read More »

በባህርዳር 17 ሰዎችን በጥይት አርከፍክፎ በግፍ የገደለው የፌደራል ፖሊስ አባል ከዘር ጋር የተያያዘ ምክንያት የለውም ሲሉ የአማራ ክልል የፖሊስ አዛዥ ተናገሩ

ግንቦት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እሁድ ግንቦት4፣ 2005 ዓም ከምሽቱ 2 ሰአት ከ45 ደቂቃ ላይ ፣ የሁለት አመት ህጻንን ጨምሮ 17 ሰዎችን  በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 11 ወይም በተለምዶ አባይ ማዶ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በግፍ የገደለው የፌደራል ፖሊስ አባል ማንነት መለየቱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አስታውቋል። ኢሳት ትናንት  ፖሊሱ የሌላ ብሄር ተወላጅ መሆኑን ጠቅሶ የዘገበ ሲሆን አንዳንድ ወገኖች ይህን በመንተራስ ...

Read More »

በቻግኒ ከተማ የህዝብን ተቃውሞ ተከትሎ አንድ መስጊድ ታሸገ

ግንቦት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዊ ዞን በቻግኒ ከተማ መስጊድ አረህማን እየተባለ የሚጠራው ነባር መስጊድ የታሸገው ህዝቡ መንግስት የወከለውን አሰጋጅ አንቀበልም በማለት ተቃውሞ በማሰማቱ ነው። በመስጊዱ መግቢያ ላይ  የተለጠፈው ወረቀት ፣ ” ከዛሬ ጀምሮ በዚህ መስጊድ መስገድ በህግ ያስቀጣል” የሚል ይዘት እንዳለው የአይን እማኞች ተናግረዋል። ነባሩ መስጊድ እንዲታሸግ መደረጉን ተከትሎ ህዝበ ሙስሊሙ መንገድ ላይ መስገድ መጀመሩን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ...

Read More »

የኩል ዉሀ ፋብሪካ መርዛማ ዝቃጭ አሳስቦናል ሲሉ ኗሪዎች ተናገሩ

ግንቦት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በምእራብ ጎጃም ዞን በቡሬ ከተማ ንብረትነቱ የሼህ ሙሀመድ አላሙዲን የሆነው የቡሬ ኩል ውሀና ለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ መርዛማ ዝቃጭ በጤና ላይ እያደረሰው ያለ ችግር አሳስቦናል ሲሉ የወረዳው ኗሪዎች ተናገሩ፡፡ ህዝቡ ለመጠጥና ለመስኖ ስራ በሚገለገልባቸው ይስርና ኩል ወንዞች የሚለቀቀው መርዛማ ዝቃጭ ወንዙን ተከትሎ በሰፈረው ህዝብ ላይ ከሚያደርስው የጤና ችግር ባለፈ በንብረት ላይ አሉታዊ ተፅንኦ ፈጥሯል ...

Read More »

በመኪና አደጋ የ 17 ሰዎች ህይዎት አለፈ

ግንቦት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በባህር ዳር ከተማ በመሸንቲ ሳተላይት ቀበሌ ቆጥቆጥማ ተብሎ  በሚጠራው አካባቢ ግንቦት 1/2005 ዓ/ም ሁለት መኪናዎች ተጋጭተው የ16 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ አደጋው የተከሰተው ከእንጅባራ ወደ ባህር ዳር ከተማ 19 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-08862  አማ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ከባህር ዳር ከተማ ወደ  ዳንግላ ከተማ በመጎዝ ላይ ...

Read More »