.የኢሳት አማርኛ ዜና

ባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞቹን አባረረ

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞች ባለፈው ነሀሴ ወር ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ በፋብሪካው አስተዳደር ላይ ያላቸውን ቅሬታ ገልፀው ነበር፡፡ ቦርዱ እና ማነጅመንቱ ሰራተኞቹን በመሰብሰብ መልስ እንደሚሠጡ ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም፣ ቃላቸውን በማጠፍ  በጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ.ም ሰራተኞቹን ለአመፅ አነሳስተዋል ተብለው የተፈረጁ 27 ሰራተኞች ከስራ አባረዋል ፡፡ በእለቱ የወጣው የማገጃ ደብዳቤ በፋብሪካው ...

Read More »

በደብረ-ብርሀን በማጅራት ገትር በሽታ ሰዎች እየሞቱ ነው

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወኪላችን ከስፍራው እንደዘገበው በበሽታው እስካሁን ከ4 በላይ ሰዎች ሞተዋል። 3 ሰዎች ደግሞ ሆስፒታል ተኝተዋል። በአዲስ አበባ የማጅራት ገትር በሽታ ክትባት መጀመሩን መዘገባችን ይታወሳል። የማጅራት ገትር ሕመም በተዋህሲን አማካይነት ተከስቶ የአንጎልን ህብለሰረሰር በተለይ ከራስ ቅል በታች ያለውን የሰውነት ክፍል የሚያጠቃ ሕመም ነው፡፡ በባክቴሪያ አማካይነት የሚከሰተው ማጅራት ገትር በሽታ በወረርሽኝ መልክ የሚተላለፍ ፣ በምድር ...

Read More »

ለመለስ ፋውንዴሽን ህዝብ የሰጠው መለስ ቀዝቃዛ ነው ተባለ

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመጋቢት ወር 2005 ዓ.ም መጨረሻ በይፋ የተመሠረተው የመለስ ፋውንዴሽን ዓላማውን ለማሳካት ከሕዝብ ገንዘብ በመዋጮ መልክ ለማሰባሰብ እያደረገ ያለው ጥረት የታሰበውን ያህል ውጤት እያስገኘ አለመሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ፡፡ በመለስ ፋውንዴሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 781/2005 መንግስታዊ ተቋም ሆኖ የተመሰረተው ይህው ፋውንዴሽን ቤተመጻህፍትና ሙዚየም ለማቋቋም በማሰብ ሕዝቡ ገንዘብ እንዲያዋጣ በየቀኑ በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ...

Read More »

ከአሸጎዳ የንፋስ ሃይል ማመንጫ በስተጀርባ ሙስና መኖሩን መረጃዎች አመለከቱ ፡፡

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ ሃይል ያመነጫል በሚል በ210 ሚሊዮን ዩሮ ወይም በ5 ቢሊዮን 200 ሚሊዮን ብር ገደማ የተገነባው የአሸጎዳ የንፋስ ሀይል ማመንጫ 120 ሜጋ ዋት ሀይል በማመንጨት፣ በአዳማ ከተገነባው ከሁለት እጥፍ በላይ የሚበልጥ ነው። ከ90 በመቶ በላይ በፈረንሳይ መንግስት የተሸፈነው ፐሮጀክት ሙስና እንደተፈጸመበት ከጸረ ሙስና ኮሚሽን የተገኘው መረጃ አመልክቷል። የንፋስ አውታሮች ለሚቆሙባቸው ቦታዎች ...

Read More »

በደቡብ ክልል የመምህራን ተቃውሞ እየተስፋፋ ነው

ጥቅምት ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መምህራን ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል  የመስከረም ወር ደሞዛቸው ያለፈቃዳቸው ተቀንሶ ከተሰጣቸው በሁዋላ የጀመሩት ተቃውሞ እየተስፋፋ መሆኑን ለኢሳት የሚደርሱት መረጃዎች ያመለክታሉ። የጨንጫ ወረዳ 7 ትምህርት ቤቶች መምህራን የተቆረጠው ደሞዛችን ካልተመለሰ ስራ አንሰራም በሚል አድማ ከመቱ በሁዋላ፣ በዛሬው እለት ደግሞ በጋሞጎፋ ዞን በምእራብ አባያ ወረዳ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን ” የተቆረጠብን ደመወዝ ...

Read More »

የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ ሶስት የአማራ ክልል አመራሮችን ማገቱን አስታወቀ

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ በአማራ ክልል ላኩማ ወረዳ ሁለት የሚሊሽያ ሀላፊዎችንና አንድ የወረዳ አስተዳዳሪን በቁጥጥር ስራ ማድረጉን ገለፀ፡፡ ንቅናቄው ሰሞኑን 22 የፖለቲካ አመራሮች በላኩማ ወረዳ በሚገኘው በሰላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በስብሰባ ላይ እንዳሉ በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ መልቀቁን ገልጾ ሶስቱን አመራሮች ግን አሁንም ድረስ በቁጥጥር ስር አድርጎ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ የተያዙት አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለው ...

Read More »

በአዲስአበባ ከተማ የማጅራት ገትር ወረርሽኝ በአዲስ መልክ ተቀሰቀሰ

ጥቅምት ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ከተማ ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር 2005 አካባቢ ተከስቶ የነበረው ማጅራት ገትር ወረርሽኝ እንደገና በአዲስ መልክ በመቀስቀሱ የክልሉ ጤና ቢሮ ሕዝቡን የመከተብ ስራ ላይ መጠመዱ ተሰማ፡፡ ክትባቱ በሁሉም ጤና ጣቢያዎች በመሰጠት ላይ ሲሆን ክትባቱን መውሰድ ያለባቸው ደግሞ ዕድሜያቸው ከ30 በታች የሆኑ ነዋሪዎች ብቻ መሆናቸው ለምን የሚል ጥያቄ አስነስቶአል፡፡ ምንጮቻችን እንደሚሉት መንግስት ...

Read More »

በጋምቤላ ለሞቱ የሰራዊቱ አባላት ካሳ ተከፈለ – ለሞቱ ነዋሪዎች ግን ካሳ አለመከፈሉ ታወቀ

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በጋምቤላ ክልል ንዌር ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ሚኒኛንግ ከተማ ተካሂዶ በነበረ ግጭት ለሞቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በነብስ ወከፍ 90 ሺህ ብር እንዲከፈል ተወሰነ፡፡ ለሞቱ ሲቪል ሰዎች የካሳ ክፍያ ሳይፈጸም መቅረቱን ግን ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል፡፡ የዞኑ ሚሊሺያዎች እና ነዋሪዎች ከመከላከያ አባላት ጋር ባደረጉት ግጭት ስምንት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሞተው ሰባት መቁሰላቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡ ከሞቱ እና ከቆሰሉት ...

Read More »

በአዲስአበባ የውሃ ችግርን ተባብሶ ቀጥሎአል

ጥቅምት ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስአበባ ከተማ የውሃ ሽፋን 94 በመቶ ደርሶአል ቢባልም በአሁኑ ወቅት መሃል አዲስአበባን ጨምሮ አብዛኛው አዳዲስ የማስፋፊያ አካባቢዎች በቂ የውሃ ሽፋን የማያገኙት ከ40 በመቶ አይበልጡም። የአዲስአበባ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ባለሰልጣን እንደሚናገረው የከተማዋ የውሃ ሽፋን እያደገ ቢመጣም ውሃን በቁጠባ የመጠቀም ልምድ ባለመዳበሩ እስከ40 በመቶ የሚደርስ ከፍተኛ ብክነት በከተማዋ ውስጥ አለ ብሎአል፡፡ ይህ ሁኔታም ያለውን ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሰሜን ኮርያ ዲፕሎማት በደቡብ ኮርያ ኢምባሲ ጥገኝነት ጠየቁ

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የሰሜን ኮርያ ዲፕሎማት ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩ ኮርያዊ በደቡብ ኮርያ ኢምባሲ ጥገኝነት መጠየቃቸው ተገለጸ፡፡ ስማቸው ይፋ ያልሆነው ዲፕሎማት የሚወክሉትን ሀገር ትተው ከአንድ ወር በፊት የደቡብ ኮርያን መንግስት አዲስ አበባ በሚገኘው ኢምባሲ በኩል ጥገኝነት መጠየቃቸውን የተለያዩ የሁለቱ ኮርያዎች መገናኛ ብዙሀን በመዘገብ ላይ ናቸው፡፡ ዲፕሎማቱ ወደ ደቡብ ኮርያ ኢምባሲ በመግባት ጉዞአቸውን እንዲያመቻችላቸው ጠይቀው ከአዲስ አበባ ወደ ደቡብ ኮርያ ማቅናታቸው ...

Read More »