ኀዳር ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በወሎ፣ቆቦና ዋግ ህምራ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች የዘንድሮው ድርቅ ከ1977ቱ ያልተለየ ነው በማለት ለኢሳት ተናገሩ፡፡ ተጎጂዎች በድርቁ በርካታ ሃብት ንብረታቸውን በመጨረሳቸው ባዶ እጃቸውን እንደቀሩ ይናገራሉ፡፡የገዢው መንግስት ሚዲያዎች በድርቁ የሞተ ሰው የለም በማለት ለማስተባበል ቢሞክሩም ተጎጅዎቹ ‹‹ ከሃብታችን ባሻገር ልጆቻችን እየተነጠቅን ነው፡፡ ›› በማለት በተጨባጭ ያለውን የወቅቱን ችግር ይገልጻሉ፡፡ ድርቁ ዘንድሮ በይፋ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ኢትዮጵያ ወደ ኬንያ የሚወስዱ መንገዶችን ዘጋች
ኀዳር ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው አርብ በኬንያ ፖሊስና እና በኢትዮጵያ ወታደሮች መካካል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ 3 የኬንያ ፖሊሶች እና 4 የኢትዮጵያ ወታደሮች መገደላቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያ ወደ ኬንያ የሚወስዱ መተላለፊያ መንገዶችን ዘግታለች። ሞያሌ፣ ሶሎሎ፣ ፎሮሌ፣ ዱካና እና ኢሌሪቲ የተባሉት የድንበር መተላለፊያዎች ተዘግተዋል። የኢትዮጵያ ወታደሮች የኦነግ ታጣቂዎችን ለመዋጋት በሚል ወደ ኬንያ በመግባታቸው የተኩስ ልውውጡ ተደርጓል። በድንበር አካባቢ ...
Read More »የእስራኤል መንግስት የመጨረሻ ዙር ቤተ እስራኤላዊያን ወደ አገሩ እንዲገቡ ፈቀደ
ኀዳር ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለብዙ ዓመታት ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው ሲጉላሉ የነበሩት 9 ሽህ ቤተ-እስራኤላዊያን ወደ እስራኤል እንዲገቡ በእስራኤል መንግስት ፍቃድ ማግኘታቸው እንዳስደሰታቸው በተስራኤላዊያኑ ተናግረዋል።እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ1970 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ እስራኤል እንዲገቡ የተፈቀደላቸው ቤተ እስራኤላዊያን ከሰላሳ ዓመታት በላይ በተለያዩ ሁኔታዎች ጉዟቸው መደናቀፉ ያሳዘናቸው ሲሆን ዘግይቶም ቢሆን ውሳኔ መሰጠቱን በጸጋ ተቀብለውታል። ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ ኢትዮ-እስራኤላዊያን በእስራኤል ማኅበረሰብ መድሎና ...
Read More »የጉጂ ማህበረሰብ አባላት ህዝባዊ እምቢተኝነት ለመጀመር እየተዘጋጀን ነው አሉ
ኀዳር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በጉጂ ዞን የሚኖሩ የተለያዩ ብሄረሰቦች በአንድ ላይ በመሆን ያቀረብነው የመልካም አስተዳደር እና የፍትህ ጥያቄ ካልተመለሰ የህዝባዊ እምቢተኝነት ተቃውሞአቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። የዞኑ የአገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ሰዎችና የአካባቢው ባለስልጣናት በአንድነት ሆነው ኦሮምያ ክልል በመሄድ ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ መልስ ሊያገኙ አልቻሉም። ጥያቄያቸውን ይዘው ወደ ጠ/ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ማምራታቸውንም ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ለኢሳት ገልጸዋል። አስተባባሪዎች ...
Read More »በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች ዜጎች በምግብ እጥረት እየተሰቃዩ ነው
ኀዳር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአለማቀፍ ድርጅቶች ችግሩ አሳሳቢ መሆኑን እየገለጹ ሲሆን፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ችግሩ አስከፊ ሆኖ ቀጥሎአል። በደቡብ ኦሞ ዞን የሚገኙ አርብቶአደሮች በድርቅ፣ ከግልገል ጊቤ ግድብ ግንባታና በአካባቢው የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ከመከላከያ ሰራዊት በሚደርሰው ጥቃት፣ ለምግብ እጥረት መጋለጣቸውን የደቡብ ኦሞ ህዝብ ድርጅት ምክትል ሰብሳቢ አቶ አለማየሁ መኮንን ተናግረዋል።በአማራ ክልል በተለይ በሰሜን ወሎ አካባቢ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ...
Read More »ብአዴን የባጃጅ አሽከርካሪዎች ሰልፍ እንዲወጡ ሲያሳድድ እንደነበር ተገለጸ
ኀዳር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ህዳር 9፣ 2008 ዓም ብአዴን በሰልፉ ለመሳተፍ የሚፈልገውን አሽከርካሪ ማግኘት ባለመቻሉ የባጃጅ ማህበር አመራሮችን በመንገድ ትራንስፖርት አማካኝነት በመጥራት በሰልፉ ባይሳተፉ የአምስት መቶ ብር ቅጣት እንደሚፈጽም በማስፈራራት ከቀኑ 10፡30 እስከ 11፡30 መንገዶችን በመዘጋጋት ህብረተሰቡን ሲያስጨንቅና ባጃጆችን ተሰለፉ በማለት ሲያሳድድ እንደነበር ዘጋቢያችን ገልጻለች። የባህርዳር ነዋሪዎች ብአዴን በዓሉን ብቻውን እያከበረ መሆኑን ያየንበት ክስተት ነው ብለዋል። ...
Read More »የብአዴን ታጋዮች የሞትንለት እና የደማንለት ድርጅት አክስሮናል አሉ፡፡
ኀዳር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ብአዴን ህዳር 11 በባህርዳር በሚያከብረው በአል ላይ ለነባር ታጋዮች ልዩ የሽልማት ስነስርዓት ያዘጋጀ ሲሆን፣ ለሽልማቱ የታጩት አመራሮች በድርጅት ነባር አባላት አስተያየት እንዲሰጥባቸው ማድረጉን ተከትሎ፣ ነባር ታጋዮቹ በብአዴን አመራሮች ላይ የሰላ ትችት አቅርበዋል፡፡ ታጋዩች ከድል በሁዋላ እስከ ሜጀር ጀኔራልነት የሚደርስ ማዕረግ ቢሰጠንም ከመዝገብ ቤት ያለፈ የውሳኔ ሰጭነት ስልጣን የለንም ብለዋል፡፡ ነባር አባሎቹ “ብአዴን ...
Read More »በኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር ውስጥ ፍርሃት ነግሷል
ኀዳር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ በነሃሴ ወር ባካሄደው 10ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ የመልካም አስተዳዳር ችግሮችን ለመፍታት ከከፍተኛ አመራሩ ጀምሮ እርምጃ እንደሚወድድ ውሳኔ ቢያሳልፍም አብዛኛው አመራር የችግሩ ሰለባ በመሆኑ በግንባሩ እርስበእርስ ከፍተኛ መፈራራትና መጠባበቅ መከሰቱ ታውቋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት በሚለው ጉዳይ ላይ ልዩነት ያላቸው ሁለት ቡድኖች በግልጽ መውጣታቸው ታውቆአል፡፡ራሱን ንጹህ አደርጎ የሚያየው ቡድን ድርጅቱ አጥፊዎችን ...
Read More »በሰሜን ሸዋ 23 እስረኞች አመለጡ
ኀዳር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ማክሰኞ ሸዋ ሮቢት በቀወት ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የነበሩ እስረኞች በሙሉ ያመለጡ ሲሆን፣ እስረኞቹ እስካሁን አልተያዙም። አብዛኞቹ እስረኞች በህገወጥ መንገድ ትነግዳላችሁ ተብለው የተያዙ ነበሩ። እስረኞቹ ሌሊት ላይ የጭቃ ቤቱን ግድግዳ በውሃ አርሰው ከቀደዱት በሁዋላ ሁሉም በአንድ ላይ አምልጠዋል። ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ እስረኞችን ለመያዝ ፍተሻ በመካሄድ ነው። የወረዳው ነዋሪዎች እስረኞችን አምጡ በማለት ...
Read More »የዞን 9 ጦማሪ ዘላለም ክብረት ከአገር እንዳይወጣ ታገደ
ኀዳር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እንደ አውሮፓዊያን ዘመን አቆጣጠር በ2015 ዓ.ም ዓለማቀፍ የድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን የነጻነት ሽልማት በሲቲዝን ጆርናሊዝም ጋዜጠኝነት ምድብ አሸናፊ በመሆን ተሸላሚ የሆኑትን ዞን 9 በመወከል ጦማሪ ዘላለም ክብረት ሽልማታቸውን ለመውሰድ ወደ ፈረንሳይ ሊያደርገው የነበረው ጉዞ በኢትዮጵያ የደኅንነት ኃይሎች ፓስፖርቱን በመነጠቁ መታገዱ እንዳሳሰበው ዓለምአቀፉ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን ገልጿል። ”የጉዞ እገዳው በዘላለም ክብረት ...
Read More »