ነሃሴ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሞያሌ ከተማ በገሪና በቦረና ጎሳዎች መካከል ከሳምንታት በፊት የተነሳው ግጭት እንደገና አገርሽቶ የአካባቢው ነዋሪዎች ቀያቸውን ለቀው እየተሰደዱ ነው። የኬንያ መንግስት የጸጥታ ሀይሎችን ወደ አካባቢው በመላክ ግጭቱን ለመከላከል እየሞከረ መሆኑን ቢናገርም ችግሩ ግን ተባብሶ መቀጠሉን የኬንያ ጋዜጦች አየዘገቡ ነው። እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ ከ20 ያላነሱ ሰዎች ተገድለዋል። በአካባቢው የሚገኙ የንግድ ቤቶች ሲወድሙ ትራንስፖርትም ቆሟል። ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ወታደራዊ ትጥቅማ ምረቻ ፋብሪካ በቃጠሎ ጉዳት ደረሰበት
ሃሴ ፳፫(ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ በተነሳ የእሳት አደጋ ቃጠሎ በመከላከያ ሚኒስትር የትጥቅና ወታደራዊ ልብስ ስፌት ፋብሪካ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የአይን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ፡፡ ከአዳማ ከተማ ወደ ወንጂ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው ወታደራዊ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ በፋብሪካው ላይ ከፍተኛ የንብረት ጉዳት መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በ18 ሚሊዮን ብር ወጪ በቅርቡ የተገነባው ፋብሪካው ...
Read More »ኢትዮጵያውያን ነገ በዋሽንግተን ዲሲ ሰልፍ ይወጣሉ
ሃሴ ፳፫(ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እየተካሄደ ያለውን የሙስሊም ማህበረሰብ ጥያቄ የማፈን ተግባርን በመቃወም ነገ በዚህ በዋሽንግተን ዲሲ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ የሰልፉ አስተባባሪ አካላት ለኢሳት ገለጹ፡፡ የአርብ የፀሎትና የስግደት ስነ ስርዓትን ተከትሎ የሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ በሀገር ቤት እየተካሄደ ያለውን የመንግስት እርምጃ ለማውገዝ ያለመ እንደሆነ የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ሰይድ አብዱራህማን ተናግረዋል፡፡ የሙስሊሙን ጥያቄ ለማፈን ...
Read More »ፓሊስ የሰማያዊ ፓርቲ አመራርን ነገ ሊያነጋግር ነው
ነሃሴ ፳፫(ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰማያዊ ፓርቲ የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ፓሊስ የፓርቲውን አመራሮች በመጥራት ለነገ ሊያነጋግራቸው ቀጠሮ መያዙን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ፡፡ ፓርቲው በበኩሉ ሊካሄድ የታቀደውን የተቃውሞ ሰልፍ በምንም አስገዳጅ ሁኔታ ሊሰርዝ እንደማይችል በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፓርቲው አመራሮች ተናግረዋል፡፡ ምንጮች ለኢሳት እንደገለጹት ከሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ነገ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ላይ ...
Read More »በሀይማኖት ጉዳይ የመጣው ችግር ጊዜ የሚሰጥ አልሆነም ሲሉ አቶ በረከት ተናገሩ
ነሃሴ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጠቅላይ ሚ/ሩ አማካሪ አቶ በረከት ስምኦን ይህን የተናገሩት በመካሄድ ላይ ባለው የሀይማኖቶች ጉባኤ ላይ ነው። በጉባኤው ላይ የተገኙት አንዳንድ የሀይማኖት አባቶች መንግስት “ትእግስቱን አብዝቶታል፣ እርምጃ ይውሰድልን” እያሉ መጠየቃቸውን ተከትሎ፣ አቶ በረከት ” መንግስት ሀይሉ እንዳለውና መታገሱ ጠቃሚ መሆኑን” ተናግረዋል። “ይሁን እንጅ” ይላሉ አቶ በረከት “የተፈጠረው ችግር ጊዜ የሚሰጥ አልሆነም”። አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ...
Read More »የአዲስ አበባ መስተዳድር ሰማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ ሰልፍ የሚያደርግ ከሆነ፤ሰልፉ ህገወጥ ነው አለ።
ነሃሴ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰንደቅ እንደዘገበው በመጪው እሁድ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በማወዛገብ ላይ ነው። ቀደም ሲል ሰማያዊ ፓርቲ በዕለቱ ሰልፍ እንደሚያካሂድ ቢያስታውቅም፤ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት በበኩሉ ነሐሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም በጽ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ በተመሳሳይ ቀን ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ይፋ አድርጓል። ይህንን ተከትሎ ...
Read More »ዩኒስኮ የላሊበላ አብያተ-ክርስቲያናት አደጋ ላይ ናቸው አለ
ነሃሴ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የባህል እና የሳይንስ ድርጅት ስር በአለም ቅርስነት የተመዘገቡት የላሊበላ ውቅር እና ፍልፍል አብያተ ክርስትያናት የመፍረስ አደጋ ውስጥ ናቸው ሲል አለም አቀፉ ድርጅት አስታውቋል፡፡ ዩኔስኮ ባቀረበው ጥናት ቅርሶቹ ባለፉት አርባ አመታት በተለያየ መልኩ በርካታ ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሺ ችግሮች ተጋርጦባቸዋል ብሎአል፡፡ የኢትዮጵያ የቅርስ ጥናት ጥበቃ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ደስታ ...
Read More »ምእራባዊያን በሶሪያ ላይ ጥቃት ሊሰነዝሩ እየተዘጋጁ ነው
ነሃሴ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የበሽር አላሳድ መንግስት በሲቪሎች ላይ የኬሚካል የጦር መሳሪያ ተጠቅሟል በሚል ሰበብ ምእራባዊያን ሀይል እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጁ ነው። እንግሊዝ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት አንድ ህግ ረቂቅ ያዘጋጀች ሲሆን ረቂቁም አገሮች በሶሪያ ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ መብት ይሰጣል። የአየር ላይ ጥቃታቸውን ለመሰንዘር እየተዘጋጁ ያሉት አሜሪካ፣ ፈረንሳይና እንግሊዝ ከቻይናና ከሩሲያ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። ...
Read More »አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ተቃዋሚዎችን በድጋሜ አስጠነቀቁ
ነሃሴ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት ባዘጋጀው በሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ” የአገሪቱ አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የአክራሪዎችንና የአሸባሪዎችን እንቅስቃሴዎች ከመደገፍ ካልተቆጠቡ ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት እርምጃ እንወስዳለን” ብለዋል። ማንኛውም ጸረ ሰላም እንቅስቃሴ በሚያደርጉትም ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የገለጡት አቶ ሐይለማርያም፣ የጥፋት ሀይሎችን ለማምከን የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል። አዲሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን ፓትሪያርክ ...
Read More »በመጪው እሁድ በአዲስ አበባ ሰማያዊ ፓርቲ እና ኢህአዴግ በየፊናቸው ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ተከትሎ አዝማሚያው ወደ ውጥረት እያመራ መሆኑን ታዛቢዎች ገለጹ።
ነሃሴ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰማያዊ ፓርቲ ቀደም ካሉት ጊዜያት ጀምሮ ለነሐሴ 26 ቀን 2013 ዓመተምህረት ሰልፍ እንደሚጠራ አስታውቆ የቅስቀሳ ሥራ መሥራት በጀመረበት ጊዜ፤ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ሰሞኑን በዚያው ቀን ሰልፍ ለማድረግ ጥሪ ማቅረቡ ያታወቃል። በተለይ በኢህአዴግ የሰልፍ ጥሪ የሴትና ወጣት ማህበራት፣የመንግስት ሠራተኞች፣ የሀይማኖት ተቋማትና ሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጭምር በግዳጅ እንዲወጡ መታዘዛቸው፤ ሁኔታውን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ...
Read More »