የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል አንዳርጋቸው በአስቸኳይ እንዲለቀቅ አስጠነቀቀ

ሰኔ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል ” አንዳርጋቸው የማይጨበጥ ጽኑ መንፈስ እንጂ አንድ ግለሰብ አይደለም” በሚል ርእስ ባወጣው ጠንካራ መግለጫ ” የየመን መንግሥት የፈጸመው ድርጊት እጅግ  ስህተት  መሆኑን  ዘግይቶም ቢሆን  ተረድቶ የነፃነት ታጋዩን እንዲለቅ” አስጠንቅቋል።  ይህ ባይሆን ግን ይላል የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል ” አንዳርጋቸው ወያኔ እጅ ውስጥ ከገባ  የትውልዱ  የበቀል ሰይፍ ከዛሬ ጀምሮ ከሰገባው መውጣቱን እንዲያውቁት ” ያስፈልጋል።

“ምንም አይነት ምድራዊም ይሁን ሰማያዊ መነሻምክንያት ለአቶአንዳርጋቸው በየመን መንግሥት መታገት እናመታሰር ምክንያት ሊሆን እንደማይችል ” በመግለጽ ” የየመን መንግሥት የነፃነት ታጋያችንን ባስቸኳይእንዲለቅ ላለፉት ተከታታይ ቀናት የተደረገው ሁሉን አቀፍ ጥረት ውጤት አለማስገኘቱን ፣ ከዚህም በመነሳት አቶ አንዳርጋቸው ለዘረኛውእና ከፋፋዩየወያኔ ቡድን ሊሰጥይችላል የሚለው ስጋታችን ቀን በገፋእና ምላሽ በራቀ  ቁጥር እየጨመረ ” ሄዷል ብሏል በመግለጫው።

በግንቦት 7ሕዝባዊ ኃይል በኩል የነፃነት ታጋዩ ለወያኔ ተላልፎመሰጠቱን መቶ በመቶእስከምናረጋግጥበት ቅጽበትታጋዩን የማስለቀቅ ጥረቱ መቀጠል እንዳለበት በጽኑ እናምናለንየሚለው ህዝባዊ ሃይሉ፣ “አንዳርጋቸውን ማሰር ይቻላል፤ምናልባትምበዚህ ቅጽበት ተችሏል፤አንዳርጋቸውንማሰቃየትይቻላል፤ምናልባትም በዚህ ቅጽበት ተችሏል፤አንዳርጋቸውን መግደል ይቻላል።

ሞትን ፈርቶ ወደ ትግል አልገባምናአንዳርጋቸውን በማሰር የአንዳርጋቸውን እንደ እቶን የሚያቃጥል የፍትህ፣የነፃነት፣ የዴሞክራሲናየእኩልነት መንፈስ ግን ለሴኮንዶች እንኳን ማሰር አይቻልም፣   አንዳርጋቸውን በማሰቃየትያን ዘመን ተሻጋሪ የሆነ የትውልዱን መንፈስ የሚገዛ የሁላችንም የምትሆን የጋራ ኢትዮጵያን የመፍጠርንጹህ ራዕዩን ግን ፈጽሞማቁሰል አይቻልም!!!

አንዳርጋቸውን በመግደል ዕንቁ ዓላማውን መግደል ከቶ አይቻልም፤ የታሪክ መዛግብት ገጾች ለዚህ ሃቅ በሚመሰክሩ እውነታዎች የተሞላ ነውና” በማለት የሚያትተው መግለጫ፣  አንዳርጋቸውን በመግደል “ከአባቶቹ የማይበልጥ ትውልድ እንዳልተፈጠረ  ይቆጠራል፣ልጅ አባቱን ሩጦመቅደም አለበት፣ስለዚህ እናንተ ወጣቶች እኛን ሩጡእናብለጡ ቅደሙን፣ቀናዎች ሁኑ፣ርስ በርስ ተዋደዱ፣ያለፉት ትውልዶች የሰሩትን ስህተት ላለመድገም ታሪክን ከስሩ ተረዱ፣ ያለማወቅ ጠንቅ ከሚያመጣው ጥፋት ለመዳን ሁሌም ለእውቀት ጉጉዎች ሁኑ።

ለማወቅ ጣሩ፣የማይቀረው ሞታችሁ ለፍትህ፣ለዴሞክራሲ እና  ለነፃ ኢትዮጵያ ይሁን” እያለ ላለፉት በርካታ አመታትያስተማራቸውእናየኮተኮታቸው የነፃነት ታጋይ አርበኛ  ወጣቶችን እና እሳት መንፈሳቸውን መግደል አይቻልም:” ሲል ያክላል።

“አንዳርጋቸውንበአንድ ካቴናበማሰር፤ በአንድክፍል ውስጥ በመዝጋት ወይም በአንድ ጥይትበመግደል “መገላገል” የሚቻል አንድ ግለሰብ አይደለም::አንዳርጋቸው ለሽህ ካቴናዎች የማይታጠፉ እጆች፤ ለሽህ ማጎሪያዎች የገዘፈ ገላ፤ ለሽህ ጥይቶች የሰፋ እና ሽህ ጥይቶችን የሚተፋ ግንባር እና ደረት ያለው ብርቱ ታጋይ ነው። አንዳርጋቸው አንድ ግለሰብ አይደለም፤ የማይጨበጥ ጽኑ መንፈስ እንጅ!!!” ሲል ለመሪያቸው ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

አንዳርጋቸውይላል መግለጫው በማስከተል ” ለአርባ አመታት በሚጠጋ የፖለቲካ ሕይወቱ ሁሉ በረሃ የሚወረወረው አፈር ላይ የሚንከባለለው፤ በእሱ እድሜ  በማይታሰብ ሁኔታ እንኳን የበረሃ ሃሩር፣ጥም እና ረሃብ የሚያንገላታው ነገ ኢትዮጵያን በፕሬዝዳንትነት ወይ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስቴርነት ለመምራት ካለው ሰዋዊ ፍላጎት አይደለም::የሱ ምኞት የሁላችንም የሆነች ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ማየት ነው!!! አንዳርጋቸው ሁሌ ለሚያልማት ንጽህት ኢትዮጵያ መሥራት የነበረበትን ፈታኝ እና ታሪካዊ ሥራዎች  ቀድሞ  አከናውኗቸዋል::ላለፉት 6 እና 7 ዓመታት ከጥልቅ የፖለቲካ  ተሞክሮው እየቀዳ ለወጣት  ኢትዮጵያውያን በየበረሃው እየዞረ አስተምሯል::

እያማጠ አደራ ብሏል::እያለቀሰ ምኞቱን፣ፍላጎቱን እና ራዕዩን ከውስጡ አውጥቶ መዳፉ ላይ በማስቀመጥ ልቡን ለታዳጊዎች አሳይቷል::ንጹህ ዓላማው ሽህ ባለ ራዕዮችን  ፈጥሯል የተግባር ሰዎችን አምርቷል::የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አንዳርጋቸው እንደመጥምቁ ዮሃነስ በበረሃ  እየዞረ ሲያስተምር እና  ሲሰብክ ከፈጠረው ንጹህ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ላይ የበቀለ ኃይል ነው:: ”

መግለጫው በመጨረሻም ”  ዛሬ አንዳርጋቸው በአካል አብሮን ላይኖር ይችላል::ነፍሳችን ውስጥ ያሰረፀው ዘላለማዊ መንፈስ ግን እስከመጨረሻ ህቅታችን ድረስ አብሮን ይዘልቃል::አንዳርጋቸውን በማስቆም ትግሉን አቆማለሁ ብሎ የሚያስብ ካለ ዓለምን እና ሁኔታዎችን መገንዘብ የማይችል ከራሱ የተጣላ የወያኔ አይነት ቂል ብቻ ነው::አንዳርጋቸውን በማስቆም ትግሉን ማስቆም አይቻልም::መንፈስን ማስቆም ከቶ ማን ይቻለዋል??አንዳርጋቸው እኮ መንፈስነው::

ሁሉም ቦታ፣ሁሉም ጫፍ፣ሁሉም ልብ ውስጥ የሚገኝ እና የሚንሳፈፍ መንፈስ::” ካለ በሁዋላ ” የየመን መንግሥት የፈጸመው ድርጊት እጅግ  ስህተት  መሆኑን  ዘግይቶም ቢሆን  ተረድቶ የነፃነት ታጋያችንን ባስቸኳይ ይለቀው ዘንድ አሁንም ደጋግመን እንጠይቃለን::ይህ ሳይሆን ቀርቶ  ታጋያችን ወያኔ  እጅ ውስጥ ከገባ ግን የትውልዱ  የበቀል ሰይፍ ከዛሬ ጀምሮ ከሰገባው መውጣቱን እንዲያውቁት እንፈልጋለን::ወያኔም ይህ የቂል ድርጊት የነፃነት ታጋዮችን የበለጠ ቁጭትእናየበቀልእርምጃዎች ውስጥ የሚከት መሆኑን አብሮ ሊገነዘበው ይገባል::ለዚህ ቃላችን ታሪክ ምስክር  ይሁንብን::” በማለት መግለጫውን አጠቃሏል።

የየመን መንግስት በአተፐ አንዳርጋቸው ዙሪያ እስካሁን የሰጠመው መግለጫ የለም። ኢሳት የተለያዩ የአገሪቱን ባለስልጣናት ለማነጋገር ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል።