መስከረም ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ በረከት ስምኦን በተመራው የኢህአዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ ውይይት ላይ ፣ የሀይማኖት አክራሪነት ከምርጫ 97 ቀጥሎ ከፍተኛ ፈታኝ አደጋ እንደሆነ ከተገለጸና ውይይት ከተካሄደ በሁዋላ የአገሪቱ ሲቪል ሰርቪስ የሀይማኖት ጉዳይን እንደ አንድ የእድገት መመዘኛ መስፈረት እንዲተገብር ስምምነት ላይ ተደርሷል። በጉባኤው ላይ የሐይማኖት አክራሪነት የመንግስትን ተቋም በማፈራረስ እና ተከታዮቹ ነፍጥ አንስተው መስዋእት እንዲሆኑ በማነሳሳት ከፍተኛ የሆነ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
እነወ/ሮ ሚሚ ስብሃቱ ፕሬስ ካውንሰል መመስረት አልቻሉም
መስከረም ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ምክርቤት ወይንም ፕሬስ ካውንሰል ለማቋቋም ኃላፊነቱን የተረከበው ጊዜያዊ ኮምቴ የካውንስሉን መስራች ጉባዔ መጥራት እንዳልቻለ ተጠቆመ፡፡ በኢህአዴግ ደጋፊነት በሚታወቁት ወ/ሮ ሚሚ ስብሃቱ የሚመራው ጊዜያዊ መስራች ኮምቴ ፕሬስ ካውንስሉን እንዲመሰረት ኃላፊነት ቢሰጠውም አመራሩ እርስበርስ ባለመግባባቱና ከብዙሃኑ ጋዜጠኞች አዎንታዊ ምላሽ ባለማግኘቱ የምስረታውን ጉዳይ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ጥሎታል፡፡ ይህ ኮምቴ በወ/ሮ ሚሚ ሊቀመንበርነት፣ በአቶ ...
Read More »የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ራዲዮ 3ተኛ ዓመት በጀርመን-ሙኒክ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።
መስከረም ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቅዳሜ ከቀኑ 14 ሰዓት ጀምሮ ሙሉ ሌሊቱን ጭምር በደማቅ ሁኔታ በተከበረው የኢሳት 3ኛ ዓመት በዓል ላይ ‘ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል። በዝግጅቱ ኢሳት ከየት ተነስቶ የት ላይ እንደደረሰ በስፋት ያብራሩት የድርጅቱ ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ነዓምን ዘለቀ፤ኢሳት ለወደፊቱ መድረስ ያለበትን ደረጃ አስመልክቶ የተሰነቀውን ራዕይ ጠቁመዋል። ከፓናል ውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል የኢህአፓው አመራር ዶክተር ዘነበ ...
Read More »የኢትዮጵያ አየር ሀይል መዳከሙን ካፒቴን አክሊሉ ተናገሩ
መስከረም ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ አየር ሃይል በመተው ሰሞኑን ግንቦት 7ትን ከተቀላቀሉት አብራሪዎች እና የበረራ አስተማሪዎች መካከል የተዋጊ ሄሊኮፕተር ተዋጊና አዛዥ የሆኑት ካፒቴን አክሊሉ መዘነ ዛሬ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ በአንድ ወቅት በገናናነቱ የሚታወቀው የኢትዮጵያ አየር ሐይል አሁን ያለበት ደረጃ የሚያሳፍር መሆኑን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ ሰፍኖ አየር ሀይሉ ተመልሶ የሚገነባበት ጊዜ እንደሚመጣ የገለጹት ካፒቴን አክሊሉ፣ እስከ ዛሬ ...
Read More »ተቃዋሚዎች በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳያደርጉ ተከለከሉ
መስከረም ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መስከረም 12 እና መስከረም 19 ሰማያዊ እና አንድነት ፓርቲዎች በተከታታይ የጠሩዋቸው ሰልፎች በመስቀል አደባባይ እንደማይካሄዱ የአዲስ አበባ መስተዳድር ህዝባዊ ስብሰባ ማስታወቂያ ክፍል አስታውቋል። ጽህፈት ቤቱ ይህን ያስታወቀው ከሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ጋር ውይይት ካደረገ በሁዋላ ነው። ይህንን ውሳኔ ተከትሎ ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ” ህዝባዊ አገልግሎት የሚሰጥ ቦታ ለዜጎች ሁሉ መብት የሆነውን ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ...
Read More »የደቡብ ነዋሪዎች በኑሮዋቸው መጎሳቆላቸውን ገለጹ
መስከረም ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በቆላማና ከፊል ቆላማ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ አርብቶአደሮች ባለፉት 20 ዓመታት በአካባቢው በተደጋጋሚ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ለከፍተኛ ጉስቁልና መዳረጋቸው ታውቋል። በቦረና ዞን ብቻ በ2005 ዓ.ም 30 ሺህ 216 እንስሳት በድርቅ ሲያልቁ፣ በ2004 ዓ.ም ደግሞ 10 ሺህ 609 እንስሳት አልቀዋል፡፡ በማኅበራዊ ጥናት መድረክ የአካባቢ ጉዳዮች ተመራማሪ የሆኑት አቶ አለባቸው አደም ከመልካም አስተዳደርና ከአየር ጸባይ ...
Read More »ግብጽ ወደ አደገኛ የግጭት ቀጣና ውስጥ እየገባች ነው
መስከረም ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ሙርሲ ስልጣናቸውን በሀይል ከተነጠቁበት ጊዜ ጀምሮ ግብጽ ሰላም ማግኘት አልቻለችም። የአገሪቱ መንግስት የፕሬዚዳንት ሙርሲን ደጋፊዎች ለማደን በሚያደርጉት ጥረት አንድ የፖሊስ ጀኔራል ተገድለዋል። መንግስት በርካታ የፕሬዚዳንቱን ደጋፊዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ሲያስታውቅ፣ ደጋፊዎቹ ግን ራሳቸውን መሰራያ በማስታጠቅ መንግስት ለመፋለም ቆርጠው መነሳታቸው ይነገርላቸዋል። መንግስት በያዘው አቋሙ ከገፋበት ግብጽ ዳግም ሶሪያ ልትሆን እንደምትችል ምሁራን ይናገራሉ። ከሁለት አመት ...
Read More »4 የአየር ሀይል አብራሪዎች ግንቦት 7ትን ተቀላቀሉ
መስከረም ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ አራት አብራሪዎች ፣ የበረራ አስተማሪዎች ስርአቱን ከድተው ግንቦት7ትን መቀላቀላቸው ታውቋል። ከኢትዮጵያ አየር ሀይል በመለየት ግንቦት 7ትን መቀላቀላቸውን ለኢሳት ያረጋገጡት የበረራ ባለሙያዎች በአየር ሀይል ውስጥ የተንሰራፋውን ዘረኝነትና አድሮ ለርምጃው እንደገፋፋቸው አመልክተዋል። በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ ከዘረኝነትና አድሎው ባሻገር በሰራዊቱ ውስጥ የተስፋፋው ሙስና ተቋሙን ለቀው የነጻነት ታጋዮችን ለመቀላቀል እንዳስወሰናቸው ...
Read More »ኢህአዴግ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሩን በመያዝ እየገመገመና እያሰለጠ ነው
መስከረም ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦህአዴድ፣ ብአዴን፣ ኢህዴንና ህወሀት ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ካለፈው እሁድ ጀምሮ በየክልሎቻቸው ተሰባስበው ግምገማ እያደረጉና ስልጠናም እየወሰዱ መሆኑን ከድርጅቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ለ10 ቀናት በሚቆየው ስልጠና አመራሮቹ እርስ በርስ ከመገማገም ባለፈ ስለ ልማት ሰራዊት አደረጃጀት፣ ስለ አንድ ለአምስት አተገባበር ፣ አክራሪነትና ኪራይ ሰብሳቢነት እንዲሁም በመጪው አመት ስለሚካሄደው አገራቀፍ ምርጫ ስልጠናዎች እና ውይይቶች ይካሄዳሉ። ተመሳሳይ ስልጠናዎችና ...
Read More »ሰማያዊና አንድነት ፓርቲዎች የጠሩዋቸውን ሰልፎች ተከትሎ መንግስት የጎዳና ላይ ነጋዴዎችን መበተን ጀመረ
መስከረም ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ሁለቱ ፓርቲዎች የጠሩዋቸውን ሰልፎች ተከትሎ በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የሚገኘው መንግስት በዛሬው እለት በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የሚገኙ ሊስትሮዎችን፣ በጎዳናዎች ላይ እቃዎችን የሚሸጡትን በጸጥታ ሀይሎቹ አማካኝነት እንዲሰበሰቡና ወደ አልታወቀ ስፍራ እየወሰዱዋቸው ነው። የሚታፈሱት ሰዎች ወዴት እንደሚወስዱ ባይታወቅም ከአንዳንድ ሰዎች ባገኘነው መረጃ ሰዎቹ ፓርቲዎቹ ያዘጋጁት ሰልፍ እሲከጠናቀቅ ታግተው ይቆያሉ። ሰማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ የሚያደርገው ...
Read More »