በኢትዮጵያ ትላላቅ ከተሞች የሚታየው የውሀ እጥረት እንደቀጠለ ነው

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአገሪቱ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ያለው የውሀ አቅርቦት አሳሳቢ እየሆነ ባለበት ሰአት በመቀሌና በአዳማ የሚታየው ከፍተኛ የውሀ እጥረት ነዋሪዎችን በእጅጉ እያስመረረ ነው። በመቀሌ አንዳንድ አካባቢዎች ካለፉት 4 ወራት ጀምሮ ውሀ ተቋርጧል። በአዳማም እንዲሁ አንዳንድ አካባቢዎች ለረጅም ቀናት ውሃ በመቋረጤ ነዋሪዎች ምሬታቸውን እየገለጹ ነው ።

መንግስት የአገሪቱ የንጹህ መጠጥ ውሀ ሽፋን 61 በመቶ መድረሱን  ቢናገርም፣ ወተር ዶት ኦርግ የተባለው ድረገጽ እንዳመለከተው በኢትዮጵያ 34 በመቶ የሚሆነው የህብረተሰብን ክፍል ብቻ ነው የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሆነው።