ነሃሴ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የ33 ፓርቲዎች ትብብር ለኢሳት በላከው መግለጫ እንዳመለከተው መንግስት እየተከተለ ያለው የሀይል እርምጃ በዜጎች ህገመንግስታዊ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ላይ የተፈጸመ ህገወጥ አምባገነናዊ ድርጊት በመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ድርጊቱን ሊቃወምና ሊያወግዝ ይገባዋል። በአገር ቤትና በውጪ ያሉ የመገናኛ ብዙኃን፣ የነጻው ፕሬስ አባላት እና ማኅበራዊ ድረ-ገጾች በህዝበ ሙስሊሙና ክርስቲያኑ መካከል ያለመተማመን ለመፍጠር ከሚሰራጨው አፍራሽ ፕሮፖጋንዳ ሰለባነት የመታደግና የዘመናት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ኢትዮጵያ ከወጪ ምርት ያገኘችው ገቢ ከሌሎች አገራት ጋር ሲነጻጸር በጣም በአነስተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ።
ነሃሴ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አሜሪካ በሰጠችው የአጎዋ የገበያ ዕድል ቀነ ቀጠሮ ማራዘም ላይ በሰፊው ሲመክር የነበረው 12ኛው የአጎዋ ጉባዔ አፍሪካ ዕድሉ እንዲራዘም መፈለጓን የአሜሪካ የህግ አውጭ ምክርቤት ተወካዮች ለምክር ቤቱ እንዲያሳውቁላቸው በመጠየቅ ተጠናቋል፡፡ በ12ኛው የአጎዋ ፎረም የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ ኢትዮጵያ ባለፉት 12 ዓመታት ወደ አሜሪካ የላከችው ምርት በየዓመቱ በአማካይ 80 በመቶ ጭማሪ ያሳዬ ቢሆንም፤ ከወጪ ምርቱ ...
Read More »ሁለት ተቀጣጣይ ባእድ እቃ የያዙ ሲሊንደሮች በቦሌ አውሮፓላን ማረፊያ መገኘታቸውን መንግስት ገለጸ
ነሃሴ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል ፖሊስ የጋራ የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል እንዳስታወቀው፣ ሁለቱ ሲሊንደሮች የተገኙት በጽዳት ሰራተኞች ጥቆማ ነው። መንግስት ባእድ ነገሩን ማን እንዳስቀመጠው፣ በባእድ ነገሩ ውስጥ ምን እንዳለ ያስታወቀው ነገር የለም።
Read More »12 የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ
ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢድ አልፈጥርን በዓል ለማክበር ባለፈው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ ከተጓዙ በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች መካከል አስራ ሁለት የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ለኢሳት አስታወቁ፡፡ አራት የአሜሪካ፣ ሁለት የሲዊዲን፣ አንድ የአውስትራሊያና አምስት የተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያኑ ከትላንትናው እለት ጀምሮ በማዕከላዊ ማረሚያ ቤት እንደሚገኙ ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡ በቁጥጥር ስር ...
Read More »የአሜሪካ ፓሊስ ኢትዮጵያውያኑን በማደን ላይ ናቸው
ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአሜሪካ ፖሊሶች ከኢትዮጵያ ለምስክርነት መጥቶ የጠፋን ኢትዮጵያዊ ዱካ ለማግኘት ፍለጋ ላይ መሆናቸውን ሲአትል ኒውስ ዛሬ ዘገበ፡፡ ካሳይ ወልደ ፃድቅ የተባለው ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊያኖቹ ጥንዶች ከኢትዮጵያ በማደጎ ያመጧትን ልጅ ገድላችኋል ተብለው ለተከሰሱበት ወንጀል አቃቢ ህግ ለምስክርነት ማስረጃ ይሆን ዘንድ ብለው ነበር ከኢትዮጵያ ያመጡት፡፡ ካሳይ በፍርድ ሂደት ላይ ላለው ጉዳይ ባለፈው አርብ በማውንት ቬርኖን ካውንቲ ፍርድ ቤት ...
Read More »250 ሺህ ዜጎች በግጭት በኦሮሚያና አማራ ክልሎች ተፈናቀሉ
ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት አለም አቀፍ የምግብ ድርጅት በኦሮሚያና አማራ ክልሎች በተለያዩ ግጭቶችና አደጋዎች ጉዳት ለደረሰባቸው 250 ሺህ ዜጎች አስቸኳይ እርዳታ መስጠት መጀመሩን ለኢሳት በላከው መግለጫ አስታወቀ፡፡ ድርጅቱ በኦሮሚያና አማራ ደርሶ ስለነበረው ግጭት ዝርዝር መረጃን ከመስጠት ቢቆጠብም 250ሺህ ለሆኑት ዜጎች ግን ጊዜያዊ የሆነ የምግብና የገንዘብ እርዳታ መስጠት ላይ እንደሆነ ገልጿል፡፡ ከአውሮፓ ህብረት ...
Read More »በወልድያ የታሰሩት ፍርድ አጥተው በመሰቃየት ላይ ናቸው
ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንዲት አራስን ጨምሮ ከ19 ያላነሱ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ለአንድ ወር ያክል በእስር ካሳለፉ በሁዋላ ዛሬ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ምንም መፍትሄ ሳይሰጥ ወደ እስር ቤት እንደሚለሱ ተደርጓል። የአካባቢው ሰዎች ፍትህ ለማግኘት በፍርድ ቤቱ አካባቢ ቢሰባሰቡም በፖሊስ ሀይል እንዲበተኑ ተድርጓል። አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ፍርድ ቤቱ በተከሳሾች ላይ በቂ ማስረጃ ያልቀረበለት በመሆኑ ጉዳያቸውን መከታተል አቁሟል። ኢሳት ...
Read More »አቶ መለስ ዜናዊን ለመዘከር በተለያዩ ከተሞች ማእከላት እየተገነቡ ነው
ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ መለስ ዜናዊን አንደኛ የሙት አመት መታሰቢያ በማድረግ በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች የዝክረ መለስ ዝግጅቶች እየተካሄዱ ነው። በአዲስ አበባ 100 ሄክታር መሬት ስፋት ያለው ቦታ ከሀያት ሆስፒታል ፊት ለፊት ለመለስ ማእከል ግንባታ ተከልሏል። መስተዳድሩ ማእከሉን እንደሚያሰራ የአዲስ አበባ መስተዳድር አዲሱ ከንቲባ ድሪባ ኩማ የመሰረት ድንጋይ ባስቀመጡበት ወቅት ገልጸዋል። ግንባታው ምን ያክል ገንዘብ እንደሚፈጅ ግን ...
Read More »ጋዜጠኛ ሌሊሴ ወዳጆ ከአምስት ዓመት እስራት በሁዋላ ተፈታች።
ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የኦሮሚኛ ፕሮግራም ባልደረባ የነበረው ባለቤቷ ጋዜጠኛ ዳበሳ ዋቅጅራ ከሦስት ዓመት እስር በሁዋላ ከአገር መውጣቱን ተከትሎ በኦነግ አባልነት ክስ ተመስርቶባት ታስራ የቆየችው ጋዜጠኛ ሌሊሴ ወዳጆ ከ እስር ተፈታች። በ 1995 ዓመተ ምህረት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እየሠራ ሳለ ድንገት ለእስር የተዳረገው ጋዜጠኛ ዻበሳ ዋቅጅራ አንዳችም ክስ ሳይመሰረትበት ለሦስት ዓመታት በእስር ከቆየ በሁዋላ መፈታቱ ይታወሳል። ከእስር ቢለቀቅም ...
Read More »የሙስሊም ጥያቄ እና የኢህአዴግ ስጋት
ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የሕዝበ ሙስሊሙን ከ18 ወራት በላይ የዘለቀ እንቅስቃሴ በኃይል ለማፈን ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ እየወሰደ ያለው እርምጃ በሙስሊም አባላቱ ዘንድ ቅሬታ ማሳደሩ የግንባሩን ከፍተኛ አመራር ስጋት ውስጥ እንደጣለ የውስጥ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ አብዛኛዎቹ የግንባሩ ሙስሊም ከፍተኛ የአመራር አባላትን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ መካከለኛ፣ ዝቅተኛ አመራር አባላት መንግስት በሙስሊሙ ጥያቄ አፈታት ጉዳይ እየተከተለ ባለው ኃይል የተቀላቀለበት ...
Read More »