በሸኮና መዠንገር በተነሳው ግጭት አንድ የልዩ ሃይል አዣዝ ተገድሏል።

ሰኔ ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በርካታ የሌሎች አካባቢ ሰዎች ተፈናቅለው፣ በቴፒ ከተማ ኤግዢቢሽን አዳራሽ ሰፍረዋል። ሰፋሪዎች በምግብ እና በውሃ ችግር ለአደጋ መጋለጣቸው ታውቋል። እስካሁን ከ700 ያላነሱ ሰዎች ተፈናቅለዋል። ግጭቱ ካለፉት 3 ቀናት ጀምሮ ከቁጥጥር ውጭ መውጣቱ ተነግሯል። ልዩ ፖሊስና የወረዳው ፖሊስ፣ ዘመናዊ መሳሪያ ከታጠቁት የሸኮና መዠንገር ተዋጊዎች ጋር እየተዋጋ መሆኑ ታውቋል።

ሸኮና መዠንገር መሬታቸው ጻኑ ቀበሌ ለደቡብ ክልል መሰጠቱን ይቃወማሉ ። ባለስልጣኖች ግጭቱ ከአቅማችን በላይ ነውና ለቃችሁ ውጡ እያሉ በአካባቢው ላሉ ሰዎች እየተናገሩ ነው።