.የኢሳት አማርኛ ዜና

ተጠልፈው የተወሰዱት ሁለቱ የኦጋዴን ነጻ አውጭ ባለስልጣናት በአንድ ወታደራዊ ሆስፒታል ውስጥ ሲታከሙ መታየታቸውን ግንባሩ ገለጸ

የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግንባሩ ለኢሳት በላከው መረጃ ፣ ከኢህአዴግ መንግስት ጋር ድርድር ለማድረግ በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ተገኝተው  በኢትዮጵያ የደህንነት ሃይሎች ታፍነው የተወሰዱት የኦብነግ አመራሮች፣ የደረሰባቸውን ከፍተኛ ድብደባ ተከትሎ በአንድ ወታደራዊ ሆስፒታል ውስጥ ሲታከሙ ታይተዋል። የመንግስት የደህንነት ሰራተኞች ” ባለስልጣኖቹ በገዛ ፈቃዳቸው እጃቸውን እንደሰጡ ለማሳመን ያደረጉት ከፍተኛ ጥረት ባለመሳካቱ  አሰቃቂ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው” ግንባሩ አክሎ ገልጿል። ...

Read More »

የዩጋንዳ ጦር ደቡብ ሱዳንን ለቆ እንዲወጣ አቶ ሃይለማርያም አስጠነቀቁ

የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚ/ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ በደቡብ ሱዳን የሚገኘው የዩጋንዳ ጦር በሂደት ለቆ ካልወጣ አካባቢው የጦርነት ቀጠና ሊሆን ይችላል ብለዋል። ሁሉም ሃይሎች የራሳቸው የሆነ ፍላጎት አላቸው ያሉት አቶ ሃይለማርያም፣ በደቡብ ሱዳን ሰላም ይመጣ ዘንድ የዩጋንዳ ጦር ጁባን ለቆ መውጣት አለበት ሲሉ አሳስበዋል ። አቶ ሃይለማርያም የገለጹት አቋም የደቡብ ሱዳንን መንግስት የሚያስከፋ ቢሆንም፣ በሌላ በኩል ግን ለተቀዋሚዎች ...

Read More »

በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ችግሩ እንደተባባሰ ነው

የካቲት  ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከተማው ውስጥ የሚገኙ የመንግስት ተሽከርካሪዎች ፣ የግል ባለንብረቶችና ባለታክሲዎች በመላ አገሪቱ የጠፋውን ነዳጅ ተከትሎ ነዳጅ ለማግኘት ላይ ታች እየተንከራተቱ ሲሆን፣  የነዳጅ መጥፋቱን  ተከትሎ የትራንስፖርት ታሪፊም  ጨምሯል። ዘጋቢያችን እንዳለው ዛሬ ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀስ 0.25 ሳንቲም ተጨማሪ ገንዘብ ለመክፈል ተገዷል፡ ነዳጅ ማደያዎችን ተዘዋውሮ የተመለከተው ዘጋቢያችን፣ በከተማው የሚገኙ ነዳጅ ማደያዎች ናፍጣም ሆነ ቤንዚን በማጠራቀሚያቸው  ውስጥ ...

Read More »

በአዲስ አበባ በሌሊት የሚጻፉ የተቃውሞ ጽሁፎች ቁጥር እየጨመረ ነው

የካቲት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከታህሳስ ወር 2006 ዓም ጀምሮ በመዲናዋ  ሌሊት የሚጻፉ  የተቃውሞ ጽሁፎችን ማየት የተለመደ እየሆነ መምጣቱን ነዋሪዎች ይናገራሉ። ትናንት ሌሊት በአስኮ መስመር ጀኔራል ዊንጌት ከሚገኘው አደባባይ ጀምሮ አወሊያ፣ካኦጄጄ፣ አስኮ የሚወስደውን ዋና መንገዱን በመሃል በሚከፍለው እስከ 2.5 ሜትር ቁመት ባለው ግድግዳ ላይ የሙስሊሙን የመብት ጥያቄና የትግል ቀጣይነት የሚያንፀባርቁ ጽሁፎች በተለያዩ ቀለማት ተጽፈው ዛሬ ህዝብ ሲያነባቸው ...

Read More »

የሃይማኖት ተቋማትን በሚመለከተው አዋጅ ላይ የሚመክር ስብሰባ በአዋሳ ተጠራ

ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የተዘጋጀው  የእምነት አኩልነትና ተቻችሎ የመኖር የሃይማኖት እሴትን ሊያጎለብት ይችላል የተባለ ረቂቅ አዋጅ ላይ የሚመለከታቸውን ወገኖች ሃሳብ ለማሰባሰብ  ከነገ ጥር 30 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ቀናት በአዋሳ ከተማ እንደሚካሄድ ምንጮቻችን ጠቆሙ። በዚሁ ስብሰባ ላይ በዋንኛነት የሚሳተፉት በአገሪቱ አሉ የሚባሉት 945 ያህል የእምነት ተቋማት መሆናቸውም ታውቆአል፡፡ መንግስት የሙስሊም ማህበረሰብ የመብት ጥያቄ ...

Read More »

አቶ አስራት ጣሴ ታሰሩ

ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአንድነት ፓርቲ መስራችና የድርጅቱ ዋና ጸሀፊ የነበሩት አሁን ደግሞ የፓርቲው የብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አስራት ጣሴ አኬልዳማ በሚል በመንግስት የተዘጋጀውን ዶኩመንታሪ ፊልም በአዲስ ጉዳይ መጽሄት ላይ ዘለፋ አዘል ጽሁፍ ጽፈዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸው ፣ ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ ለአንድ ሳምንት ታስረው በሚቀጥለው ቀጠሮ እንዲቀርቡ ወስኗል። በዚህም መሰረት ...

Read More »

የሃሙሲት ነዋሪዎች ገዢው ፓርቲ እየተበቀለን ነው ይላሉ

ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከባህርዳር 30 ኪሚ ርቃ በምትገኘው በደቡብ ጎንደሩዋ ሃሙሲት ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች ገዢው ፓርቲ እየተበቀለን ነው ሲሉ ይናገራሉ። ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት ኢህአዴግ ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጋር ሲያደርግ በነበረው ጦርነት ሃሙሲት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል። በዚህም በቀል ይመስላል ይላሉ ነዋሪዎች ፣የህወሃት የደህንነት ሰዎች በከተማ ውስጥ አሉ የሚባሉ ታላላቅ ሰዎችን ከመግደል ጀምሮ አፍነው ...

Read More »

የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤት በመስተዳድሩ ግቢ ውስጥ የሚቆሙ መኪኖች ታርጋቸው እንዲፈተሽ አሳሰበ

ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የከንቲባ ጽ/ቤት እና የካቢኔ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት አቶ አሰግድ ጌታቸው ይመኑ ጥር 29 ቀን 2006 ዓም ለሁሉም የመስተዳድሩ ቢሮችና ለክፍለከተሞች በጻፉት ደብዳቤ ፣ ማንኛውም በግቢው ውስጥ የሚያድር መኪና የማን እንደሆነ ለማወቅ ይቻል ዘንድ ታርጋቸው ተገልጾ ይቅረብልን ብለዋል። ደብዳቤው በግልባጭ ለግቢው ጸጥታ ዴስክ ተመርቷል። መስተዳድሩ ይህን ደብዳቤ የጻፈው ኢሳት በቅርቡ በመስተዳድሩ ግቢ ውስጥ ...

Read More »

አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ክብረ-ወሰን ሰበረች።

ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስዊድን-ስቶኮሆልም በተካሄደው የቤት ውስጥ የ 3 ሺ ሜትር ውድድር አትሊት ገንዘቤ ዲባባ በአስደናቂ ብቃት በማሸነፍ  አዲስ የዓለም ክብረወሰን አስመዘገበች። ገንዘቤ ዲባባ ርቀቱን በ8:ደቂቃ 16 ሴኮንድ  60 ማይክሮ ሴኮንድ በማጠናቀቅ  እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2007 ዓመተ ምህረት፣ ማለትም ከ 7 ዓመት በፊት  በአገሯ ልጅ በአትሌት መሰረት ደፋር  ተይዞ የነበረውን ሪከርድ ከ7 ሰከንድ በላይ አሻሽላለች። ...

Read More »

የዩክሬንን የውስጥ ቀውስ አስመልክቶ የ አሜሪካ ባለስልጣናት የአውሮፓ ህብረትን ሲዘልፉ የሚደመጡበት የስልክ ምልልስ አፈትልኮ ወጣ።

ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዩናይትድ ስቴስት ከፍተኛ  ዲፕሎማት የሆኑት ምክትል ሴክሬታሪ  ቪክቶሪያ ኑላንድ- በዩክሬን ከ አሜሪካ አምባሳደር ጋር ስለ ዩክሬን ግጭት በስልክ ያወሩት ወሬ  ተጠልፎ በድረ ገፆች መለጠፉ አሜሪካን ማሳፈሩን ዘገባዎች አመልክተዋል። ቪክቶሪያ ኑላንድ  በዙሁ የስልክ ምልልስ ላይ ስለዩክሬን ግጭት ሲያወሩ የአውሮፓ ህብረትን ሲወቅሱና  በወረደ ቃላት ሲዘልፉ ይሰማሉ። በሁኔታው የደነገጠችው አሜሪካ ፦”ቪክቶሪያ ኑላንድ ለተናገሩት ነገር ይቅርታ ጠይቀዋል” ...

Read More »