ሐምሌ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአገር ውስጥ እና በውጭ ከፍተኛ ጫና የተፈጠረበት የኢህአዴግ መንግስት የአቶ አንዳርጋቸውን ምስል በቴሌቪዥን ካቀረበ በሁዋላ የተለያዩ አስተያየቶች በማህበራዊ የመገናኛ መንገዶችና በስልክ እየተሰጡ ነው።አብዛኛው አስተያየት ሰጪ በቴሌቪዥን የቀረበው ምስልና ድምጽ መቆራረጡን ፣ ኢቲቪን የሚያክል ድርጅት ጥራት ያለው ቀረጻ ለማካሄድ አለመቻሉ ገዢው ፓርቲ ለፕሮፓጋንዳ የሚሆን ነገር ለማግኘት አለመቻሉን ገልጸዋል። ሚኒሊክ ሳልሳዊ የተባለው ጸሃፊ ” የግንቦት ሰባት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የአቶ አንዳርጋቸውን እስር ተከትሎ ከአገር ቤት በስልክ የሚሰጠው አስተያየት እንደቀጠለ ነው
ሐምሌ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከአገር ቤት በተከታታይ የሚደወሉ ስልኮችን ለማስተናገድ ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት እየገለጸ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ደዋዮች አቶ ለአቶ አንዳርጋቸው ያላቸውን ከበሬታ የሚገልጹና ኢህአዴግን በሃይል ለማንበርከክ የሚታገሉትን ቡድኖች ለመቀላቀል እንዴት እንደሚቻል የሚጠይቁ ናቸው። በሌላ ዜና ደግሞ የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የተፈጸመውን የአፈና ተግባር አውግዟል። ትህዴን ” የወያኔ አምባገነን ስርአት ህዝቡን እየጨፈጨፈና ለነፃነት የቆሙትን ...
Read More »አንድነት ፓርቲ የታሰሩት የአመራር አካሎች በአስቸኳይ እንዲለቀቅ ጠየቀ
ሐምሌ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች የአንድነት ፓርቲን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆነውን ወጣት ሃብታሙ አያሌውን ፣ የፓርቲውን የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሃላፊ አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነውን የሽዋስ አሰፋን እንዲሁም በማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃን ከመቀሌ በመጻፍ የሚታወቀውና አረና ፓርቲ አባል የሆነው መምህር አአብራሃ ደስታን ይዞ አስሯል። እሰረኞቸ ማእከላዊ በሚባለው ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። ...
Read More »አቶ አንዳርጋቸው ለኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች ተላልፈው መሰጠታቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያውያን የሚያሰሙት ቁጣ እንደቀጠለ ነው
ሰኔ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የየመን የጸጥታ ሃይሎች የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አሳልፈው በሰብአዊ መብት ጥሰትና ህዝብን በማሰቃየት በአለም የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ዘወትር ለሚወገዘው ለኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች አሳልፈው መስጠታቸው ያበሳጫቸው በአገር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የነጻነት ትግሉን የምንቀላቀልበትን” መንገዱን ምሩን” በማለት ጥያቄ ሲያቀርቡ፣ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደግሞ የተቃውሞ ሰልፎችን እያዘጋጁ ነው። ለኢሳት ስልኮችን እየደወሉ ቁጣቸውን የሚገልጹት ኢትዮጵያውያኑ ...
Read More »አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈው መሰጠታቸውን ሂውማን ራይትስ ወች ገለጸ
ሰኔ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታዋቂው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሂውማን ራይትስ ወች ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ፣ አቶ አንዳርጋቸው ከማንም ጋር እንዳይገናኙ ተደርጎ ለኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች ተላልፎ መሰጠቱን ከታማኝ ምንጭ ማግኘቱን ገልጿል። የየመን ባለስልጣናት ሰነዓ ከሚገኘው ኤል ራህባ አየር ማረፍያ ላይ እኤአ ጁን 23 ወይም 24 ከእንግሊዝ ኢምባሲ ጋር እንዳይገናኝ አድርገው አቶ አንዳርጋቸውን ወዲያውኑ ወደ ኢትዮጵያ ልከውታል ሲል ሂውማር ራይተስ ወች ...
Read More »የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት ተላልፈው መሰጠታቸውን ተከትሎ ግንቦት 7 የክተት አዋጅ አወጀ
ሰኔ ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ ፣ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓም ባወጣው መግለጫ ፣ “የየመን መንግሥት በህገወጥ መንገድ ያገተብንን የንቅናቀዓችንን አመራር በአስቸኳይ እንዲፈታ በተለያዩ መንገዶች ላለፈው አንድ ሣምንት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም ” ብሎአል። “የአገሩን የረዥም ጊዜ ጥቅም ማየት የተሳነው የየመን መንግሥት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ይልቅ አምባገኑን ወያኔ መርጦ መሪያችንን ለእርድ አሳልፎ ሰጥቶብናል ፣በዚህም ሳቢያ የየመን መንግሥት ይቅርታ የማያሰጥ ...
Read More »የአቶ አንዳርጋቸውን መያዝና ተላልፎ መሰጠት ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ቁጣቸውን እየገለጹ ነው
ሰኔ ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንዲት እናት ” እኔ ሁለት ልጆች አሉኝ፣ ልጆቼን ዛሬ ብሰጥ ደስ ይለኛል” ሲሉ በአቶ አንዳርጋቸው መያዝ የተሰማቸውን ስሜት በለቅሶ ገልጸዋል። አንድ ወጣት ደግሞ እርሱና ጓደኞቹ በአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ወደ ትግል ፈጥነው እንዲገቡ እንደሚያደርጋቸው ገልጸዋል። “ቀድሞ ዘርዘሩን ዘርቷል” በሚል ቅኔ የተቀኙት አንድ ኢትዮጵያ ደግሞ በአንዳርጋቸው መስዋትነት፣ ነጻነታችንን እውን እናደርጋለን ብለዋል ሌላ ወጣት ደግሞ ” ...
Read More »ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ዛሬም የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ዋሉ።
ሰኔ ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአንዋር መስጊድ እጅግ በርካታ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በተካሄደው ተቃውሞ ፣ መንግስት “መጅሊሱን ለህዘበ ሙስሊሙ እንዲያስረክብ እንዲሁም የታሰሩትን መሪዎች እንዲፈታ” ጠይቀዋል። “ትግሉ የጽኑዎች ነው፣ ፍትህ ይስፈን፣ የእምነት ቤቶቻችን ይከበሩ፣ የታሰሩት ይፈቱ፣ የትግላችንን መነሻ እናሳካው የማነፍርበት የትግል መዳረሻችን ነው፣ አፈና ግፍና ማስገደድ ይቁም” የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል። ሙስሊሙ ኢትዮጵያውያን በረመዳን ጾም መግቢያ ጀምሮ ጠንካራ ተቃውሞዎችን እየሰማ ...
Read More »በሸኮና መዠንገር በተነሳው ግጭት አንድ የልዩ ሃይል አዣዝ ተገድሏል።
ሰኔ ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በርካታ የሌሎች አካባቢ ሰዎች ተፈናቅለው፣ በቴፒ ከተማ ኤግዢቢሽን አዳራሽ ሰፍረዋል። ሰፋሪዎች በምግብ እና በውሃ ችግር ለአደጋ መጋለጣቸው ታውቋል። እስካሁን ከ700 ያላነሱ ሰዎች ተፈናቅለዋል። ግጭቱ ካለፉት 3 ቀናት ጀምሮ ከቁጥጥር ውጭ መውጣቱ ተነግሯል። ልዩ ፖሊስና የወረዳው ፖሊስ፣ ዘመናዊ መሳሪያ ከታጠቁት የሸኮና መዠንገር ተዋጊዎች ጋር እየተዋጋ መሆኑ ታውቋል። ሸኮና መዠንገር መሬታቸው ጻኑ ቀበሌ ለደቡብ ክልል ...
Read More »የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል አንዳርጋቸው በአስቸኳይ እንዲለቀቅ አስጠነቀቀ
ሰኔ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል ” አንዳርጋቸው የማይጨበጥ ጽኑ መንፈስ እንጂ አንድ ግለሰብ አይደለም” በሚል ርእስ ባወጣው ጠንካራ መግለጫ ” የየመን መንግሥት የፈጸመው ድርጊት እጅግ ስህተት መሆኑን ዘግይቶም ቢሆን ተረድቶ የነፃነት ታጋዩን እንዲለቅ” አስጠንቅቋል። ይህ ባይሆን ግን ይላል የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል ” አንዳርጋቸው ወያኔ እጅ ውስጥ ከገባ የትውልዱ የበቀል ሰይፍ ከዛሬ ጀምሮ ከሰገባው መውጣቱን እንዲያውቁት ...
Read More »