ታህሳስ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሪክ ማቻር ከተደበቁበት ቦታ ሆነው ለአለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን እንደገለጹት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ተቃዋሚዎቻቸውን ለመምታት የተጠቀሙበት ዘዴ ነው ብለዋል። የፕሬዚዳንቱ ጠባቂዎች እርስበርሳቸው መጋጨታቸውን የገለጹት የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ማቻር፣ ይሁን እንጅ የሳልቫኪር መንግስት አጋጣሚውን ተጠቅሞ ተቀናቃኞችን እያሰረ ነው ሲል አክለዋል። በአገሪቱ ውስጥ የሚታየው ውጥረት በማየሉ አዲሲቷ አፍሪካዊት አገር በእርስበርስ የጎሳ ጦርነት ትታመሳለች ተብሎ ይፈራል። ሪክ ማቻር ያሉበት ቦታ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በኢትዮጵያ በዲያስፖራው ከተያዙ 744 ፕሮጀክቶች ውስጥ ሩቡ እንኳን በአግባቡ ተግባራዊ አልሆኑም ተባለ፡፡
ታህሳስ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳያስፖራ ተሳትፎ ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ጀኔራል የተገኘ መረጃ በግምት ከ2-3 ሚሊዮን የሚደርሱ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ የአለም ከፍሎች ቢኖሩም ለአገራቸው ያላቸው አስተዋጽኦ ግን አነስተኛ ነው ብሎአል። አውሮፖና አሜሪካ የኢትዮጵያውያኑ ዳያስፖራዎች ዋነኛ መዳረሻዎች ሲሆኑ በርካታ የዳያስፖራው አባላትም በእነዚሁ አህጉራት ይገኛሉ ይላል። እውቅና ያገኙ ተመራማሪዎች ፤ የጤና ባለሙያዎች ፤የዩንቨርስቲ መምህራን ፤በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ...
Read More »ለሚቀጥሉት ሶስት አመታት ለመንግስት ሰራተኛው የሚጨመር ደሞዝ አይኖርም ተባለ
ታህሳስ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመንግስት ሰራተኛው በከፍተኛ የኑሮ ውድነት እየተሰቃዩ መሆኑን እንደሚያዉቁ የተናገሩት ሁለት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣኖች፣ ይሁን እንጅ በሚቀጥሉት ሶስትና አራት አመታት በጉልህ የሚታይ ደሞዝ ጭማሪ እንደማይኖር ገልጸዋል። በየአምስት አመቱ የቤተሰብ ፍጆታቸው በተመረጡ ናሙናዎች ተወስዶ በሚለካው የግሽበት አሃዝ ስሌት መንግስት የኑሮ ውድነቱ በአንድ አሃዝ መውረዱን ቢገልጽም፣ የኑሮ ውድነት ግን አለመርገቡን ነዋሪዎች ይናገራሉ። የማእከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ...
Read More »በአዲስአበባ አስተዳደር የተጠያቂነት ችግርን በመፍራት ውሳኔዎችን ማስተላለፍ አልተቻለም ተባለ
ታህሳስ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለይ ከመሬት ይዞታ ጋር በተያያዘ ውሳኔ የሚያስፈልጋቸውና በታችኛው አመራር ጭምር ሊፈቱ የሚገቡ ጉዳዮች ተጠያቂነትን ከመፍራት አኳያ ወደ መካከለኛና ከፍተኛ አመራሩ የመግፋት ጉዳይ በተደጋጋሚ መከሰቱ አሳሳቢ መሆኑ ሰሞኑን በተደረገው ግምገማ ላይ ቀርቧል፡፡ አስተዳደሩ የ2006 የመጀመሪው ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም በገመገመበት መድረክ ላይ ተጠያቂነትን ለመሸሽ ሲባል ስራዎችን ወደላኛው አካል የመግፋት ጉዳይ በበጀቱ ኣመቱ አሳሳቢ ችግር ሆኖ ...
Read More »በደቡብ ሱዳን ግጭቱ አልበረደም
ታህሳስ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ተሞክሮ የነበረው መፈንቅለ መንግስት መክሸፉን በተናገሩ ማግስት ግጭት መነሳቱን ረዩተርስ ዘግቧል። አልፎ አልፎ ይሰማ የነበረው ተኩስ በተከታታይ መሰማቱን የገለጸው ረዩተርስ፣ የአሜሪካ ልዩ ልኡክ የሆኑት ዶናልድ ቡዝ ሁኔታው ውጥረት የበዛበትና ያልተረጋጋ መሆኑን ገልጸዋል። እስካሁን ባለው መረጃ 26 ሰዎች እንደተገደሉ ቢታወቅም አንዳንድ የመገናኛ ብዙሀን ከ60 በላይ ወታደሮች እንደተገደሉ እየዘቡ ነው። ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር የቀድሞው ምክትላቸው ስልጣን ...
Read More »በጅጅጋ የተካሄደው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃ ማለፉ በክልሉ ሰላም አለመኖሩን ያመለክታል ሲሉ አንድ ታዛቢ ተናገሩ
ታህሳስ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመንግስት የሀላፊነት ቦታ ላይ የሚገኙ አንድ ስማቸው እንዳይገለጸት የፈለጉ ሰው ለኢሳት እንደተናገሩት በክልሉ በቆዩባቸው ቀናት የታዘቡት ነገር ቢኖር በክልሉ የሰላም እጦት ዋናው ችግር መሆኑን ነው። ምንም እንኳ መንግስት ያለምንም ችግር በአሉ መጠናቀቁን ቢገልጽም እውነታው ግን ከዚህ የተለየ እንደነበር ሃላፊው ይናገራሉ። በከተማዋ ዳርቻዎች ታንኮች፣ ከባድ መሳሪያ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ፣ ልዩ ኮማንዶችና እና እስካፍንጫቸው የታጠቁ እግረኛ ...
Read More »የኢህአዴግ አመራር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሐኖምን ገሰጸ
ታህሳስ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የወደፊቱ ጠ/ሚንስትር ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ የሚነገርላቸው ዶ/ር ቴዎድሮስ ግሳጼው የቀረበባቸው ” በሳውድ አረቢያ ላይ ተመጣጣኝ የአጸፋ እርምጃ እንወስዳለን” ብለው መናገራቸውን ተከትሎ ነው። ኢህአዴግ በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር አስቸኳይ ስብሰባ የጠራ ሲሆን ዶ/ር ቴዎድሮስም ” ያለግንባሩ ውሳኔ እንዲህ አይነት ጠንካራ አስተያየት ለምን እንደሰጡ እንዲያብራሩ ተጠይቀዋል። “ዶ/ር ቴዎድሮስ በቂ ማብራሪያ ለመስጠት ባለመቻላቸው ግለ-ሂሳቸውን እንዲያወርዱ ተጠይቀዋል። ከፓርቲው ይልቅ ...
Read More »አንድ ወጣት የመንግስት ሰራተኛ መንግስትን በመቃወም ራሱን አጠፋ
ታህሳስ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሲዳማ ዞን በአለታ ጩኮ ወረዳ የግብርና ፅ/ቤ ባለሙያ የሆነው ወጣት ነጋልኝ ፀጋዬ በሙያው ለአመታት ህብረተሰቡን ሲያገለግል ቢቆይም የመንግስትን አሰራር በተደጋጋሚ በመተቸቱ፣ ከመስርያ ቤቱ ኃላፊዎች ጋር በተለያዩ ግዜያት ግጭት ውስጥ ከመግባቱም በላይ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ሳይቀር ደርሶት ነበር። ወጣት ነጋልኝ ፀጋዬ መንግስትን በግልፅ በመቃወም፤ መስተካከል ያለበትን ጉዳይ በግልፅ መናገር ልዩ ባህሪው እንደነበር የሚናገሩት ጓደኞቹ፣ በዚህ ባህሪው ...
Read More »በደቡብ ሱዳን የተደረገው መፈንቅለ መንግስት መክሸፉን የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ተናገሩ
ታህሳስ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲሲቷ አገር መሪ የሆኑት ሳልቫኪር የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር ታማኝ ወታደሮች መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ሌሊቱን ተኩስ መጀመራቸውን ተናግረዋል። ችግሩ በቁጥጥር ስር መዋሉን የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ እንዲህ አይነቱን ድርጊት እንደማይታገሱትና ሙከራውን ባደረጉት ላይ ሁሉ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስዱ ተናግረዋል። የአገሪቱ ቴሌቪዥን ከጠፋ ከሰአታት በሁዋላ እንደገና ስራ ጀምሯል። እስካሁን ድረስ ምን ያክል ሰዎች እንደሞቱ አልታወቀም። በደቡብ ሱዳን ...
Read More »ለጋዜጠኛ ኤፍሬም በየነ ህክምና የሚውል የእራት ግብዣ ተዘጋጀ
ታህሳስ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቀረረበባቸው የፕሬስ ክስ ወደ አዋሳ በተጉዋዙበት ወቅት በድንገት በተከሰተ የተሸከርካሪ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበትን የኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ አዘጋጅ ለሆነው ለወጣት ኤፍሬም በየነ የሕክምና ወጪ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ምሽት ሰኞና ማክሰኞ በአዲስአበባ እንደሚካሄድ ከዕርዳታ አስተባባሪዎች መካከል አንዱ ለሪፖርተራችን ገልጿል፡፡ በዚህ የእራት ምሽት ላይ 500 ብር ዋጋ ያላቸው ትኬቶች ተዘጋጅተው በመሸጥ ላይ ሲሆኑ በተለይ ጋዜጠኞች ...
Read More »