.የኢሳት አማርኛ ዜና

የግንቦት7 አባላት ናቸው የተባሉ ሰዎች ክስ ተመሰረተባቸው

ነሃሴ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከተለያዩ የአማራ አካባቢዎች ተያዙ የተባሉ 10 ሰዎች ዛሬ በአቃቂ 4ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል። ዘመኑ ካሴ ከተባለው ሰው በስተቀር ሌሎች 9ኙ ተከሳሾች ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ለህዳር 2 ቀን፣2006 ዓ/ም ቀጠሮ ተሰጥቶአቸዋል። ፍርድ ቤት ከቀረቡት መካከል የባህርዳር ከተማና ዙሪያዋ ነዋሪዎች የሆኑት አሸናፊ አካሉ፣ ደህናሁን ቤዛ፣ ምንዳየ ለማ፣ አንሙት የኔዋስ፣ ሳለኝ አሰፋ ፣ የክልሉ ...

Read More »

በቢኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መብራት ለተከታታይ ሳምንታት መቆረጡን ኑዋሪዎች ተናገሩ፤

ነሃሴ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቢኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ፓዊ እና አልሙ የከተማ እና የገጠር አካባቢዎች እንዲሁም በአማራ ክልል ቻግኒ እና አካባቢው መብራት ለተከታታይ ሳምንታት መቆረጡን ኑዋሪዎች ተናገሩ፤ ነዋሪዎች ለኢሳት ባደረሱት መረጃ እንዳሉት በመብራት እጦት በከፍተኛ ሁኔታ ተሰቃይተናል ሲሉ ምሬታቸውን ገልጸዋል፡፡ የኢትዩጵያ መብራት ሃይል ኮርፖሬሺ ከአቅም በላይ ሁኖብኛል ሲል ተናግሮዋል፡፡ ድሃ አስፈጭቶ ለመብላት በየቀኑ ገዝተው ፤ ...

Read More »

አንድነት ፓርቲ በፍቼ የተቃውሞ ሰልፍ ሲያደርግ በባሌ ሮቤ አቅዶት የነበረውን ሰልፍ ደግሞ ሰረዘ

ነሃሴ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በፍቼ ከተማ እሁድ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፈ ላይ የገዢው ፓርቲ አፈና በግልጽ የተነጸባረቀበት እንደነበር የፓርቲው የምክርቤት አባል አቶ አበበ አካሉ ገልጸዋል በባሌ ሮቤ ሊካሄድ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ገዢው ሀይል የሀይል እርምጃ ለመውሰድ በማቀዱ ሳይሳካ መቅረቱን በስፍራው የተገኙት የፓርቲው የምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካርያስ የማነብርሀን እንደገለጹት ገዢው ፓርቲ በተቃውሞው ላይ ለመገኘት በሚመጡ ሰዎች ላይ እርምጃ ...

Read More »

ኢህዴግ ነሐሴ 26 ቀን ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ይፋ አደረገ

ነሃሴ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጽያ ሃይማኖቶች ተቋማት ጉባዔ ዛሬ ከቀትር በሁዋላ በአ/አ አምባሳደር ቲያትር አካባቢ በሚገኘው ጽ/ቤቱ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ አክራሪነትን ለመቃወም የፊታችን እሁድ ነሃሴ 26 ቀን በመስቀል አደባባይ ሰልፍ መጥራቱን አስታወቀ፡፡ በዕለቱ ሰማያዊ ፓርቲ ሁለተኛ ሰልፉን በመስቀል አደባባይ ለማድረግ በይፋ ለአስተዳደሩ አሳውቆ ምላሽ እየተጠባበቀ የሚገኝ ሲሆን ምናልባት የሃይማኖት ተቋማቱ ሰልፍ ለማካሄድ መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ የሰማያዊ ሰልፍ ...

Read More »

ኢ/ር ተስፋሁን ጨመዳ በእስር ቤት ውስጥ ህይወቱ አለፈ

ነሃሴ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለኦሮሞ ህዝብ መብት በመታገል ላይ የነበረው የ37 ዓመቱ ወጣት ኢ/ር ተስፋሁን ጨመዳ ቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ እንዳለ መሞቱ ታውቋል። ኢ/ሩ በምን ምክንያት እንደሞተ ግን አልታወቀም።  ከጓደኞቹ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ኢ/ር ተስፋሁን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ከነበረበት ጌዜ ጀምሮ ገዢውን ፓርቲ ይቃወም ነበር። ኢ/ር ተስፋሁን ኬንያ በነበረበት ወቅት ምንም እንኳን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እውቅና ...

Read More »

መንግስት በቫንኩቨር ካናዳ ሊያደርግ የነበረው የቦንድ ሽያጭ ተቃውሞ ገጠመው

ነሃሴ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከአባይ በፊት ዘረኝነት የወገድ በማለት መቃወማቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የመንግስት ወኪሎች ተቃውሞውን በመፍራት ሊሰበሰቡበት ተከራይተውት የነበረውን አዳራሽ በመተው በሰዎች ቤት ስብሰባውን በግለሰቦች ቤት ለማድረግ ተገደዋል። በስፍራው ለተገኙት አንዳንድ አረጋውያን ለአባይ ቦንድ የሚገዙ ከሆነ የቤት መስሪያ ቦታ እንደሚሰጠቻው በስበሰባው መሪዎች ተነግሮአቸዋል። መንግስት በውጭ አገራት የሚያደርገው የቦንድ ሽያጭ ቅስቀሳ በተደጋጋሚ ተቃውሞ ...

Read More »

ከአዲስ አበባ ወደ ወልዲያ ሲጓዝ የነበረ አውቶቡስ ተገልብጦ በርካታ ሰዎች ሞቱ

ነሃሴ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአዲስ አበባ ወደ ወልድያ ሲጓዝ የነበረ ሚኒባስ አውቶቡስ ደሴ አካባቢ ሲደርስ በመገልበጡ የ21 ሰዎች ህይወት ጠፋ፣ የዛሬውን ጨምሮ በአንድ ሳምንት ውስጥ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 66 ደርሶአል። የአደጋው  መንስኤ ጥራት የሌለው የአስፓልት መንገድ በጎርፍ በመቆረጡ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። የወልድያ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ለኢሳት እንደገለጸው ደግሞ የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ባሙያዎች ከደሴ በመላካቸው መረጃው ...

Read More »

በአንዋር መስጂድ የጁምአ ሰላት ይሰግዱ የነበሩ ሴት ሙስሊሞቸ ተደበደቡ፡፡

ነሃሴ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ በአንዋር መስጂድ የጁምአ ሰላታቸውን በመስገድ ላይ የነበሩ ሙስሊም ሴቶች በፖሊስ መደብደባቸውን የ ኢሳት ወኪል ከስፍራው ዘግቧል። በጁምአ ሰላት ላይ የነበሩት ሙስሊም ሴቶች የተደበደቡት፤ “ሶላት መስገድ የምትችሉት በግቢ ውስጥ እንጂ ከግቢ ውጪ አንጥፋችሁ አትሰግዱም” ተብለው በውጪ እንዳይሰግዱ በፖሊሶች መከልከላቸውን ተከትሎ በተፈጠረ አለመግባባት ነው። ሙስሊም ሴቶቹ ሁልጊዜ እንደሚያደርጉት ከውጪ አንጥፈው መስገድ መጀመራቸውን የጠቆመው ...

Read More »

በባህርዳር የኢህአዴግ አባል ያልሆነና በአንድ ለአምስት አደረጃጀት ያልተደራጀ ስኳዐር አያገኘም ተባለ

ነሃሴ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከባህርዳር የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው ኢህአዴግ ለከተማው ነዋሪዎች አዲስ የአባልነትና አንድ ለአምስት አባልነት መለያ ወረቀት ያዘጋጀ ሲሆን፣ ይህንን ወረቀት ያላሳየ ሰው በመንግስት የሚከፋፈለውን ስኳር አያገኝም። አንዳንድ ነዋሪዎች ችግራቸውን በኤፍ ኤም ራዲዮ ላይ ቢናገሩም ምንም መፍትሄ እንደሌለው እንዳወቁ ለኢሳት ተናግረዋል። በጉዳዩ ዙሪያ የክልሉን ህዝብ ግንኙነት ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። ኢህአዴግ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገር ...

Read More »

በሱዳን ከ300 ሺ ህዝብ በላይ በጎርፍ ተጠቃ

ነሃሴ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አለም የጤና ድርጅት እንደገለጸው በያዝነው ወር በጣለው ዝናብ ከ50 በላይ ሰዎች ሞተው፣ ከ300 ሺ ያላነሱት ደግሞ ተፈናቅለዋል። በተለይ በዋና ከተማዋ ካርቱም ላለፉት 25 አመታት ያልታየ ጎርፍ መታየቱን ድርጅቱ አስታውቋል። በአገሪቱ ካሉ 18 ግዛቶች መካከል በ14 ላይ ከፍተኛ የንብረት መውደምም ተከስታል።

Read More »