ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወደዓረብ አገራት ዜጎች የሚያደርጉት ጉዞ ከ2003 ዓ.ም በኋላ በአስደንጋጭ መልኩ ከ4ሺህ ወደ 198 ሺህ ማደጉን ዶ/ር ዘሪሁን ከበደ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ይፋ አደረጉ፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው ለንባብ በበቃው “ዘመን” ከተባለው መንግስታዊ መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፤ በ2002 ዓ.ም ሚኒስቴር መ/ቤቱ መሰረታዊ የሥራ ሂደት ጥናት አጥንቶ ተግባራዊ ሲደርግ ከ3-5 ሺህ ሰዎች በዓመት ሊጓዙ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ከኢሳት ጋር በተያያዘ የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት እየተወዛገቡ ነው
ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ለኢሳት መረጃ በመስጠት ድርጅቱን ከውስጥ ሆነው የሚቦረቡሩ ሃይሎች አሉ በማለት እርስበርስ መወዛገባቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። አቶ በረከት ለሚኒስትሮችና ለኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ያደረጉት ንግግር በኢሳት ከተለቀቀ በሁዋላ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች እርስ በርስ እየተወነጃጀሉ ነው። የኢህአዴግ አንዳንድ ከፍተኛ አመራሮች ውስጣችን ማጥራት አለብን በሚል ትናንትና ዛሬ ለአመራሮች ማስጠንቀቂያ ሲሰጡ ውለዋል። ኢሳት ...
Read More »የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ በባህር ዳር ሊካሄድ ነው
ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከጥር 16-18 ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው የአፍሪካ ሚኒስትሮችና አምባሳደሮች ስብሰባ የአማራ ክልል ም/ቤት በቻይና ድጋፍ ባሰራው አዲስ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል፡ ህብረቱ አፍሪካ በ2063 ስለምትከተለው አቅጣጫ ይነጋገራል ተብሎአል። የአፍሪካ ህብረት ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ የኢትዮጵያ ከተሞች ስብሰባ ሲያዘጋጅ የመጀመሪያው ይሆናል።
Read More »አርሶ አደሩን እንደፈለገ ብናደርገው በኢህአዴግ ላይ አይነሳም ሲሉ አቶ በረከት ተናገሩ
ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን ለመንግስት ሚኒስትሮችና ለከፍተኛ የኢህአዴግ አመራሮች በተዘጋጀው የምርጫ ውይይትና ግምገማ ላይ ባቀረቡት ንግግር ላይ እንደገለጹት አርሶ አደሩ እስካሁን በተሰረላት ስራ በመርካቱ ” መንግስት ሰላማዊ ሰልፍ ውጣ ቢለው ይወጣል፣ መንግስት ተኛ ቢለው ይተኛል፣ ግፍ ብንፈጽም አርሶአደሩ ይህን መንግስት ምንም አይለውም፣ ይሸከመዋል” ብለዋል። 30 በመቶ የሚሆነውን ...
Read More »ኢትዮጵያ በአለም የምግብ እጥረትና ባልተመጣጠነ ምግብ የመጨረሻውን ደረጃ ያዘች
ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦክስፋምን ጥናት መነሻ በማድረግ ረዩተርስ እንደዘገበው በምግብ አቅርቦት፣ በምግብ ጥራትና በምግብ ዋጋ ኢትዮጵያ ከ125 አገራት ከቻድ በመቀጠል የመጨረሻውን ደረጃ ይዛለች። በአለም ላይ የተመጣጠነ ምግብ በማቅረብ፣ በምግብ ዋጋና በጥራት ሆላንድ አንደኛ ሆና ስትመረጥ ፈረንሳይና ስዊዝርላንድ ይከተላሉ። አሜሪካ 21ኛ ደረጃ ስትይዝ ከአንድ እስከ 10 ያሉትን ደረጃዎች የአውሮፓ አገራት ይዘውታል። የኦክስፋም ጥናት ላለፉት 23 አመታት ኢትዮጵያን ...
Read More »ቻይና የጃፓኑ መሪ ኢትዮጵያን በመጎብኘታቸው ተቃውሞዋን ገለጸች።
ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አሶሸትድ ፕሬስ እንደዘገበው የቻይና የአፍሪካ ህብረት ተወካይ የሆኑ አንድ ባለስልጣን ኢትዮጵያን በመጎብኘት ላይ ያሉትን የጃፓኑን ጠ/ሚ ሽንዞ አቤን ችግር ፈጠሪ ብለዋቸዋል። በአይቮሪኮስት፣ ሞዛምቢክና ኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ወደ አፍሪካ የመጡት ጠ/ሚ አቤ ለአፍሪካ አገራት ከፍተኛ የእርዳታ ገንዘብ ለመለገስ ቃል በመግባት የቻይናን ተጽእኖ ለመቋቋም ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ጋዜጣው ዘግቧል። .በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደርና ...
Read More »በኢትዮጵያ ትላላቅ ከተሞች የሚታየው የውሀ እጥረት እንደቀጠለ ነው
ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአገሪቱ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ያለው የውሀ አቅርቦት አሳሳቢ እየሆነ ባለበት ሰአት በመቀሌና በአዳማ የሚታየው ከፍተኛ የውሀ እጥረት ነዋሪዎችን በእጅጉ እያስመረረ ነው። በመቀሌ አንዳንድ አካባቢዎች ካለፉት 4 ወራት ጀምሮ ውሀ ተቋርጧል። በአዳማም እንዲሁ አንዳንድ አካባቢዎች ለረጅም ቀናት ውሃ በመቋረጤ ነዋሪዎች ምሬታቸውን እየገለጹ ነው ። መንግስት የአገሪቱ የንጹህ መጠጥ ውሀ ሽፋን 61 በመቶ ...
Read More »በደቡብ ሱዳን የሚካሄደው አስከፊ ጦርነት እንደቀጠለ ነው
ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሁለቱም ተፋላሚ ሃይሎች በአዲስ አበባ የሰላም ድርድር እያደረጉ ቢሆንም፣ ጦርነቱ ግን በመሬት ላይ እየተካሄደ መሆኑን የሚወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ። ከቀናት በፊት በነዳጅ ሀብቱ የበለጸገው አፐር-ናይል ስቴት የተበላውን ግዛት ዋና ከተማ ማላካልን መቆጣጠራቸውን የመንግስት ሃይሎች ቢያስታውቁም፣ የአማጽያኑ መሪ የሆኑት ሪክ ማቻር ከተማዋን መልሰው መቆጣጠራቸውን አስታውቀዋል። የአማጽያኑ የድል ወሬ እንደተሰማ መንግስት ጦርነት የተካሄደ በሆንም፣ ከተማዋ ...
Read More »የግብጽ ህዝብ ለአዲሱ ህገ መንግስት ድምጽ ሰጠ
ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡት የግብጹ መሪ ሙሀመድ ሙርሲ በወታደሮችና በተቃዋሚዎች ድጋፍ ከስልጣን ከተወገዱ በሁዋላ የሽግግር መንግስቱ አዲስ ህገመንግስት በማርቀቅ ድምጽ እንዲሰጥበት አድርጓል። ባለፉት ሁለት ቀናት በተሰጠው ድምጽ አብዛኛው ህዝብ አዲሱን ህገመንግስት ይደግፋል ተብሎ ይጠበቃል። በአዲሱ ህገመንግስት አንድ ፕሬዚዳንት ለ2 ጊዜ ብቻ የሚመረጥ ሲሆን ፓርላማውም ፕሬዚዳንቱን ከስልጣን የማንሳት መብት ተሰጥቶታል። ህገመንግስቱ እስልምና የአገሪቱ ብሄራዊ ...
Read More »ኢህአዴግ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ መመሪያን መተውን አስታወቀ
ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን በቅርቡ ከሚኒስትሮች እና ከኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይትና ግምገማ ላይ ” ህዝቡን ለመምራት የሚነደፉ ንድፈ ሀሳቦች ( ቲዮሪዎች) በየጊዜው ካልተሻሻሉ የሚዝጉ በመሆናቸው አብዮታዊ ዲሞክራሲ በልማታዊ ዲሞክራሲ እንዲተካ ተደርጓል ብለዋል። የኢህአዴግ መንግስት ይበልጥ የሚገለጸው በአብዮታዊ ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ሳይሆን በልማታዊ ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ነው ...
Read More »