.የኢሳት አማርኛ ዜና

ዞን ዘጠኝ በሚል ስም የሚጠሩት ወጣት ጸሃፊዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ

ጥር ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው ጥር 20 ቀን 2007 ዓ.ም ለ16ኛ ጊዜ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት ጸሃፊዎች፣ ፍርድ ቤቱ ቀደም ብሎ ተሻሻለ የተባለውን ክስ አይቶ ብይን ሰጥቷል፡፡ የፌደራል አቃቤ ህግ አሻሽየዋለሁ ያለውን ክስ ከአንዱ ነጥብ በስተቀር ሦስቱን መቀበሉን ፍርድ ቤቱ ገልጿል። በክሱ ላይ ‹ቡድን› በሚል የተጠቀሰው ነጥብ ተከሳሾቹ በህቡ ...

Read More »

አንድነት በመጪው እሁድ የጠራው ሰልፍ ውጥረት ፈጥራል

ጥር ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአንድነት ፓርቲ ለእሁድ ጥር 24 በደሴ ለሚያካሄደው ሰልፍ ከከተማው አስተዳዳር እውቅና ያገኘ ሲሆን ፤ የአዲስ አበባው ግን እያወዛገበ ይገኛል። ከፓርቲው ጽህፈት ቤት የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው በደሴ ሰልፉ  አራዳ አከባቢ ከሚገኘው የአንድነት ቢሮ ተነስቶ  ሆጤ አደባባይ ይጠናቀቃል። ከ2: 00 ሰ ዓት  እስከ 7:00 ሰዓት በሚቆየው በዚህ ሰልፍ ፤የደሴና የአከባቢዋ ህዝብ በነቂስ በመውጣት ምርጫ ...

Read More »

ሼክ ሙሃመድ አላሙዲን ከባለስልጣናት ጋር ባላቸው ቀረቤታ የህዝብ ሃብት የሆኑ ኩባንያዎችን ወደ ግል እንዲያዞሩ ረድቷቸዋል ተባለ

ጥር ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕራይቬታይዜሽንና የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ የመንግስት ልማት ድርጅቶችን መሸጥ ከጀመረበት ከ1997 ዓ.ም እስከ 2006 ዓ.ም ድረስ ባሉት ጊዜያት ከሸጣቸው 370 ድርጅቶች መካከል ሼህ አልአሙዲ ወደ 30 የሚጠጉትንና እጅግ አትራፊ የሆኑ ድርጅቶችን በርካሽ ዋጋ መሰብሰብ መቻላቸው ስርአቱ ለተዘፈቀበት ሙስና ማሳያ መሆኑን ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ገልጸዋል። ሼሁ የለገደንቢን ወርቅ ማዕድን በአሁኑ ወቅት ሚድሮክ ...

Read More »

አንድነት ፓርቲ በድጋሜ የተቃውሞ ሰልፍ ጠራ

ጥር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ህወሃት /ኢህአዴግ ጥር 17/2007 ዓም በአንድነት አመራሮችና አባላት ላይ ያደረሰውን አሰቃቂ ድብደባ ለማውገዝ እንዲሁም ፓርቲውን ለመቀማት የሚደረገውን ጥረት ለማውገዝ ለጥር 24 በአዲስ አበባና በሌሎች የተለያዩ የክልል ከተሞች ላይ ሰልፍ ለማድረግ ማቀዱን ገልጸሏል። አምባገነኑ የህወሀት/ኢህአዴግ መንግስት የዘንድሮውን ሀገራዊ ምርጫ ሂደቱንም ጭምር በማበላሸት ጠንክራ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከምርጫው ውጪ እንዲሆኑ ለማድረግ ላይ ...

Read More »

በእስራት ላይ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በድጋሜ ተቀጠሩ  

ጥር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ማዕከላዊ ፌደራል ወንጀል ምርመራ የሚገኙት የሦስት ተቃዋሚ ፓርቲ  አመራሮች ለአራተኛ ጊዜ 28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው፡፡ የሰማያዊ፣  የአንድነት እና መኢአድ የዞን አመራሮች ዛሬ ጥር 19 ቀን 2007 ዓ.ም በፌደራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ለአራተኛ ጊዜ   የቀረቡ ቢሆንም፤  ፖሊስ ፦‹‹ምስክሮችን ማደራጀት ይቀረኛል›› በማለት ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው በጠየቀው መሰረት ...

Read More »

ሃይቅ ከተማ የሚገኘው የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት ሙሉ በሙሉ በእሳት ወደመ

ጥር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ወሎ ዞን በተሁለደሬ ወረዳ ሀይቅ ከተማ የሚገኘው  የሙያና ቴክኒክ ትምህርት ቤት ሰኞ ጥር 18፣ 2007 ዓም ሙሉ በሙሉ በቃጠሎ መውደሙን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል። ቃጠሎው የተነሳው ከምሽት 1:30 አካባቢ ሲሆን ለ2 ሰአታት ያክል መቆየቱንና  የተማሪዎችን መረጃ ላፕቶፖ ኮምፒዩተሮች፣ ዴስክ ቶፖች እና የተለያዩ የሰርቬ ጂፒኤሶችን ማውደሙ ተውቋል።  ከኮምቦልቻ ከተማ የተነሳው የእሳት አደጋ ...

Read More »

ጎጃምን ከጎንደር የሚያገናኘው የአባይ ድልድይ ትክ የሚሰራበት  የቆይታ ጊዜ በመርዘሙ አደጋ ያደርሳል በሚል ስጋት ላይ መሆናቸውን የባህርዳር ከተማ  ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

ጥር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በባህርዳር ከ1949 ዓ.ም ጀምሮ ነዋሪ የሆኑት አስተያየት ሰጪ ሲናገሩ ድልድዩ ሲሰራ አለሁ የመሰረት ዲንጋዩ ሲቀመጥ ነበርኩ ካሉ በኋላ ከ25 እስከ 30 ዓመት እንደሚያገለግል በይፋ ተነግሮ እንደተሰራ  ከዚህ ዓመት በላይ ከቆየ አደጋ ለያደርስ እንደሚችል በወቅቱ በነበሩ የግንባታ ባለሙያዎች እንደተነገረ በማስታወስ ገልጸው ምንም አይነት የተሰራ አዲስ ነገር ሳይኖር ከ50 ዓመታት በላይ መቆየቱ ስጋት እንዳሳደረባቸው ...

Read More »

ወደ ኤርትራ በማቅናት ላለፉት ሶስት ሳምንታት በኤርትራ ድንበር የሚገኙ የኢትዮጰያ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴ ሲቃኙ የቆዩት የኢሳት ጋዜጠኞች ትናንት እሁድ ተመለሱ።

ጥር ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን እና ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም  የኢህዴግን መንግስት በትጥቅ ትግል ለመፋለም ብረት ያነሱ  የኢትዮጰያ ተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ በዓይን ለማየት እንዲሁም ስለ ኢትዮጰያና ኤርትራ የወደፊት ግንኙነት የኤርትራ ባለስልጣናትን ቃለ ምልልስ ለማድረግ ወደ ኤርትራ ያቀኑት ከሶስት ሳምንታት በፊት መሆኑ ይታወቃል። ፋሲልና መሳይ ባለፉት ሶስት ሳምንታት የኤርትራ ቆይታቸው የሄዱበትን ዓላማ በሚገባ ማሳካታቸውን  ጋዜጠኛ ፋሲል ገልጿል። በኤርትራ ...

Read More »

<<ሁላችንም የለውጥ ሀይሎች ያለን አማራጭ ሁለት ነው፤ አንደኛው እንደሰው መኖር ነው፤ ይህ ካልሆነ መብትን ለማስከበር እስከመጨረሻው መጽናት ነው>>ሲል ጋዜጠኛ ስለሽ ሀጎስ ገለጸ።

ጥር ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በትናንቱ የአንድነት ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በፖሊሶች ከፍተኛ ብትር ያረፈበትና የአካል ጉዳት የደረሰበት ጋዜጠኛ ስለሽ ታሞ በተኛበት ከኢሳት ጋር ባደረገው አጭር ቆይታ ትናንት እንደሱ የከፋ በትር ላረፈባቸው የትግል አጋሮቹ እና ለለውጥ ሀይሎች በሙሉ፦<< አይዟችሁ!እንበርታ! መብታችንን ለማስከበር ከምናደርገው ትግል በፍጹም ወደ  ሁዋላ እንዳንል፤ 2007 የለውጥ ዓመታችን ነው”ሲል መልእክት አስተላልፏል። በሰልፉ ላይ እንዴት እና በምን ...

Read More »

ራዲዮ ፋና የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ካወያየ በሁዋላ ፕሮግራሙን  አልለቅም አለ። ውይይቱ ኢሳት ዝግጅት ክፍል ገብቷል።

ጥር ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መጪውን ምርጫ ተከትሎ ራዲዮ ፋና “ሞጋች” በተሰኘ ፕሮግራሙ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን ለውይይት በመጋበዝ በተለይም አመጽ ቀስቃሾች መሆናቸውን በሚያሳጣ መልኩ ፕሮግራሞችን ሲለቅ ቆይቷል። ባለፈው ሳምንት የአንድነት አመራሮችን- ከድርጅቱ ካፈነገጡት ከነትእግስቱ አወል ቡድን ጋር በማከራከር  ለህብረተሰቡ አንድነቶች የተከፋፈሉ ናቸው የሚል መል እክት በስፋት ያስተላለፈው ራዲዮ ፋና፤  ሀሙስ እና አርብ እለት በተመሳሳይ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ-መንበር ...

Read More »