የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኛውን የዘነጋው የኢትዮጽያ መንግሥት የሲቪል ሰርቪስ ቀንን እያከበረነው

ሰኔ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሠራተኛው በከፍተኛ የኑሮ ውድነት በደመወዝ መኖር የማይችልበት ስቃይ ውስጥ በሚገኝበትና ሲቪል ሰርቪሱ በገዥው ፓርቲ ቁጥጥር ሥር ሙሉ በሙሉ በወደቀበት በዚህ ወቅት ፣ ኢህአዴግመራሹ  መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናቱ በተገኙበት በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ የሲቪል ሰርቪስ ቀንን በድምቀት እያከበረውይገኛል፡፡

በየዓመቱሰኔ 16 ቀንየሚከበረውየሲቪልሰርቪስቀንዘንድሮለስምንተኛጊዜየሚከበረው “በተደራጀሲቪልሰርቪስለውጥሠራዊትፈጣንናቀጣይነትያለውልማትበተግባርእናረጋግጥ” በሚልመርህመሆኑታውቋል፡፡

የሲቪልሰርቪስዘርፉከፖለቲካጋርተቀይጦሠራተኛውየኢህአዴግአባልበመሆንናባለመሆንመካከልባለበትእንዲሁምበየተቋማቱሠራተኛውአንድለአምስትእንዲደራጅበማስገደድበከፍተኛቁጥጥርውስጥባለበትሁኔታሲቪልሰርቪሱበለውጥሂደትላይነውበሚልጉሮወሸባዩመያዙእንዳሳዘናቸውያነጋገርናቸውአንዳንድየመንግሥትሠራተኞችተናግረዋል፡፡”ሙስናናየመልካምአስተዳደርችግሮችንለመቅረፍየሚያስችልየለውጥሠራዊትለመገንባትበሚልአንድለአምስትእንድትደራጅትገደዳለህ፣እምቢካልክትገለላለህ፡፡በየቀኑተሰብስበህትወያያለህ፣ይህንንምሪፖርትታደርጋለህ፡፡በዚህሁኔታአንዱከአንዱእየተፈራራናእየተጠባበቀ፣ሰዎችበችሎታናበሜሪትሳይሆንበፖለቲካአቋማቸውብቻተጠቃሚየሚሆኑበትስርዓትእንዲሰፍንሆኗል፡፡በዚህምምክንያትየመንግሥትሥራናአገልግሎትአሰጣጥእያሽቆለቆለ፣ምርታማነትእንዲቀንስበማድረግየሠራተኛውንየስራዋስትናጭምርአሳሳቢደረጃላይአድርሶታል” ሲሉያነጋገርናቸውገልጸዋል፡፡

በመንግሥትሁለተኛደረጃት/ቤትየሚያሰተምሩአንድመምህርበሰጡትአስተያየትከሲቪልሰርቪሱሠራተኞችየመምህራንቁጥርከፍተኛመሆኑንአስታውሰውበአሁኑሰዓትመምህራንእጅግበአነስተኛደመወዝየሰቆቃህይወትእየመሩመሆኑንአስታውሰዋል፡፡ “እኔበማስተምርበትትቤትዲግሪያላቸውመምህራንኑሮአቸውንለመደጎምሲሉበሰፈርአካባቢየድለላስራላይጭምርመሰማራታቸውን፣አንዳንዶቹምበተለይየደመወዝመዳረሻሰሞንበጣምስለሚቸገሩከሥራገበታቸውበተደጋጋሚስለሚቀሩበመማርማስተማሩሒደትላይአሉታዊተጽዕኖእየደረመሆኑ እውነትነው” ብለዋል፡፡

ሌላበአንድየሚኒስትርመ/ቤትበሕዝብግንኙነትሙያላይየተሰማራባለሙያእንዳስረዳውበመ/ቤቱውስጥሲካሄድየነበረውየቢፒአርእናየቢኤሲሲየለውጥፕሮግራሞችሠራተኛውሊቀበለውባለመቻሉከፍተኛወጪወጥቶበትተግባራዊሊሆንእንዳልቻለአስረድተዋል፡፡

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የዋጋ ንረት በማይፈጥር መልኩ የደሞዝ ጭማሪ ለማድረግ እንደታሰበ መናገራቸውን ዘግይቶ የደረሰን ዜና ያመለክታል። ስለደሞዝ ጭማሪው ዝርዝር የሰጡት ማብራሪያ የለም።