ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቀድሪያ እንድሪስ የተባለች ኢትዮጵያዊት ወጣት በ6 የሱዳን ወጣቶች እጅግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ ስትደፈር የሚያሳይ ቪዲዮ ኢሳት የደረሰው ሲሆን ፣ ካርቱም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ የዲያስፖራ ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ አረጋ ልጂቷ መደፈሩዋን አምነው ተጨማሪ መረጃ ለመስጠት ግን ከፍተኛ ባለስልጣኖች መፍቀድ አለባቸው በሚል ዝርዝር ጥያቄዎችን ለመመለስ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። ጥቅምት ወር አካባቢ ቤት ለመከራየት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ሰመጉ በቁጫ ከ400 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን አንድ ሰው መገደሉን ገለጸ
ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ፣ የአሁኑ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ እየተባለ የሚጠራው አንጋፋው የሰብአዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት ባወጣው 129 ልዩ መግለጫ ” የሚለቀቁትን ሳይጨምር በሰላም በር ፖሊስ ጣቢያ 198 ሰዎች ፣በአርባ ምንጭ ማረሚያ ቤት 212 ሰዎች ” መታሰራቸውን እና ከሚደርሰው መንገላታት እና ጥቃት ለማምለጥ በሺህዎች የሚቆጠሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ወደ አጎራባች አካባቢዎች መሰደዳቸውን” ገልጿል። ቤቶች ...
Read More »በኢትዮጵያ 6 ሚሊየን ሕዝብ ስር በሰደደ የምግብ ዋስትና ችግር ውስጥ ነው ተባለ
ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እ.ኤ.አ በ2013 ለሁለተኛው አጋማሽ ማለትም ከጁላይ እስከ ዲሴምበር የአስቸኩዋይ የእለት ጊዜ እርዳታ ለሚያስፈልገው 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ሕዝብ የሚውል 162 ሺህ176 ሜትሪክ ቶን ምግብ ውስጥ ማሙዋላት የተቻለው 69 በመቶ ያህሉን ብቻ መሆኑን፣ 6 ሚሊየን ያህል ስር የሰደደ የምግብ ዋስትና ችግር ያለባቸው ቤተሰቦች በሴፍትኔት መታቀፋቸውን የግብርና ሚኒስትሩ አስታወቁ፡፡ ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበው ዛሬ ...
Read More »የአሜሪካ ኮንግረስ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው እርዳታ ህዝብ የማያፈናቅልና የሰብአዊ መብት ጥሰት የማያባብስ መሆኑ እንዲረጋገጥ የሚያደርግ ውሳኔ አሳለፈ።
ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኦክላንድ የምርምር ተቋም ውሳኔውን ታሪካዊ ብሎታል። በኮንግረሱ የጸደቀው ኦምኒበስ አፕሮፕሬየሽንስ ቢል እየተባለ የሚጠራው ህግ (Omnibus Appropriations Bill) አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው እርዳታ ዜጎችን ለማፈናቀል እንደማይውል፣ ይህንንም ተከትሎ ሰብአዊ መብቶች እንዳይጣሱ ያረጋግጣል። በኦሞ ሸለቆና በጋምቤላ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ነዋሪዎችን በማፈናቀል በሚደረገው ልማት ላይ የአሜሪካ እርዳታ ጥቅም ላይ እንዳይውል ህጉ ይከለክላል። የአሜሪካ እርዳታም ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ሃይሎች 2 የኦብነግን መሪዎች አፍነው መውሰዳቸውን ግንባሩ ገለጸ
ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ለኢሳት በላከው መረጃ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ኬንያ የሚገኙት የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች ሱሉብ አህመድና አሊ ሁሴን በኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ታፍነው ወደ አልታወቀ ቦታ ተወስደዋል። መሪዎቹ የታፈኑት ናይሮቢ ውስጥ ሲሆን፣ ከመንግስት ጋር ለሚደረገው ሶስተኛ ዙር ውይይት ዝግጅት እያደረጉ ነበር። ግንባሩ በመግለጫው ከዚህ ቀደምም የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የኦብነግ መሪዎችን ሲገድሉና ሲያፍኑ ...
Read More »በእስር ላይ የሚገኘው እውቁ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የ2014 የፔን አለማቀፍ ሽልማት አሸናፊ ሆነ
ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የድርጅቱ ሊቀመንበር የሆኑት ቶማስ ብሩኒጋርድ ” እስክንድር አፋኝ የፕሬስ ህግ ባለበት አገር በድፍረት ለመጻፍ በመቻሉ ሽልማቱ እንደተሰጠው ገልጸው፣ የኢትዮጵያ መንግስት እስክንድርን ጨምሮ በአሸባሪነት ታስረው የሚገኙትን ሰሎሞን ከበደ፣ ውብሸት ታየ፣ ርእዮት አለሙ እና የሱፍ ጌታቸውንም እንዲለቅ ጠይቀዋል። የፔን አለማቀፍ ሽልማት ለፕሬስ ነጻነት ለሚታገሉት ጋዜጠኞች በእየአመቱ የሚሰጥ ሽልማት ነው። ከዚህ በፊት ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌናም ...
Read More »የአረና ትግራይ መሪዎች ለቅስቀሳ በሄዱበት አዲግራት ተደበደቡ
ጥር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነባሩ የቀድሞው የህወሀት ታይ እና አሁን የአረና ከፍተኛ አመራር አቶ አስገደ ገብረስላሴ፣ በማህበራዊ ሚዲያዎች በመጻፍ የሚታወቀው ና የመቀሌ ዩኒቨርስቲ መምህር አብረሃ ደስታ እንዲሁም የፓርቲው የአመራር አባል አቶ አምዶም ገ/ስላሴ እሁድ እለት ከአዲግራት ህዝብ ጋር ለመነጋገር ወደ ስፍራው ቢያቀኑም በከተማው የደህንነት ፣ የፖሊስና የቀበሌ ሹሞች የሚመሩ ወጣቶች ድብደባ በመፈጸማቸው ስብሰባውን ማከሄድ ሳይችሉ ...
Read More »በሽብርተኝነት ህጉ ውይይት ስም የአዲስ አበባ ህዝብ እየተሸበረ ነው ሲሉ አንዳንድ ተወያዮች ገለጹ
ጥር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በአዲስ አበባ ውስጥ ለሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞችና በተዋረድም ከህዝቡ ጋር እተደረገ ባለው የሽብርተኝነት ህግ ውይይት፣ ነዋሪዎች ጥላቸውን እንኳን ማመን እንደሌለባቸው በአሰልጣኞች እየተነገራቸው ሲሆን፣ በስልጠናው ላይ የተካፈሉ አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞች፣ ስለሽብረተኝነት ልንማር ሂደን ተሸብረን መጣን ሲሉ ተናግረዋል። በመንግስት ከፍተኛ አመራሮች የተዘጋጀው የማሰልጠኛ ሰነድ ኢሳት እጅ የገባ ሲሆን፣ ሰነዱ ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን ቆሞ ...
Read More »በቁጫ ከታሰሩት መካከል 13 ቱ ፍርድ አገኙ
ጥር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥር 16፣ 2006 ዓም ባስቻለው ችሎት በእነ አቶ ደፋሩ ዶሬ መዝገብ የተከሰሱ 13 ሰዎች በሙሉ በ2 አመት ከ9 ወራት እስር እንዲቀጡ ወስኗል። በውሳኔው መዝገብ ላይ እንደተመለከተው እስረኞቹ የተፈረደባቸው “ እኛ ወይም ቁጫ የጋሞ ብሄረሰብ አይደለንም በሚል ህዝብን አነሳስታችሁዋል፣ ህገወጥ ስብሰባ አድርጋችሁዋል፣ እንዲሁም የጸረ- ህዝብ አቋም አራምዳችሁዋል” ...
Read More »በኖርዌይ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
ጥር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “ባልመረጥነው መጅሊስ አንተዳደርም! ያላመንንበትን የሀይማኖት አስተምህሮ አንቀበልም! የህዝበ-ሙስሊሙ የትምህርት ተቋም የሆነው አወሊያ ትምህርት ቤት በገለልተኝነት ይተዳደር” የሚሉ የመብት ጥያቄዎችን በማንሳታቸው የ አሸባሪነት ክስ የተመሰረተባቸው የሙስሊም አመራሮች ወደ ወህኒ ከወረዱ ከሁለት ዓመታት በላይ ተቆጠሩ። ለሁለት ዓመታት ከዘለቀው የፍትህ ሂደት በሁዋላ በቅርቡ ለብይን በተቀጠረው ችሎት ላይ በብዘዎች ሰንድ ታሳሪዎቹ በሙሉ ይፈታሉ የሚል ...
Read More »