.የኢሳት አማርኛ ዜና

የአንድነት የአዋሳ ሰልፍ “በእስር ተጀምሮ በእስር ተጠናቀቀ”

ሰኔ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት በሚል አንድነት ፓርቲ በአዋሳ ሊያካሂደው የነበረው ሰልፍ ፣ የሰልፉ አስተባባሪዎችና የፓርቲው የአመራር አባላት በመታሰራቸው ምክንያት ሳይካሄድ ቀረ። ሰልፉ ከመካሄዱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ በፓርቲው ቅስቀሳ የተደናገጡት የሚመስሉት የአዋሳ ባለስልጣኖችና ፖሊስ አባላት 37 የሚሆኑ በቅስቀሳ ላይ የተሰማሩ አመራሮችንና ደጋፊዎችን ይዘው በተለያዩ እስር ቤቶች አስረዋቸዋል። በማግስቱ እስረኞችን ለመጠየቅና ስንቅ ለማቀበል ከሄዱት ...

Read More »

የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኛውን የዘነጋው የኢትዮጽያ መንግሥት የሲቪል ሰርቪስ ቀንን እያከበረነው

ሰኔ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሠራተኛው በከፍተኛ የኑሮ ውድነት በደመወዝ መኖር የማይችልበት ስቃይ ውስጥ በሚገኝበትና ሲቪል ሰርቪሱ በገዥው ፓርቲ ቁጥጥር ሥር ሙሉ በሙሉ በወደቀበት በዚህ ወቅት ፣ ኢህአዴግመራሹ  መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናቱ በተገኙበት በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ የሲቪል ሰርቪስ ቀንን በድምቀት እያከበረውይገኛል፡፡ በየዓመቱሰኔ 16 ቀንየሚከበረውየሲቪልሰርቪስቀንዘንድሮለስምንተኛጊዜየሚከበረው “በተደራጀሲቪልሰርቪስለውጥሠራዊትፈጣንናቀጣይነትያለውልማትበተግባርእናረጋግጥ” በሚልመርህመሆኑታውቋል፡፡ የሲቪልሰርቪስዘርፉከፖለቲካጋርተቀይጦሠራተኛውየኢህአዴግአባልበመሆንናባለመሆንመካከልባለበትእንዲሁምበየተቋማቱሠራተኛውአንድለአምስትእንዲደራጅበማስገደድበከፍተኛቁጥጥርውስጥባለበትሁኔታሲቪልሰርቪሱበለውጥሂደትላይነውበሚልጉሮወሸባዩመያዙእንዳሳዘናቸውያነጋገርናቸውአንዳንድየመንግሥትሠራተኞችተናግረዋል፡፡”ሙስናናየመልካምአስተዳደርችግሮችንለመቅረፍየሚያስችልየለውጥሠራዊትለመገንባትበሚልአንድለአምስትእንድትደራጅትገደዳለህ፣እምቢካልክትገለላለህ፡፡በየቀኑተሰብስበህትወያያለህ፣ይህንንምሪፖርትታደርጋለህ፡፡በዚህሁኔታአንዱከአንዱእየተፈራራናእየተጠባበቀ፣ሰዎችበችሎታናበሜሪትሳይሆንበፖለቲካአቋማቸውብቻተጠቃሚየሚሆኑበትስርዓትእንዲሰፍንሆኗል፡፡በዚህምምክንያትየመንግሥትሥራናአገልግሎትአሰጣጥእያሽቆለቆለ፣ምርታማነትእንዲቀንስበማድረግየሠራተኛውንየስራዋስትናጭምርአሳሳቢደረጃላይአድርሶታል” ሲሉያነጋገርናቸውገልጸዋል፡፡ በመንግሥትሁለተኛደረጃት/ቤትየሚያሰተምሩአንድመምህርበሰጡትአስተያየትከሲቪልሰርቪሱሠራተኞችየመምህራንቁጥርከፍተኛመሆኑንአስታውሰውበአሁኑሰዓትመምህራንእጅግበአነስተኛደመወዝየሰቆቃህይወትእየመሩመሆኑንአስታውሰዋል፡፡ “እኔበማስተምርበትትቤትዲግሪያላቸውመምህራንኑሮአቸውንለመደጎምሲሉበሰፈርአካባቢየድለላስራላይጭምርመሰማራታቸውን፣አንዳንዶቹምበተለይየደመወዝመዳረሻሰሞንበጣምስለሚቸገሩከሥራገበታቸውበተደጋጋሚስለሚቀሩበመማርማስተማሩሒደትላይአሉታዊተጽዕኖእየደረመሆኑ እውነትነው” ብለዋል፡፡ ሌላበአንድየሚኒስትርመ/ቤትበሕዝብግንኙነትሙያላይየተሰማራባለሙያእንዳስረዳውበመ/ቤቱውስጥሲካሄድየነበረውየቢፒአርእናየቢኤሲሲየለውጥፕሮግራሞችሠራተኛውሊቀበለውባለመቻሉከፍተኛወጪወጥቶበትተግባራዊሊሆንእንዳልቻለአስረድተዋል፡፡ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የዋጋ ንረት በማይፈጥር መልኩ ...

Read More »

ከምዕራብ ወለጋ የተፈናቀሉ እና አሁንም በአካባቢው ያሉ ዜጎች ፍትህ ማጣታቸውን ተናገሩ

ሰኔ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ከምእራብ ወለጋ ዞን ጊምቢና ከቄለም ወለጋ ዞን የተፈናቀሉ አማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ ያቀረበውን ዘገባ ተከትሎ ኢሳት ከጊምቢ በታች በሚገኘው አሹ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑትን እንዲሁም ተፈናቅለው ባህርዳር ከሚገኙት መካከል አንዳንዶቹን አነጋግሮ እንደተረዳው ፍትህ አጥተው የሚሰቃዩ ወገኖች በብዙ መቶዎች ይቆጠራል። አሹ ቀበሌ ውስጥ የሚኖረው በንግድ ስራ የሚተዳደረው ወጣት እንደተናገረው ወንድሙ አካባቢውን ለቆ ...

Read More »

አንድነት ፓርቲ በአዋሳ ለሚያደርገው የተቃውሞ ሰልፍ ችግር እንደገጠመው ታወቀ

ሰኔ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመጪው እሁድ በአዋሳ የሚካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ በቅስቀሳ ላይ የሚገኘው አንድነት፣ ሶሰትአባሎቹ እንደታሰሩበት አስታውቛል። አዲስ አበባ መስተዳድር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ያሬድ አማረ በቅስቀሳ ላይ የነበሩ 3 ሰዎች መያዛቸውን ገልጸዋል። መስተዳድሩ የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ለመስጠት በሂደት ላይ በመሆኑ መቀስቀስ አትችሉም መባላቸውን የገለጹት አቶ ያሬድ፣ የእውቅና ጥያቄ ካስገቡ አንድ ወር ሞላቸው በመሆኑ በመስተዳድሩ የቀረበውን ...

Read More »

አዲሱ የጉምሩክ ረቂቅ አዋጅ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በፍርቤቶች ሊወሰን የሚገባ ጉዳዮችን እንዲወስን የተለ የመብት መስጠቱ አነጋጋሪሆነ፡፡

ሰኔ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ረቂቅ አዋጁ ሰሞኑን ለፓርላማው የቀረበ ሲሆን በዚሁ አዋጅ በዋና ዳይሬክተሩ ውሳኔ ብቻ ክስ የማይመሰረትባቸው ድንጋጌዎች ማካተቱ በፓርላማ አባላቱ ዘንድ ጥያቄ አስነስቷል፡፡ ረቂቅአዋጁ “ለሕዝብጥቅምሲባል በዋና ዳይሬክተሩ ውሳኔ ክስ የማይመሰረትባቸው አዲስ ሁኔታዎች በሚል ከዘረዘራቸው ውስጥ ወንጀል ፈጽሞአል የተባለ ሰው በዕድሜ መጃጀት ወይም በበሽታ ምክንያት ጉዳዩን በፍርድ ቤት መከታተል የማይችል ሲሆን ፣ጉዳዩ በክስሒደትውስጥቢያልፍብሔራዊደህንነትንወይምዓለምአቀፍግንኙነትንይጎዳልተብሎሲታመን፣የክሱመመስረትተመጣጣኝናሚዛናዊያልሆነየጎንዮሽጉዳትየሚያስከትልመሆኑከታመነበት፣ወንጀሉስልጣንላለውፍርድቤትሳይቀርብበመቆየቱአስፈላጊነትያጣከሆነ ክስ እንዳይመሰረትዋና ዳይሬክተሩ ...

Read More »

ሌ/ጄኔራል ዮሃንስ የጁባ የሰላም አስከባ ሃይል አዛዥ ሆኑ

ሰኔ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ሃይል በአብየ አዛዥ የሆኑት ሌ/ጄ/ዮሃንስ ገብረመስቀል በደቡብ ሱዳን የሚመሰረተውን የሽግግር መንግስት ሂደት እንዲመሩ ተሹመዋል። ከ100 ያላነሱ ወታደሮች ደቡብ ሱዳን የገቡ ሲሆን፣ አዛዡም ጁባ መግባታቸው ታውቓል። ጄ/ል ዮሃንስ በወር ከ20 ሺ የአሜሪካ ዶላር በላይ  እንደሚከፈላቸው የውስጥ ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። በአዲስ አበባ በተፈረመው የሰላም ስምምነት መሰረት በደቡብ ሱዳን አዲስ የሽግግር ...

Read More »

በኢትዮጵያ 34 ድርጅቶች ጤፍ ወደ ውጭ በመላክ ላይ ናቸው

ሰኔ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመንግስት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የመንግስቱን የእርሻ ሰብል ድርጅት ጨምሮ 34 የንግድ ድርጅቶች ጤፍ ወደ ውጭ አገር በመላክ ላይ ናቸው። መንግስት በአገሪቱ የጤፍ ምርት እጥረት ማጋጠሙን ተከትሎ ጤፍ ወደ ውጭ እንዳይወጣ አግዶ የነበረ ሲሆን እገዳውን ከ ግንቦት ወር 2005 ጀምሮ  አንስቷል። አንድ ኩንታል ጤፍ በአዲስ አበባ ከ1800 እስከ 2000 ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል።

Read More »

በእነማይ ወረዳ የመኢአድ አባላት እየተዋከቡ ነው።

ሰኔ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምስራቅጎጃም ዞን  በነማይወረዳደንጎሊማቀበሌ የሚኖሩት አቶሞሳአዳነቅዳሜሰኔ 7 ቀን በኢህአዴግ ታጣቂዎች ከተገደሉ በሁዋላ ሌሎችም አባሎች እየተዋከቡ መሆኑን የወረዳው የመኢአድ ተወካይ መቶ አለቃ ደመላሽ ጌትነት ተናግረዋል። ግለሰቡ ገበያ ውሎ ሲመለስ አዲሱ ጫኔ እና ብርሃኑ ታምሩ የተባሉ ካድሬዎች መንገድ ላይ አስቁመው በዱላ ደብድበው እንደገደሉት የሟቹ ወገን የሆኑትና በህይወትና በሞት መካከል ባለ ጊዜ ደርሰው ቃሉን የተቀበሉት አቶ ይልቃል የሻነው ...

Read More »

ለመለስ ፋውንዴሽን ማሰሪያ እየተባለ በግዴታ የሚዋጣው ገንዘብ ፋውንዴሽኑን ለመስራት ከሚፈልገው በእጅጉ እንደሚልቅ ታወቀ

ሰኔ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን በሚል በአገሪቱ ያሉ ወረዳዎች እያንዳንዳቸው በአማካኝ ከ17 እስከ 25 ሚሊዮን ብር ከህዝብ እንዲሰበስቡ ቢታዘዙም የሚዋጣው ገንዘብ ፋውንዴሽኑን ለመስራት ከሚፈለገው 300 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች ትርፉ ገንዘብ የት እንደሚገባ እንደማይታወቅ ጠቁመዋል። በአማራ ክልል  106 ወረዳዎች ያሉ ሲሆን ለፋውንዴሽኑ ማሰሪያ 2 ቢሊዮን 600 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ገንዘብ ይሰበሰባል። በኦሮምያ ደግሞ ከ205 ...

Read More »

የዋስትና መብት የተነፈጉ  ነጋዴዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ

ሰኔ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃረር በቅርቡ ከተነሳው ቃጠሎ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ ከሚገኙት ከ20 በላይ ነጋዴዎችና ሰራተኞች መካከል ፍርድ ቤት የቀረቡት 3ቱ ተከሳሾች እንደገና ሌላ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል። የ25  አመቱ  ቢኒያም ጌታቸው፣ የ28 አመቱ ሲሳይ አሊ አህመድ እና የ16 አመቱ  ዙቤር  አህመድ  በ1996 ዓም የወጣውን የወንጀል ህግ በመተላለፍ ” በፌደራል ህገመንግስት የተቋቋመውን የሃረሪ ህዝብ ክልል መንግስት ፣ በዚህ ክልል ...

Read More »