ጥቅምት ፳፪(ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በክልሉ ለረጅም አመታት ኖረው በተለያዩ ምክንያቶች ከአካባቢው እንዲለቁ የተደረጉ አንዳንድ ሰዎች ለኢሳት እንደገለጹት ፣ መስተዳድሩ እንኳንስ የሌሎችን አካባቢዎች ህዝብ መብት ለማክበር ቀርቶ የክልሉን ነዋሪዎች መብት ማክበር አልቻለም ብለዋል። ከሌላ ክአካባቢዎች የመጡ በተለይም የአማራ ተወላጆች ሶማሊያ መናገር አትችሉም እየተባሉ ከስራ መባረራቸውን የገለጹት እኝህ ነዋሪዎች፣ በንግድ ስራ የሚተዳደሩና በጅጅጋ ቁልፍ የገበያ ቦታዎችን እና ቀበሌ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
አዲሱ ሌተናንት ጄኔራል በመቶ ሚሊዮን ብር የሚቆጠር ሀብት እንዳላቸው ታወቀ
ጥቅምት ፳፪(ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ሌተናንት ጄኔራል ሆነው የተሾሙት በሱዳን የሚገኘውን እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር በመሆን በጸጥታ መስከበር ስራ ላይ የተሰማራውን የኢትዮጵያ ጦር የሚመሩት ምናልባትም ጀኔራል ሳሞራ የነሱን ሊተኩ ይችላሉ የሚባሉት ሌተናንት ጀኔራል ዮሀንስ ገብረመስቀል ተስፋማርያም በአዲስ አበባ የገነቡዋቸው የንግድ ህንጻዎች በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዋጋ እንደሚያወጡ ለእርሳቸው ቅርብ የሆኑ ሰዎች ገልጸዋል። ጀኔራሉ ባለፈው አመት መጋቢት ...
Read More »የፓኪስታን የታሊባን መሪ ተገደለ
ጥቅምት ፳፪(ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሀኪሙላ መሱድ የሚባለው የፓኪስታን ታሊባን መሪ የተገደለው በአሜሪካ ሰው አልባ የጦር ጅቶች መሆኑን አለማቀፍ ሚዲያዎች ቢዘግቡም እስካሁን ከአሜሪካ መንግስት በኩል የተሰጠ ማረጋገጫ የለም። ግለሰቡ በአሜሪካ ከሚፈለጉ አሸባሪዎች ማካከል አንዱ ነው። አሜሪካ ግለሰቡ ያለበትን ለጠቆመ 5 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገብታ ነበር። የመሱድ ምክትል ባለፈው ግንቦት ወር በተመሳሳይ መንገድ መገደሉ ይታወሳል። የፓኪስታን መንግስት ...
Read More »በባህርዳር ከተማ ከፍተኛ ፍተሻ እየተካሄደ ነው
ጥቅምት ፳፩(ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምክንያቱ በውል ባይታወቅም ካለፉት 4 ቀናት ጀምሮ በከተማዋ ከፍተኛ ፍተሻ እየተካሄደ እንደሆነ የዘጋብያችን መረጃ ያመለክታል። በተለይ ዛሬ በከተማዋ መውጫና መግቢያ በሮች ላይ ሰዎች ከመኪናዎች እና ባጃጆች ላይ እንዲወርዱ እየተደረገ በጥብቅ ተፈትሸዋል። አንዳንድ ወገኖች መንግስት ጸረ ሰላም እና አሸባሪዎች በከተማዋ ገብተዋል የሚል ወሬ እንደሚያስወራ ሲገልጹ፣ ሌሎች ነዋሪዎች ደግሞ የከተማውን ህዝብ ለማስበረገግ ሆን ብሎ ...
Read More »በኮንዶሚኒየም ቤት ግንባታ የቻይና ኩባያዎች ሊሰማሩ ነው
ጥቅምት ፳፩(ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዓመት 50ሺ የኮንዶምኒየም ቤቶችን ለመገንባት የያዘው ዕቅድ ከባድ ትችትን ያስከተለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዓመት ከ 100ሺ በላይ የቤቶች ግንባታ ለማከናወን ፊቱን ወደቻይና ኩባንያዎች ማዞሩ ተሰማ፡፡ አስተዳደሩ ከ800ሺ በላይ የኮንዶምኒየም ፣ ከ 136 ሺ በላይ የ40 በ60 ቤት ፈላጊ ነዋሪዎችን የመዘገበ ሲሆን ከዚህ ፍላጎት ጋር በማይጣጣም መልኩ በዓመት 50ሺ ቤቶች ገደማ ለመስራት ...
Read More »በዳኞች መካከል የሚታየው አለመግባባት የፍርድ ሂደቱን እያጓተተው ነው
ጥቅምት ፳፩(ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በከፍተኘው ፍርድ ቤት ባለው የአስተዳደር ቊንጮ ማለትም በዋናው ፕሬዚዳንት በዳኛ ውብሸት ሽፈራውና በምክትሉ ማሃል ያለው አለመስማማት እየጨመረ በመሄዱ የፍርድ አሰጣጥ ሂደቱን እያበላሸው መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች ገለጹ ። አሁን ባለው አሰራር ተሰሚነት ያለው የኢሃዴግ አባል የሆነው ምክትሉ ሲሆን ፣ ፕሬዘዳንቱ የኢሃዴግ አባል ባለመሆኑ ተሰሚነት አጥቷል ይላሉ ምንጮች:። ሌሎች ዳኞችም ከዋናው ፕሬዘዳንት ...
Read More »አገር ቤት የሚገኘው ሲኖዶስ ከውጭ ከሚገኘው ጋር የተጀመረው ድርድር እንዲቀጥል ወሰነ
ጥቅምት ፳፩(ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቅዱስ ሲኖዶሱ ሰሞኑን ሲያደርግ የነበረውን ምልዓተ ጉበኤ ሲያጠናቅቅ ባወጣው የአቋም መግለጫ ፣ በውጭ አገር ከሚገኙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ጋር ተጀምሮ የነበረው እርቀ ሰላም ወደ ፊት እንዲቀጥል እና ቤተክርስቲያን አንድነት እንዲጠናከር ወስኗል። የኦሮቶዶክስ ሀይማኖት ተከታዮች ቆጠራ እንዲካሄድና የቤተክርስቲያኒቷ ታሪክ በደንብ ተጠንቶ እንዲቀርብም ወስኗል። ከፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ተወክለው የመጡ ሰዎች በቅርቡ ስለ አክራሪነት የሀይማኖት ...
Read More »አርሶ አደሮች በማዳበሪያ እና በምርጥ ዘር እዳ እየተዋከቡ ነው።
ጥቅምት ፳፩(ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ እና በአማራ ክልሎች ያሉ አርሶ አደሮቹ ለኢሳት እንደተናገሩት ውጤታማ ባልሆኑበትና በግዴታ እንዲገዙ በተጠየቁት የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ እዳ እየተዋከቡ ነው። እዳችንን መክፈል አልቻንም የሚሉት አርሶ አደሮች መንግስት መፍትሄ እንዲፈልግላቸው ጠይቀዋል። ግብርና ሚኒስቴር ለረጅም ጊዜ በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ የዋለውን ዳፕ የተባለውን ማዳበሪያ ውጤታማ አልሆነም በሚል እንደሚቀይር ማስታወቁ ይታወቃል። ይሁን እንጅ አርሶአደሮቹ ውጤታማ አልሆነም ...
Read More »ኮሜዲያን አብረሀም አስመላሽ አረፈ
ጥቅምት ፳፩(ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቁም ነገር አዘል በሆኑ ቀልዶቹ የሚታወቀው ኮሜዲያን አብረሀም ከጀርባ ህመም ጋር በተያያዘ ሲሰቃይ ቆይቷል። ከጥቂት ወራት በፊት ወደ አውሮፓ በመምጣት በጀርመን አገር ህክምናውን ተከታትሎአል። አብርሀም በማእደ ኢሳት ዝግጅት ላይ ቀርቦ ለኢትዮጵያ ህዝብና የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ የረዱትን ወገኖች ማመስገኑና ጤናውም መሻሻልእያሳየ እንደሆነ መግለጹ ይታወሳል ፡፡ ከዲስከ መንሸራተት ጋር በጀርመን ሲታከም የቆየው አብራሃም ህመሙ ...
Read More »የስሚንቶ ፋብሪካዎች የገበያ ችግር እንዳጋጠማቸው ተዘገበ
ጥቅምት ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሪፖርተር ዛሬ ባወጣው ዘገባ በአገሪቱ የሚገኙ ሶስቱ ታላላቅ ስሚንቶ ፋብሪካዎች በአመት 12 ሜትሪክ ቶን ሲሚንቶ የማምረት አቅም ቢኖራቸውም በገበያ ውስጥ የሚገኘው ስሚንቶ ድምር ከ5 ሚሊዮን አይበልጥም። አብዛኛውን ስሚንቶ የሚገዛው መንግስት ሲሆን፣ የግሉ ዘርፍ ድርሻ ቀዝቃዛ መሆኑ ተዘግቧል። የሼክ ሙሀመድ አላሙዲን ንብረት የሆነው ደርባን ኩባንያ የዋጋ ቅናሽ በማድረግ በኩንታል 209 ብር እየሸጠ፣ ለደንበኞቹ ቤታቸው ...
Read More »